ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ እናንተ ወጣቶች በሕልም መንገድ ላይ የምትጓዙ መንፈሳዊ ነጋዲያን ናችሁ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “እናንተ ወጣቶች በሕልም መንገድ ላይ የምትጓዙ መንፈሳዊ ነጋዲያን ናችሁ” ማለታቸው ተገለጸ።

በጣልያን ግዛት ከሚገኙ 195 ሀገረ ስብከቶች የተውጣጡ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ለሳምንት ያህል በእግር በመጓዝ  ያደርጉትን መንፈሳዊ ንግደት በነሐሴ 05/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ ቺርኮ ማክሲሞ በሚባልበት ስፍራ ተገኝተው መንፈሳዊ ንግደታቸውን ማጠቃለላቸውን ቀድም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

በወቅቱም ወጣቶቹ ቺርኮ ማክሲሞ በመባል በሚታወቀው ስፍራ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ተገናኝተው በጋራ ጸሎት ማድረጋቸውን ለሬዲዮ ቫቲካን ከደርሰው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ አካላዊ ድካም በምያስከትለው መንፈሳዊ ጉዞ የተሳተፉ ወጣቶች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት ቅዱስነታቸ ወጣቶች የቅዱስ ወንጌል እሴት መስካሪዎች እንዲሆኑና ሕልማቸውን እንዲያምኑ ማበረታታታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

“እኛ እዚህ የተገኘነው ለእርሶ ያለንን ፍቅር ለመገለጽ እና እርሶ እያደረጉት ከምገኘው መንፈሳዊ ጎዞ ጋር አብሮ ለመጓዝ ነው” በማለት ወጣቶቹ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሰላምታ ማቅረባቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ወጣቶቹ በዚሁ በሮም ባደረጉት የሁለት ቀናት ቆይታ በጸሎት እና በደስታ መንፈስ መሞላታቸውን መግለጻቸውን፣ እንዲሁም በወጪው ጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም ለምካሄደው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ቅድመ ዝግጅት አንዱ አካል የሆነ መንፈሳዊ ንግደት መሆኑን ወጣቶቹ መግለጻቸውን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

በዓል እና ጸሎት

በጣሊያን ግዛት ውስጥ ከሚገኙ ከ195 ሀገረ ስብከቶች የተውጣጡ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያን ለአንድ ሳምንት ያህል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በእግር አቆራርጠው ባለፈው ቅዳሜ ማለትም በነሐሴ 05/2010 ዓ.ም ሮም ከተማ በደረሱበት ወቅት በአሁኑ ወቅት በመላው አውሮፓ በሚሰተዋለው ወቅታዊ የሆነ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ወጣት ነጋዲያን አካላዊ ድካም ይታይባቸው እንደ ነበረ  ከስፍራው ከደርሰን ዜና ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ነገር ግን ወጣቶቹ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለቅዱስነታቸው ሦስት የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው ቅዱስነታቸው በሰጡዋቸው መልሶች መርካታቸውን፣ መበረታታታቸው እና በተለይም ደግሞ ቅዱስነታቸው ሕልም፣ ታማኝነት እና ምስክርነት የሚሉትን ቃላት በመጠቀም የሰጡት ምላሽ የወጣቶቹን ልብ የነካ ምላሽ እንደ ነበረ ተገልጹዋል።

እንደ ደማቅ ከዋክብት ያሉ ሕልሞች

“ሕልማችሁን ወደ ተጨባጭ እውነታ መለወጥ የእናንተ ዋነኛው ተግባር ነው፣ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ብርታት ያስፈልጋችኋል” በማለት ለወጣቶቹ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ምንም እንኳን አንዳንድ ጉልማሶች በጭፍን ጥላቻ እና የተለያዩ ዓይነት ፍርሃቶች ቢኖሩባቸውም ነገር ግን ወጣቶች ምኞቶቻቸውን እና ሕልሞቻቸውን ለማሳካት በታማኝነት መጓዝ እንደ ሚኖርባቸው ቅዱስነታቸው መክረዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

