ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ከባሕሎች መራቅ ሰዎችን ሊያራርቅ ይችላል”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅድሚያ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ባደረጉባት በሊጧኒያ፣ ትናንት እሑድ  መስከረም 13 ቀን 2011 ዓ. ም. በካውናስ ሳንታኮስ ኣደባባይ ላይ ብዙ ምዕመናንና እንግዶች በተሰበሰቡበት፣ ኣባታዊ ሰላምታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዕለቱ በተነበቡት የብሉይ ኪዳንና የወንጌል ንባባት ላይ በመመርኮዝ ኣጠር ያለ ኣስተንትኖ ኣድርገዋል። የቅዱስነታቸውን አስተንትኖ ትርጉም ይዘት ሙሉ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

“በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ፣

ዛሬ በመጀመሪያው ንባብ ያዳመጥነው ከመጽሓፈ ጥበብ ምዕራፍ 2, 17-20 ያለውን ሲሆን ይህም ንባብ በክፉዎች ፊት የኣንድ ጻድቅ መገኘት ሁሌም ስለሚረብሻቸው ክፉ ሥራቸውን ፍንትው ኣድርጎ ስለሚያሳያቸው ይህንን መልካም ሰው ላለማየት እርሱን እንደሚያሳድዱት ይናገራል።

በዚህ በጥበብ መጽሓፈ ክፉዎች ብሎ የሚያስቀምጣቸው ድሃን የሚጨቁኑ ለባልቴቶች ርኅራኄ የማያሳዩ ሽማግሌዎችን የማያከብሩና እንዲሁም ተመሳሳይ ድርጊት የሚፈፅሙ ብሎ ይፈርጃቸዋል።

ክፉዎች የእነርሱ የተሳሳተ ኣመለካከት ሁል ጊዜ የእነርሱ ብቸኛና ኣማራጭ የሌለው የጥንካሬና የፍትህ መስፈርት እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ኃይልን በየትኛውም መልኩ በመጠቀም ኣንድን ሀሳብ ወይም ኣንድን ርዕዮተ ዓለም በሕዝቡ ላይ በመጫን በተለይም በዕለት ተዕለት ጉዞኣቸው በታማኝነትና በትህትና መልካምነትን በማራመድ ኣንድ ትልቅና መልካም ማህበረሰብ ለፍጠር ደፋ ቀና የሚሉትን ሁሉ ላማጥፋት ጉልበትን ኣሊኣም ደግሞ እስርንና እንግልትን ይጠቀማሉ። ክፉ የሆነ ሰው ማድረግ የሚፈልገዉን ክፋት ሁሉ ማድረግና በዉስጡ የሚመላለሱትን ክፉ ሓሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ ብቻም ሳይሆን ሌሎችም በፍጹም መልካምና ቅን የሆነ ነገር እንዲያደርጉ ኣለመፈልግ እና የእርሱን ሓሳብና ምኞት ብቻ እንዲፈጽሙ ከፍተኛ የሆነ ተፅእኖ ያደርጋል። ክፉ የሆነ ሰው ሁል ጊዜ መልካሙ ነገር በክፉው እንዲሸፈን ይፈልጋል መልካሙ ነገር በክፉው እንዲዋጥ ይፈልጋል።

የዛሬ 75 ዓመት በፊት ይህ ሕዝብ በቪልኒዩስ መልካም የሆኑ እሴቶች ሁሉ እንዲጠፉና ወደ ትልቅ ኣጣብቂኝ ውስጥ እንዲወድቅ የበኩሉን ኣሉታዊ ድርሻ ኣበርክቷል። ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የነበረውን ፀረ-ዕብራውያን ዘመቻ በመቀጠል ለብዙ ሺህ ዕብራውያን መጥፋት ምክንያት ሆኗል። ልክ በዚህ በጥበብ መጽሓፍ ላይ ተጻፎ እንደምናገኘው ዕብራውያኑ ብዙ ስድብና ግርፋት ስደትና ውርጅብኝ ደርሶባቸዋል የክፉ ዕጣ ፈንታ ሁሉ ተቋዳሽ ሆነዋል።

