ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ “እግዚአብሔር የሚጠሩትን ከመስማት ወደ ኋላ አይልም”።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

ር.ሊ..ጳ. ፍራንቼስኮስ እዚህ በሮም ውስጥ በተዘጋጀው 130 አዳዲስ ጳጳሳት ተሳታፊ በሆኑበት ሥልጠና ጳጳሳት ኣንዴጥ ኣድርገው ተልዕኮቸውን በዚህ ባለንበት ዓለም ባለች ቤተክርስቲያን ውስጥ ማሳካት እንዳለባቸው የሚተነትን ረዘምና ጠንከር ያለ ንግግር ማድረጋቸውን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ዴቦራ ዶኒኒን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

በዚሁ በቅድስት መንበር ሥር ከሚገኙት 9ኙ የጳጳሳት ምክርቤት ጽሕፈት ቤት ኣንዱ በሆነው የጳጳሳት ጉዳዮችን በሚመለከት ቢሮ ኣማካኝነት የተዘጋጀዉና 130 አዳዲስ ጳጳሳት ተሳታፊ በሆኑበት ሥልጠና ማብቂያ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጳጳሳት ለካህናቶቻቸውና ካህናት ለመሆን ለሚዘጋጁ ተማሪዎች ጠንከር ያለ ሥልጠናና ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ር.ሊ..ጳ. ፍራንቼስኮስ እነዚህኑ አዳዲስ ጳጳሳት በጳጳሳዊ መማክርት ቋሚ ኣዳራሽ ሰብስበው ንግግር ባስተላለፉበት ወቅት ግልጽ በሆኑ ቃላት ዕጩ ካህናትን የማዘጋጀቱ ጉዳይ ከመጀመሪያ ምርጫ ጅምሮ በሚያደርጉት ዝግጅትና ኩትኮታ በኃላም በሚኖራቸው ቆይታ የሚደረገው ግምገማ ላይ ጠንከር ያለ ሥራ እንዲሠራ ኣሳስበዋል።

ር.ሊ..ጳ. ፍራንቼስኮስ ኣያይዘውም ቅድስና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሥጋ በእጅ መዳሰስ መሆኑን ኣስታውሰው የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ኣካል የሆነችውን ቤተክርስቲያን በእጅ ለመዳደስና በውስጧም የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በመቀጠልም ቤተክርስቲያን ውስጥ በሚነሱ ጥያቄዎችና ክስተቶች ላይ በተለይም በምዕመናኑ ዘንድ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች ላይ ተስፍ ሰጪና ትክክለኛ መልስ ካልተሰጠ የእግዚኣብሔር ዝምታ የእግዚኣብሔር ኣለመናገር ኣሳከመቼ ወደሚለው ሓሳብ ሊያመራ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በሕብረት መሥራት

ር.ሊ..ጳ. ፍራንቼስኮስ እያንዳንዱ ሰው ወደ ውስጡ በመግባት እኔ የቤተክርስቲያን ገጽታ ይበልጥ ቅዱስ የሚያደርጋት ምን ነገር ላበረክት እችላለው የሚለዉን ጥያቄ ሊጠይቅ ይገባል። በኣንድ ሰው ላይ ብቻ ሁሉንም ነገር መደምደምና በኣንድ ሰው ላይ ብቻ ጣት መቀሰር ኣንድን ሰው ብቻ በሁሉ ነገር ላይ ተጠያቂ ማድረግ ሳይሆን በሁሉም ነገር ላይ ኣብሮ መሥራትና መረዳዳት ያስፈልጋል። ምንም እንኳን በተኩላ የተከበቡ ልበ ንጹህን በጎች ሁልጊዜ በጌታቸው እርዳታና ጥንካሬ ስለሚተማመኑ ከክፉ ሁል ያመልጣሉና እኛም ሕይወቱን በሙላት ያቀረበልንን እግዚኣብሔርን በሕወታችን መሓል በማስቀመጥና ዘወትር በእርሱ በመታመን ከእግዚኣብሔር ጋር ወደፊት መሄድ ያስፈልገናል ብለዋል።