የወጣቶች ህልም ለአንዳንድ አዋቂ ጎልማሶች ትንሽ አስፈሪ የሆነ ጉዳይ መሆንኑን እናንተ ታውቃላችሁ ወይ? የሚያስፈራበት ምክንያት ደግሞ ወጣቶች በጣም ረዢም የሆነ ሕልም ስላላቸው ነው። እነርሱ ምንአልባት ሕልም ማለም አቁመው ይሆናል ወይም ማለም ይፈሩ ይሆናል። ብዙን ጊዜ ከሕይወት እንደ ምንረዳው አዋቂ የሆኑ ጎልማሶች ህልም ማለም ያቆማሉ፣ ሕልም ማለም ያስፈራቸው ይሆናል፣ ምንአልባትም እናንተ ወጣቶች የምታልሙት ሕልም እነርሱ (አዋቂ ጎልማሶች) የመረጡትን የሕይወት ጉዞ ምርጫ አደጋ ላይ ስለሚጥል ሊሆን ይችላል። 

ቅዱስነታቸው ለወጣቶቹ ጨምረው እንደ ገለጹት “በ13ኛ ክፍለ ዘመን የኖረው እና የጣሊያንን ታሪክ የቀየረው፣ በወቅቱ ወጣት የነበረ እና ረዢም እና ታላቅ የሆነ ሕልም የነበረው፣ ምንም ዓይነት ድንበር ሳያግደው እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ቀን ድረስ ያልም እንደ ነበረው ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የዛሬው ዘመን ወጣቶችም ረዢም እና ጥልቅ የሆነ ሕልም ሊኖራችሁ የገባል” ያሉት ቅዱስነታቸው “ነገር ግን የሚሳካ የማይመስል ረዢም እና ታላቅ የሆነ ሕልም ማለም እና ያለማችሁትን ሕልም እውን ማድረግ የምትችሉት በእግዚኣብሔር ድጋፍ ብቻ ነው” ብለዋል። 

ፍቅር ግማሽ እርምጃዎችን አይራመድም

በነሐሴ 05/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ በሚገኘው ቺርኮ ማክሲሞ በመባል በሚታወቀው ስፍራ መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ ከመጡ ከ70 ሺ በላይ ከሚሆኑ ወጣቶች መከከል አንዷ የሆነቺው የ24 አመት እድሜ ያላት ማርቲና የተባለች ወጣት በፊናዋ ለቅዱነታቸው ባቀረበቺው ጥያቄ እንደ ገለጸችሁ እርሷ ብዙ ጎልማሳ የሆኑ ሰዎች እንደ ሚመክሩት ሳይሆን በተቃራኒው በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ ተሰማርታ ሥራ ከመስራቷ በፊት በቅድሚያ የራሷን ቤተሰብ መመስረት እንደ ምትፈልግ በመገለጽ ጥያቄ ማቅረቧ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚገኙ ጎልማሶች “የመስማት ብቃት ያላቸው እና በዋቢነት ልጠቀሱ የሚችሉ ተግባራትን ያከናወኑ ሰዎች ሊሆኑ ሲገባቸው” ነገር ግን ከዚህ በተለየ መልኩ በተቃራኒው በኩል እንደ ሚገኙ ጨምራ መግለጹዋን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እንደ ገለጹት ወጣቶች በፍጹም ፍቅርን መፍራት እንደ ሌለባቸው እና ሕይወታቸውን በዚሁ መልኩ ሊቀርጹ እንደ ሚገባ ከገለጹ በኋላ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ፍቅር የሚያስከትለው ጫና እዳለ ሆኖ፣ ፍቅር እንድናድግ እና ፍቅር ውጤታማ እንድንሆን እንደ ሚያደርገን በጥልቀት ማሰብ መፍራት የለብንም። ፍቅር የምያመጣውን ጫና ተቀበሉ! ዛሬ የምናደርገው ምርጫ ያለምንም እንቅፋት በነጻነት እስትንፋስ የማናደርገው ምርጫ ነው፣ ነገር ግን ጠንቃቃ መሆን ይኖርብናል፣ ‘ይህንን ምርጫ አደርጋለሁ ነገር ግን . . .’ የሚሉትን የማምለጫ መንገዶችን በማስወገድ የበኩላችንን ተሳትፎ ማድረግ ይኖርብናል። አንቺ ጣትሽን በቁስል ውስጥ ነው ያስገባሽው። ይህ ‘ነገር ግን’ የሚለው ቃል እንድንቆም ያደርገናል።

