ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “በሕንድ በጎርፍ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን በጸሎት ማስታወስ ያስፈልጋል”!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 13/20101 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በዕለቱ ቅዱስ ወንጌላ ላይ መስረቱን ያደርገ አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ በመቀጠል ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በዕለተ ሰንበት እኩለ ቀን ላይ ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣኩ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በቅርቡ በሕንድ በከፍተኛ ዝናብ የተነሳ በተፈጠረው ከፍተኛ ጎርፍ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ እና በርካታ ንብረት ማውደሙ እንዳሳዘናቸው የገለጹት ቅዱነታቸው በዚህ አደጋ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለተጉዱ ሰዎች መጽናናትን እንደ ሚመኙ ቅዱስነታቸው በሳምንታዊ መልእክታቸው ገለጸዋል።

በተጨማሪም በዚህ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ የተነሳ በርካታ የመሰረተ ልማት አውታሮች እና የእህል ማሳዎች ሳይቀር ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በዚህ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ  ውስጥ ከሚገኙ የሕንድ ሕዝቦቻ ጋር በጋራ በመሆን አጋርነታችንን በመግለጽ፣ የበኩላችንን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፣ በዚህ አግባብ የዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ሳይቀር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ቅዱስነታቸው ጨምረው በመልእክታቸው ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም ደግሞ በዚህ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ነፍስ መጸለይ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት በዚያው ማለትም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መንፍሳዊ ንግደት ለማድረግ የመጡ ምዕመናን ሰላምታ ያቀረቡላቸው ሲሆን በተለይም ደግሞ በወቅቱ ከዩክሬን የመጡ ወጣቶችን ቅዱስነታቸው በሳምንታዊ መልእክታቸው አመስግነዋል።

ለሁላችሁም መልካም ዕለተ ሰንበት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ በፍጹም እንዳትረሱ” በማለት ምዕመኑን ከተማጸኑ በኋላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መሰናበታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

20 August 2018, 15:11