ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ ለአከባቢ ጥበቃ ጸሎት ይደረጋል. . .”

በሚቀጥለው ቅዳሜ በዓለማቀፍ ደረጃ ለአከባቢያችን እና የጋራ መኖሪያ ቤታችን ለሆነችው ዓለማችን በጋራ፣ ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እና እንዲሁም ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በኅበረት ጸሎት ይደርጋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 23/1010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እርሳቸው ከባለፈው ከነሐሴ 19-20/2010 ዓ.ም 24ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ አየርላድ አቅንተው እንደ ነበረ፣ በዚያም ከነሐሴ 15-20/2010 ዓ.ም ድረስ በዚያው ሲከበር የነበረውን ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን መከፈላቸውን እና ቆያታቸው ያማረ እንደ ነበረ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ከገለጹ በኋላ ለምዕመናን ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት እ.አ.አ በመጪው ቅዳሜ በመስከረም 01/2018 ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ ለአከባቢ ጥበቃ ይደረግ ዘንድ ጸሎት የሚደርግበት ዕለት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በሚቀጥለው ቅዳሜ በዓለማቀፍ ደረጃ ለአከባቢያችን እና የጋራ መኖሪያ ቤታችን ለሆነችው ዓለማችን በጋራ፣ ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እና እንዲሁም ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በኅበረት ጸሎት የምናደርግበት እለት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በዚህ ዓመት በዓለማቀፍ ደረጃ ለአከባቢያችን ጸሎት በምናደርግበት ወቅት ለየት ባለ ሁኔታ የዓለማችንን የንጹዕ ውሃ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት መጸለይ እንደ ሚገባ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ውሃ የዓለማችን የሕይወት ምንጭ በመሆኑ ለሁሉም የሰው ልጆች ተደራሽ ይሆን ዘንድ ትኩረት ሰጥተን ልንጸልይ ይገባል ብለዋል።

በዚህ በመጪው ቅዳሜ በነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ ለአከባቢ ጥበቃ ጸሎት በምናደርግበት ወቅት ለየት ባለ ሁኔታ የጋራ መኖሪያ ለሆነችው ለምድራችን ጸሎት ማድረግ እንደ ሚገባ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በዚህ ጸሎት ላይ የሚሳተፉትን ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቅዱስነታቸው አስቀድመው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
29 August 2018, 14:50