ፈልግ

Vatican News
1994.10.08 Incontro Mondiale Famiglie 1994.10.08 Incontro Mondiale Famiglie 

የቤተ ሰብ ጉባኤ ከ25 ዓመታት ወዲህ ሲደረግ የቆየ የቤተ ክርስቲያን ስጦታ መሆኑ ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ እንደ ጀመሩት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን፣ የቤተ ሰብ ዓለም አቀፍ ቀንም በእርሳቸው ተጀመሮ በሌሎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጥረት እንዲያድግ የተደረገ የቤተ ክርስቲያን ስጦታ ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በጭው ዓመት በአይር ላንድ መዲና ዳብሊን የሚደረገው የቤተ ሰብ ጉባኤ ዘጠነኛው ነው። ነገር ግን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ከ25 ዓመት በፊት በሮም ከተማ እንዲካሄድ ያደረጉት የመጀመሪያው እንደሆነ ይታወቃል። የቫቲካን የዜና አገልግሎት ክፍል በሦስት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ፣ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሐዋርያዊ አስተዳደር ዓመታት የተደረጉትን የቤተ ሰብ ጉባኤዎችን ያስታውሳቸዋል።

እሁድ ግንቦት 29 ቀን 1985 ዓ. ም. የፎኮላሬ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ማህበር አባላት በጉባኤያቸው ማብቂያ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ መካፈላቸው ይታወሳል። በዕለቱም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ በጣም አስፈላጊ የሆነ ማሳሰቢያ ማቅረባቸው ይታወሳል። በሌላ ወገን 1986 ዓ. ም. የዓለም የቤተሰብ ዓመት እንዲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የታወጀ በመሆኑ ይህ ተመሳሳይ ዓመት በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዘንድም የቤተ ሰብ ዓመት እንዲሆን ታወጀ። ቤተ ክርስቲያን ይህን ዓመት የቤተ ሰብ ዓመት እንዲሆን ያወጀችበት ዋና ዓላም፣ በ12 ወራት ውስጥ በዓለም ዙሪያ ያሉት ቤተሰቦች በየቁምስናዎቻቸው እንዲገናኙ ዕድል ለመፍጠርና በኋላም በመስከረም 28 እና 29 ቀን 1987 ዓ. ም. “ቤተ ሰብ የፍቅር ምንጭ ነው” በሚል መርህ ቃል ሮም ላይ በሚደረገው ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ለማድረግ ነበር።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ እቅድ ነበር፤

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ እንደ ጀመሩት ዓለም አቀፍ የውጣቶች ቀን፣ የቤተ ሰብ ዓለም አቀፍ ቀንም በእርሳቸው ተጀመሮ በሌሎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጥረት እንዲያድግ የተደረገ የቤተ ክርስቲያን ስጦታ ነው። በመጭው ዓመት በአይር ላንድ ሊካሄድ የታቀደውን ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ቀ ጨምሮ በስድስት ከተሞች ማለትም በሮም ሁለት ጊዜ፣ በብራዚል ሪዮ ዲ ጀነይሮ፣ በፊሊፒን ማኒላ፣ በስፔን ቫለንሲያ፣ በሜክሲኮ ሲቲ፣ በኢጣሊያ ሚላኖ እና በሰሜን አሜሪካ ፊላደልፊያ የተካሄዱ ናቸው። ሦስቱን አህጉሮች እነርሱም አውሮፓ፣ እሲያንና አሜርካን ያዳረሱ ናቸው። የመጀመሪያው የቤተ ሰብ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ቤተ ሰብን በማስመልከት አስቀድመው በ19973 ዓ. ም. ያወጡት “Familiaris Consortio” የተሰኘ ሐዋርያዊ ሰነድ ይገኝበታል። ቀጥሎም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ በጥር ወር 1986 ዓ. ም. በቤተ ሰብ መካከል ሊኖር የሚገባውን ፍቅር አንገብጋቢነት በተመለከተ ሰፋ ያለ መልዕክት ጽፈዋል። የቤተ ሰብ አባላትም በሮም እንዲገናኙ ምክንያት የሆነው ይህ መልዕክታቸው ነብር። በዚህ መልዕክታቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ከሁሉ አስቀድሞ ቤተ ሰብ ማንነታቸንና ተልዕኮአቸውን በሚገባ እንዲያውቁ የሚያደርግ ነበር። በተመሳሳይ ዓመት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ሕጻናትን የሚመለከት መልዕክት አስተላልፈው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሪዮ ዲ ጀነይሮ እና የማኒላ ጉባኤዎች የቤተ ሰብ ቀንን ዓለም አቀፋዊ እንዲሆን አድርጓል፤