በመቀጠልም ራሳችሁን በምድር መናወጥና በጥፋት ትንቢቶች ላይ ኣታስቀምጡ ምክንያቱም ከሁሉ በላይ የሚጠቅመው ነገር በዉስጣችን ያለ ፍቅር እንዳይቀዘቅዝ መጠበቅና መንከባከብ እጃችንንና ልባችንን ወደ እግዚኣብሔር ማቅረብ ይገባል ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የኛ ሳትሆን የእግዚኣብሔርና በእርሱም የተመሰረተች ነች ብለዋል። እግዚኣብሔር በዚያ ከእኛ በፊት ነበረ ከእኛ በኃላም ይኖራል ትንሽ የሆነችው ይቺ የቤተክርስቲያን መንጋ በትልቅ ግርምትና አሸናፊነት በእግዚኣብሔር ልጅ በሆነው በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መስቀል ውስጥ ተቅምጣለች ብለዋል።

መልዕክተኞች በኃጢአት ምክንያት በሚፈተሩት ቁስሎች ስቃዮች ኣይደናገጡም፤

ር.ሊ..ጳ. ፍራንቼስኮስ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ደስታችን ባለበት ወቅት ውድቀቶችን እና መራራ ክስተቶችን እውቅና ለመስጠት ያለንን ጊዜና ጉልበት ኣናወጣም ልባችንንም ኣናስጨንቅም ይልቁኑም ከጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚወጣዉን ብርሃን በመመልከት እንነቃቃለን። ለምሳሌ በቤተሰብ ውስጥ የሕይወት ውጣ ውረድ የበዛበትና ነገር ግን እየተሻሻለ ባለበት ቦታ ይቅር መባባል የእርቅ ኃይል እንዳለዉና ብዙ የተቀደሱ ወንዶችና አገልጋዮች ካህናት መልካም ነገር መሥራት ብዙም ጫጫታ ኣያስፈልገዉም በማለት በዝምታ የሚያከናውኑት ዘርፈ ብዙ ኣገልግሎቶች በሌሎች ዘንድ ባይታወቁና በመጀመሪያ ገጽ ላይ ባይሰፍሩ ይላሉ ር.ሊ.ጳ.ፍራንቼስኮ ሁልጊዜ በሰው ልጅ ኃጢኣት ምክንያት በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰዉነት ላይ ያለዉን ቁስል ለመመልከትና ለመጋራት ወደኃላ ኣንልም።

የክርስቶስን ሥጋ መዳሰስ፤

በጊዜያችን ግለሰባዊነት በጣም የተስፋፋና የሰዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጨለመ ጊዜ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ወጣቶች በንዴትና በኃዘን ምንም ብሩህ ተስፋ እንደማይታያቸው ይታወቃል። እናም በዚሁ ዕጣ ፈንታቸው ብዙውን ጊዜ በሚያሳዝን ሁኔታ ታላቅ ኃላፊነት ሊወስዱ የሚገባቸው ሁሉ ያለማቋረጥ ይርቃሉ። ነገር ግን ጳጳሳት ይህንን ሊያደሩ ኣይችሉም ኣይገባምም ምክንያቱም ይህንን ማድረግ እንደ ር. ሊ. ጳጳሱ ኣገላለጽ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሥጋ መካድ ማለት ነው።

የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሥቃይና ቁስል የእኛው የሕይወታችን ክፍል ነው ሲሉ ኣስረግጠው ተናግረዋል እነዚህን ቁስሎች መንካት ያስፈልጋል። ይህንንም በማድረግ ሃዘንና ቁጣ በዉስጣችን ለመቀቀስ ሳይሆን የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችው ቤተክርስቲያን ሙሽራዋ ክርስቶስ ስለ እሷ ምን ያሕል እንደሚሰቃይና በዚሁም ምክንያት መልኩ እንደሚገረጣ የምትማርበት ቦታ ነው ብለዋል።

ቤተክርስቲያን ክርስቶስን በሙላት በመያዝ እንደገና መነሳት ትችላለች

ቅድስት ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ድምጽ በመስማት በትህትናና ጥብቅ በሆነ ዕምነት ከየት እንደገና መነሳት እንዳለባት ትማራለች። የቤተክረስቲያን ዓላማ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ኣዲሱን የወይን መጠጥ ለዓለም ሁሉ ማዳረስና በቁርጠኝነት ማረጋገጥ ነው። ነገር ግን ይላሉ ር.ሊ..ጳ. ፍራንቼስኮስ ይህንን ለማድረግ ኣዲስ የወይን ኣቁማዳ ያስፈልጋል። ይህ በማይሆንበት ሁኔታ ግን ሁሉም ከንቱ ይሆናል ስለዚህ ይህንን በመረዳት ለኣዲስ ወይን ኣዲስ ኣቁማዳ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

