2018.09.16 Angelus Domini 2018.09.16 Angelus Domini 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “የደቡብ ኢጣሊያ ሕዝብንና ምድራቸዉን እግዚኣብሔር ይባርክ”።

የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን መስቀል ስንመለከት የራሳችንን ደኅንነት እንመለከታለን

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በትናንትናው ዕለት ማለትም መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. በሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተሰበሰበው ሕዝብ በዕለቱ በተነበበው ወንጌል ላይ ኣጠር ያለ ትንታኔ ከሰጡና መልኣከ ኣግዚኣብሔር ካደረሱ በኃላ በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በተናንትናው ዕለት ሓዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሲቺሊኣ ፒያሳ ኣርመሪና እና ፓሌርሞ የብጹእ ኣባ ፒኖ ፑሊሲን የሞቱበትን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግና በቅዳሴ ሥነ ሥርዐት ለመሳተፍ ተጉዘው እንደ ነበር ተናግረዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በዚሁ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ለብጹእ ኣባ ፒኖ ፑሊሲ ለቤተክርስቲያንና ለመንግሥት ኃላፊዎች በኣጠቃላይ ይህንን ጉዞ ላመቻቹና የተለያየ ኃላፊነት ላይ ለተንቀሳቀሱ ለኣውሮፕላንና የኤሊኮፕተር ኣብራሪዎቹ ሁሉ ልባዊ መሥጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሕዝቡም ሞቅ ባለ ጭብጨባ ኣፀፋዉን መልሷል።

በመቀጠልም ለሞንሲኞር ሮዛሪኦ ጂሳና እና ለሞንሲኞር ኮራዶ ሎሬፊቼ በቦታው ላይ ለሚያደርጉት ሓዋርያዊ እንቅስቃሴ በዚህ በሚያምረው ደሴት ላይ ለሚኖሩ ምዕመናንና ምዕመናት ኣዳጊዎች ወጣቶች ስላደረጉት ኣቀባበል የተሰማቸውን ከፍተኛ እርካታና ደስታ በመግለፅ ኣመስግነዋል። በመቀጠልም የብጹእ ኣባ ፒኖ ፑሊሲ ምሥክርነት እና ምሳሌነት ለእኛ ለእያንዳዳችን ከክፉት ይልቅ መልካምነት ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር እጅግ ጠንካራ መሆናቸውን በቀጣይነት እንደሚመሰክሩልን ኣብራርተው እግዚኣብሔር ሕዝቡንና ምድራቸዉን ሁሉ እንዲባርክ ተመኝተዋል።

በመቀጠልም ልባዊና ኣባታዊ ሰላምታቸውን ከሮማ እና ከኣካባቢው ለመጡ ምዕመናን እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች ለተሰበሰቡ ነጋዲያንና ቤተሰቦች ሰበካ ቡድኖችና ማህበራት ከተለያዩ ሃገረ ስብከት ለመጡ ሕዝበ እግዚኣብሔርና ወጣቶች ኣዳጊዎች በተለይም በሚሲኦ ጆቫኒ ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎችን ሰላም ካሉ በኃላ ተሳታፊዎቹን የኢየሱስ ርህሩህ ፍቅር ምስክሮች እንድትሆኑ አበረታታችኃለሁ ብለዋል።

በመቀጠልም ከኮርዴሪኡስ ኮሌጅ የመጡትን የላቲን ቋንቋ ኣስተማሪዎችንና ተማሪዎችን ከቪቼንዛ ማርሳን ምስጢረ ሜሮን የተቀበሉትን ኣዳጊዎች እንዲሁም ከስዊዘርላንድ የኦርና ላ ቪሌ ሙዚቃ ተጫዋቾችን ሁሉ ሰላምታ ኣቅርበዋል። በመቀጠልም ዛሬ የቅዱስ መስቀልን በዓል ካከበርን ሁለት ቀን ያለፈው ቢሆንም እዚህ ለተሰበሰባችሁ ሁላችሁ የቅዱስ መስቀልን በዓል ምክንያት በማድረግ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን መስቀል ሥጦታ እሰጣችኃለው ብለው ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን መስቀል የሚከተለውን ቃል ኣስከትለዋል።

መስቀል የእግዚኣብሔር ፍቅር መገለጫ እና ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ስለ ፍቅር ብሎ የሰጠበትን እውነታ የሚያንፀባርቅ ነው። ስለዚህ ይህንን መስቀል ወደ ቤተሰቦቻችሁ ወደየ ቤታችሁ ውሰዱት በልጆቻችሁና በኣያቶቻችሁም ወይም በምትመርጡት ክፍል ኣኑሩት። ይህ መስቀል ለማጌጫነት የምንጠቀምበት ሳይሆን በጸሎት ለመመሰጥና ከእግዚኣብሔር ጋር እንድንገናኝ የሚያግዘን ኣንድ ያይማኖታዊ ምልክት መሆኑን ኣስረድተዋል። በመጨረሻም የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን መስቀል ስንመለከት የራሳችንን ደኅንነት እንመለከታለን ብለው ለተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ መልካም ምሳ ተመኝተው ተሰናብተዋል።

16 September 2018, 19:11