ከሦስት ዓመታት በኋላ በብራዚል ሪዮ ዲ ጀነይሮ የመላው ዓለም ቤተሰብ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ጋር መገናኘታቸው “ቤተሰብ የፍቅር ምንጭ ነው” የሚለው መልዕክት አንገብጋቢነትና በተግባርም እንዲተረጎም እንዳለበት የሚያሳስብ ነበር። በመስከረም 24 እና 25 1990 ዓ. ም. ይህ በብራዚል የተካሄደው የቤተ ሰብ ጉባኤ፣ ቤተሰብ ማደግና መጎልበት ያለበት የሰው ልጆች ተስፋ በሚል መሪህ ቃል የታገዘ ነበር። ቀጥሎ ከሦስት ዓመት በኋላ በሮም ከተማ የተደረገው የቤተ ሰብ ጉባኤ በአውሮፓዊያኑ 2000 ዓመት ኢዮቤልዩ ዓመት የተደረገ መሆኑ ሲታወስ የጉባኤውም መርህ ቃል፣ ልጆች የቤተሰብ እና የሕብረተሰብ ብርሃን ናቸው የሚል ነበር። በዚህ በኢዮቤልዩ ዓመት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ቤተ ሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን ቀውስ በመረዳት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ባሰሙት ንግግር፣ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን ቀውስ በመመልከት ፍርድን የምትሰጥ ወይም ከቤተ ሰብ የምትርቅ ሳትሆን ለሰዎች በሙሉ የእግዚአብሔር ቃል እንዲበራ የምታደርግ፣ ምሕረቱንም የምትመሰክር መሆን ይጠበቅባታል ብለዋል። ከሦስት ዓመት በኋላ በ1995 ዓ. ም. በእስያ አህጉር በፊሊፒን ማኒላ “ክርስቲያናዊ ቤተሰብ የሦስት ሺኛው ዓለም መልካም የምስራች ነው” በሚል መርህ ቃል የቤተ ሰብ ጉባኤ ተካሂዶ ነበር። በዚህ ጉባኤ ላይ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ በአካል ባይገኙበትም በጋብቻ ላይ የተመሠረተ ቤተ ሰብ የሰው ልጆች ሃብት በመሆኑ ለሰዎች በሙሉ መልካም ዜና ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈው ነበር።

ቤተ ሰብ እምነት የሚስፋፋበት መንገድ እንደሆነ፤

ቤተሰብ፣ ክርስቲያናዊ እና ሰብዓዊ እሴቶች የሚገለጡበት መንገድ ባሉት መልዕክታቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት መልዕክታቸው ቤተ ሰብ እየታለለበት ስላለው የነጻነት ርዕዮተ ዓለም፣ ቤተ ሰብ በምንም የአስተሳሰብ ደረጃ ሊለያይ የማይችል ውህደት እንደሆነ አስረድተዋል። በሚላኖ በተደረገው ቀጣይ ጉባኤ ወቅትም ቤተ ሰብ፣ ሥራ እና የደስታ ጊዜ በሚለው አስተምህሮአቸው፣ ቤተ ሰብን ብዙ ችግሮች እንደሚያጋጥሙት እንደመሆን የአንድ ቁምስና ወይም ካቶሊካዊ ማሕበረ ሰብ የሥራ ድርሻ ሊሆን የሚገባው ለቤተ ሰብ ፍቅርን ማሳየት፣ መንከባከብና አለኝታነትን መግለጽ ነው ብለዋል።

ቤተ ሰብ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት ነው

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሚደርገው የቤተ ሰብ ጉባኤ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት በመሆኑ ለቤተ ሰብ የሚደረገው ሐዋርያዊ አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያደርጋል። በሰሜን አሜርካ በፊላደልፊያ የተደረገው የቤተ ሰብ ጉባኤ በ2006 ዓ. ም. ከተደረገው የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ በኋላ ሲሆን የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና መርህ ቃልም በዘመናችን የቤተ ሰብ ተልዕኮና ጥሪ የሚል ነበር። መጭው ዓመት በአይር ላንድ ዋና ከተማ በዳብሊን ሊካሄድ የታቀደው የቤተሰብ ጉባኤም  ከፍቅር የሚገኝ ደስታ የተሰኘውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ መልዕክትን በጋራ በመመልከት የሚያጎለብቱበት አጋጣሚ ይሆናል።     

09 August 2018, 15:52