ምስክርነት የማትሰጥ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጭስ ትቆጠራለች።

ምስክርነት የሌለበት ቦት መንፈስ ቅዱስ የለም፣ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስትያኖች “እንዴት እንደ ሚዋደዱ ተመልኩት” እስከሚባሉ ድረስ በጣም ይዋደዱ እንደ ነበረ የገልለጹት ቅዱነታቸው ክርስቲያን መሆን ማለት ልክ እንደ አንድ ሐውልት ተገትሮ መቆም ማለት እናዳልሆን ገልጸው መስካሪዎች የሚያደርገንን ምርጫ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ዳሪዮ የተባለ አንድ የ27 አመት ውጣት በበኩሉ ለቅዱስነታቸው ባቀረበው ጥያቄ እንደ ገለጸው ሞትን በተመለከተ በእየጊዜው የሚነሱ ጠንካራ ጥይቄዎች ምላሽ ባለማገኘታቸው እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ አንዳንድ ያለተገቡ ቅሌቶች የተነሳ በአሁኑ ጊዜ የምተገኘው ቤተ ክርስቲያን ተኣማኒነት በማጣት ላይ ተገኛለች በማለት ለቅዱስነታቸው ባቀረበው ጥያቄ ቅዱነታቸው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል. . .

አንዳንድ ጊዜ ቃላቶች ስለ እግዚአብሔር ቢናገሩም እንኳ የፍቅር መልእክቱን ግን ይክዳሉ። አንዳንዴ ቅዱስ ወንጌልን የምንክደው እኛ ራሳችን ነን። የምስክርነትን መንገድ መምረጥ ይኖርብናል፣ ኢየሱስ የሚያስተምረን ከራሳችን በመውጣት ወደ ፊት እንድንጓዝ ነው (...) ያለ ምስክርነት ቤተ ክርስቲያን እንደ አንድ ጭስ ብቻ ሆና ትቀራለች።

ቤተ ክርስቲያን እናንተን ትፈልጋችኋለች

“ቤተ ክርስቲያን የእናንተን ጥንካሬ፣ የእናንተን ውስጣዊ ፍላጎት እና እምነት ያስፈልጋታል” በማለት ከ70 ሺ በላይ ለሚሆኑ በሮም ከተማ መንፈሳዊ ንግደት ላደርጉ ውጣቶች የተናገሩት ቅዱስነታቸው  እኛ ያልደረስንበት ቦታ እናንተ ቀድማችሁ ከደረሳችሁ፣ ከሐዋሪያው ጴጥሮስ ቀድሞ በመሮጥ ባዶ በነበረው በኢየሱ መቃብር ፊት ለፊት ቆሞ ይጠብቀው እንደ ነበረ ሐዋሪያው ዮሐንስ እናንተም በትዕግስ እኛን ልትጠብቁን ይገባል ብለዋል።

የወንድማማችነት መንፈስ ያስፈልገናል

“ይሁን እንጂ” አሉ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት  “ይሁን እንጂ ወደ ሩቅ ስፍራ መሄድ እና ለወንድሞቻችን ተደራሽ መሆን የምንችለው አብረን በጋራ ከእግዚኣብሔር ጋር በመሆን ስንጓዝ ብቻ እንደ ሆነ” የገለጹት ቅዱስነታቸው  ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ዛሬ በሕይወታችን ስንት ዓይነት የመቃብር ስፍራዎች ናቸው የሚያጋጥሙን! ሌላው ቀርቶ በተለያዩ ቁስሎች የሚሰቃዩ ሕዝቦች ሳይቀር እንኳን ወጣቶችም ጭምር ማለት ነው ልክ በቀብር ሥፍራ ላይ እንደ ሚቀመጥ የድንጋ ክዳን ስቃዮቻቸውን በድንጋይ ክዳን አሽገው እየኖሩ የሚገኙ ስንቶች ናቸው! በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና በክርስቶስስ ቃል ታግዘን እነዚህን የድንጋይ ክዳኖች መክፈት እና የብርሃን ጨረሮች ወደ ጨለማ ሸለቆዎች እንዲገቡ ማደርግ እንችላለን።

እንደ ተወደድን ሊሰማን ይገባል

እኛ በዚህ የሕይወት ዘመናችን በፍጥነት ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚረዳን አንድ ምስጢር መኖሩን በመገለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ምስጢር ወጣት የኢየሱስ ሐዋሪያ እንደ ነበረው እንደ “ተወዳጁ ሐዋሪያ” ዮሐንስ የመወደድ ስሜት ሊሰማን እንደ ሚገባ እና ይህም የሕይወታችን ምስጢር እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ጌታ በሆነው በእርሱ እንደ ተወደድን ማወቁ ደግሞ የሕይወታችን ትልቁ ምስጢር ነው ካሉ ከወጣቶቹ ጋር በጋራ ጸሎት ካደርጉ በኋላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ወጣቶቹን ተሰናብተዋል።

13 August 2018, 15:38