እግዚአብሔር የማይቀረብ እምላክ አይደለም፤

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በመቀጠልም ጳጳሳቱ ቤተክርስቲያንን ልክ እንደ ክርስቶስ ሙሽራ እንዲያፈቅሯት ጠይቀው ሁል ጊዜ የቅድስናችን ምንጭ እኛ እንዳልሆንንና ሁሌም መነሻው ከእግዚኣብሔር መሆኑን ኣስረድተው ይህ ከሆን ዘንድ ብለው ይቺ በዉስጣችን ያለች የቅድስና ፍንጭ በእግዚኣብሔር እጅ ውስጥ በማስገባት ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። እግዚኣንሔርን የሚገናኙት ሰዎች ሁሉ የእግዚኣብሔርን መልካምነት የእግዚኣብሔርን ቅድስና ማንፀባረቅ ይገባቸዋል። እግዚኣብሔር የማይቀረብ ኣምላክ ኣይደለም። እግዚኣብሔር ልክ እንደ ሰው ነፃነቱን ለመጠበቅ ኣጥር አይስፈልገውም ወደ እኛም ሲመጣ እኛን የሚያሳጣ ኣይደለም እንደዉም ወደ እኛ ሲመጣና ሲዳስሰን እንቀደሳለን።

የቅድስና ምንጭ የእኛ መልካም ባህሪ ተጠያቂነት የመናኝነት መርሃ ግብር የግል የስፖርት ማዘውተሪያ ወይንም ከሰኞ እስከ ሰኞ በታደሰ የአመጋገብ ስርዓት ብቻ ላይ ያተኮረ የግል ልፋት ውጤት ኣይደለም። የቅድስና ምንጭ ከወንጌል በሚመነጭ ደስታ ላይ የተመሠረተ የእግዚኣብሔር ጸጋና ይህም ጸጋ ሙሉ በሙሉ እንዲመራንና እንዲያግዘን ሁለመናችንን ለእርሱ መተው ሲሆን ከዚህ በተለየ መንገድ የቅድስናን ሕይወት መኖር አንችልም ሲሉ ኣስረድተዋል።

ተለዋዋጭነት ያለው ታማኝነት ቦታ የለዉም፤

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ለጵጳስና ማዕረግ የባለቤትነት መብት ወይም የግል መብት የሚባል ነገር የለም። ነገር ግን ሁል ጊዜ በእርሻ መካከል የተደበቀውን ሃብት ለመግዛት ሁሉን ለመሸጥ ዝግጁ እነደ ሆነው ሰው ዝግጁነትን ይጠይቃል። የእሳቸው ኣጠቃላይ ምክርና ትምህርት የሚያጠነጥነጥው የመጀመሪያዉና ኣንገብጋቢው የጵጳሳቱ የቤት ሥራ ለቅድስና የሚደረግ ሩጫ መሆን እንዳለበት የሚያመላክት ነው። በመቀጠልም ሲያስረዱ እናንተ ይላሉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ኣዲስ ለተመረጡት ጳጳሳቱ እናንተ የሌሎች ሰዎች ምርጫና ግምገማ ውጤት ፍሬ ኣይደላችሁም ይልቁንም ከላይ ከመንፈስ ቅዱስ የተመረጣችሁ መሆናችሁን ኣስታውሱ ስለዚህ በጉዞኣችሁና በኣገልግሎታችሁ ተለዋዋጭነት ያለዉን ታማኝነት በማስወገድ ይልቁንም ቀንና ማታ በማያቋርጥ ተአዝዞ ውስጥ ራሳችሁን አስገዙ ብለዋል።

የእግዚኣብሔር ኣባትነት፤

በዚህም ምክንያት ይላሉ ቅዱስ ኣባታችን ፍራንቼስኮስ ፈተና በኣሻሚ ሁኔታዎች ውስጥ ቢጥላችሁም ክፉም ነገ ተመልሶ ኣይመጣም ብሎ ሓሳቡን ቢለግሳችሁም በዚህም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ተገታችሁ ጸልዩ። እንደዉም በዚህ ጊዜ በመሬት ላይ ተደፍቶ የእግዚኣብሔርን ቃል ማዳመጥና ምንም እንኳን ጉልበት ቢከዳም ለእግዚኣብሔር ታማኝ ሆኖ መቅየት ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም ይላሉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሕዝበ እግዚኣብሔር በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ዘውትር የማይሻረዉን የእግዚኣብሔርን ኣባትነት በእናንተ ዉስጥ የመመልከትና የመግኘት ሙሉ መብት ኣለው ብለው ደምድመዋል።

14 September 2018, 18:21