እስቲ ያንን ክፉ ጊዜ በሓሳባችን እናጢነው እና እግዚኣብሔርን ያለንበትን ጊዜ በሚገባ መረዳት የምንችልበትንና ከክፉ ሁሉ ርቀን መልካምን ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ የምንወስድበትን ብሎም ኣዲስ ኃይል የምናግኝበትን እንዲሁም በልባችን ያንን የሰቆቃና የኣደጋ ጡሩምባ የማንሰማበትን ጊዜ እንዲሰጠን እንለምነው።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ባዛሬ ወንጌል ላይ በየትኛው ፈተና ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባንና ይህ በልባችን ያለ እኔ ከሁሉ በላይ ነኝ ከሁሉ እበልጣለሁ የሚለዉን ሓሳብ በሚገባ እንድናጤነው ያስተምረናል። በሰው ልጅ ታሪክ ዉስጥ ሰው ስንት ጊዜ እኔ በሁሉ ነገር ከሁሉ የተሻልኩ ነኝ ብሎ በማሰብ ኣላስፈላግጊ ችግር ቅስጥ ይወድቃል። ይህን ዓይነት የመገፋፋት ኣስተሳሰብ በልባችንም ሆነ በኣእምሮኣችን ወይም በኅብረተሰቡና በምንኖርባት ጹለም ውስጥ ሲንሸራሸር መፍትሔው ምንድን ነው?

መፍትሔው የሁሉ የበታች መሆናችንንና የሁሉ ኣገልጋይ መሆናችንን በሚገባ መረዳት ነው። ብዙ ችግርና መከራ ወዳለበት ማንም ሰው ሊሄድ ወደማይፈልገው ወዳልሰለጠነው ማኅበረሰብ መሄድና በዛ ያለዉን ኅብረተሰብ ማገዝና ከችግሩ እንዲወጣ በሚቻለው ሁሉ ማገዝ ነው። ሰው ያለውን ጉልበትና እውቀት ለዚህ ቢያውለው ይህ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በልባችን ውስጥ በሕወታችን ውስጥ እንዲሰርፅ ብናደርገው ይህ በዓለማችን ላይ ያለው ወንድማማችነትና የጋር ጉዞ መከባበርና መረዳዳት በተሳካ መልኩ ተግባራዊ ይሆናል።

በዓለማችን ውስጥ በተለይም በአንዳንድ ሀገሮች የተለያዩ ዓይነት ጦርነቶችና ግጭቶች ሲካሄዱ እኛ ክርስቲያኖች ግን አንዱ ሌላውን እንዲገነዘብ እንዲረዳ ኣንዱ የኣንዱን ቁስሎች እንዲፈውስ የግንኙነት ድልድይዎችን እንዲገነባ መረዳዳትና መተጋገዝ የሚለዉን የቅዱስ ሓዋርያው ጳውሎስ ወደ ገላትያ 6,2 የፃፈውን መልዕክት በመጥቀስ የኢቫንጀሊውም ጋውዲኡም ሓዋርያዊ ምክር ወይም መልዕክት በቁጥር 67 ላይ ያሳስበናል።

እዚህ በሊቱአኒኣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ባለፉት መቶ ዓመታቶች ውስጥ በተለያዩ መስቀሎች ያቆሙት ምሶሶ ወይ ያስቀመጡት የመስቀል ምልክት ኣለ። በዚህ መስቀል ሥር ቆመን መልአከ እግዚኣብሔር በማድረስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአገልግሎታችን ላይ የሚገጥሙንን መስቀሎች ሁሉ ለማቃለል እንድትረዳን የእኛን አገልግሎት ለማግኘት ወደሚፈልጉበት ቦታ ሁሉ ለመድረስና ለማገልገል እንድንችል በተለያየ መንገድና በተለያየ መልኩ የተገለሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሕፃናት ኣረጋውያን ወደሚኖሩበት ከፍታና ዝቅታ ቦታ ሁሉ ለመድረስ እንድንችል በአካባቢያችንና በባሕሎቻችን ሌላውን ለማጥፋት ሌላውን ለማግለል ለማዳበር እኛን የሚያስቸግረንና የሚያስጨንቀንን ብሎም ምቾታችንን የሚነሳንን ሁሉ ለማስወገድ የሚመጣዉን ክፉ ሓሳብ ለማስወገድ እንድንችል እሷን እንለምናት።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሁላችንም ልባችን መልካም ለማድረግ መልካም ለማሰብ እንዲነሳሳና እውነተኛ መልስ ለስጠት እንድንችል የእመቤታችንን እሺታ በማሰብ የእኛም እሺታ ከእርሷ እሺታ ጋር እናእንዲመሳሰል ልክ እንድእሷ ለጋስና መልካም ልብ እንድታሰጠን እንለምናት።

ለሁላችሁም መልካም እሑድና መልካም ምሳ እመኝላችኋለው”።

23 September 2018, 17:44