“ቤተሰብ በእግዚኣብሔር ፍቅር ላይ መሰረቱን ልያደርግ ይገባል “ቤተሰብ በእግዚኣብሔር ፍቅር ላይ መሰረቱን ልያደርግ ይገባል 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ቤተሰብ በእግዚኣብሔር ፍቅር ላይ መሰረቱን ልያደርግ ይገባል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በሐምሌ 26/2010 ዓ.ም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሁለት ቀናት በፊት የተጀመረውን የነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም አስመልክተው ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልክእክት ያፋ እንዳደረጉ ቀደም ሲል መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን በነሐሴ  ወር “ለቤተሰብ እንክብካቤ እና ጥበቃ እንዲደረግ መጸይ” እንደ ሚገባ መግለጻቸውን ቀደም ሲል መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በተመሳሳይ ወር ከነሐሴ 21-26 2018 ዓ.ም ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን እንደ ሚከበር ይታወቃል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ ቫቲካን

“በየደረጃው ለሕይወት ራሱን ክፍት ያደረገ፣ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት ኅብረት ላይ የተመሰረተ ቤተሰብ፣ በዓለም ውስጥ መልካም ዜና ሆኖ መኖሩን ቀጥሉዋል” በማለት ለእዚህ ዓለማቀፍ ጉባሄ አስተንትኖ ይሆን ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጋቢት 21/2009 ዓ.ም. መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

የዚህ ዘገባ አጠናቃሪ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ -ቫቲካን

አንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 21-26 2018 ዓ.ም በደብሊን ከተማ የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ “የቤተሰብ ወንጌል ለዓለም ደስታ” በሚል መርዕ ሐሳብ እንደ ሚከበረ ከወዲሁ የተገለጸ ሲሆን በመጋቢት 20/2009 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የሕትመት ቢሮ ከተሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደቻልነው የቤተሰብ ሕይወት ይበልጡኑ ይጠናከር ዘንድ ቅዱስነታቸው እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም. የጻፉት “አሞሪስ ላይቲሲያ” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ያሳተሙት ቃለ ምዕዳን በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር የሚተነትን ቃለ ምዕዳን በመሆኑ የቤተሰብ አባላት በዚህ ቃል ምዕዳን ውስጥ የተጠቀሱትን ቁምነገሮች በመጠቀም ሕይወታቸውን ማጠናከር እንደ ሚገባቸውም በከፍተኛ ሁኔታ በዚሁ ቃለ ምዕዳን ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 21-26 2018 ዓ.ም በደብሊን ከተማ ለሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ ያስተላለፉት መልእክት በሁለት ጥያቄዎች ላይ መሰረቱን ያደረገ ነበር። በቀዳሚነት “ቅዱስ ወንጌል ለዓለም የደስታ ምንጭ ሆኖ እየቀጠለ ነው ወይ?” የሚለው ጥያቄ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “ቤተሰብ ዛሬም ለዓለም መልካም ዜና በመሆን ላይ የግኛል ወይ”? የሚለው ጥያቄ ደግሞ ቅዱስነታቸው በቀጣይነት አንስተዋል።

“እኔ እንደ ማስበው ቤተሰብ ዛሬም ቢሆን ለዓለም መልካም ዜና ሆኖ እየቀጠለ ያለ ጉዳይ ይመስለኛል” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም አዎንታዊ አስተሳሰብ የመነጨው ቤተሰብ መሰረቱን ያደረገው በእግዚኣብሔር ላይ በመሆኑ የተነሳ ነው ማለታቸው ያትወሳል።

 “ቤተሰብ በዚህ የእግዚኣብሔር ፍቅር ላይ መሰረቱን ሲያደርግ ብቻ ነው በዓለም ውስጥ የእግዚኣብሔ ፍቅር ዳግም እንዲፈጠር ማድረግ እና የእግዚኣብሔርን ፍቅር መግለጽ የሚችለው በዚሁ መንገድ ብቻ ነው፡ ያለ እግዚኣብሔር ፍቅር እንደ እግዚኣብሔር ልጅ፣ እንደ ቤተሰብ እና እንደ እህት ወንድም ሆኑ መኖር በፍጹም አይቻልም”።

ቅዱስነታቸው ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የቤተሰብ አባላት ራሳቸውንና ሕይወታቸውን እንዲፈትሹ በማሰብ የምትኖሩት ሕይወት “በእግዚኣብሔር ፍቅር ላይ መሰረቱን ያደረገ ነው ወይ? በፍቅር እና ለፍቅር ብቻ ነው የምትኖሩት? የሚለውን ጥያቄ በመጠየቅ የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን ሊመረምሩ ይገባል ብለዋል።

“የፍቅር መገለጫ የሆኑ ተግባራትን በምናከናውናቸው እለታዊና ቀላል በሆኑ ተግባራት መግለጽ እንችላለን” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም በቀላሉ “እባክህን፣ አመሰግናለሁ እና ይቅርታ” የሚሉትን ቀለል ያሉ ቃላትን በመጠቀም መግለጽ እንደ ሚቻልም ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

02 August 2018, 09:15