ፈልግ

በአየርላን ዋና ከተማ በሆነችው በዳብሊን የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን  በአየርላን ዋና ከተማ በሆነችው በዳብሊን የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ እንጸልይላቸው!

በአየርላን ዋና ከተማ በሆነችው በዳብሊን የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ዛሬ በይፋ ተጀመረ

በአየርላንድ ዋና ከተማ በዳብሊን ከነሐሴ 15-20/2010 ዓ.ም የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በዛሬው ቀን በይፋ ተጀምሩዋል። ይህ “የቤተሰብ መልካም ዜና ለዓለም ሁሉ ደስታ ነው” በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት ያህል በሚካሄደው 9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ ለመሳተፍ በርካታ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ የቤተሰብ አባላት ተሳታፊ የሆኑበት፣ በአንድ ቤተሰብ ሕይወት ውስጥ የሚንጸባረቀው ደስታ እና ሰላም በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ የደስታ ምንጭ በመሆን፣ መልካም ዜና ሆኖ ለሌሎች በተግዳሮት ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ተስፋን የሚሰጥ አብነት በመሆኑ በቤተሰብ ውስጥ ያለውን ደስታ እና ፍቅር አጠናክሮ ማስቀጠል መቻል ማለት ለዓለም ሁሉ ደስታን መፍጠር ማለት በመሆኑ የተነሳ የቤተሰብ ሕይወት ደስተኛ እንዲሆን ግንዛቤ የምያስጨብጥ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን እንደ ሚሆን ከወዲሁ በብዙዎቹ ላይ ተስፋ ያሳደረ ክስተት ነው።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ 19ኛው ዓለማቀፍ የቤተስብ ቀን ላይ ለመሳተፍ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ (በነሐሴ 19-20/2010 ዓ.ም ማለት ነው) ወደ አየርላንድ እንደ ሚያቀኑ ከወዲሁ ይፋ ከሆነው የጉዞ መርዐ ግብር ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጡ ከ500 ሺ በላይ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እንደ ሚሳተፉ ይጠበቃል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚያው ተገኝተው በመጪው እሁድ በነሐሴ 20/2010 ዓ.ም በአየርላንድ ዋና ከተማ በዳብሊን 500 ሺ ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉም ይጠበቃል።

በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ እንጸልይ

የአየርላን ዋና ከተማ በሆነችው በዳብሊን የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በዛሬው እለት ማለትም በነሐሴ 15/2010 ዓ.ም “በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ በተለይም በችግር ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች እንጸልይ” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የቤተሰብ ቀን በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ዛሬ በይፋ መጀመሩን ቀደም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን በዚህ 19ኛው ዓለማቀፍ የቤተስብ ቀን ለመሳተፍ በአምስት አህጉራት ውስጥ ከሚገኙ ከ116 ሀገራት የተውጣጡ 500 ሺ ሰዎች መሳተፋቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

9ኛው የዓለም የቤተሰብ ቀን ዛሬ በይፋ ተጀምሩዋል

9ኛው የዓለም የቤተሰብ ቀን በነሐሴ 15/2010 ዓ.ም “በቤተሰብ ውስጥ ያለው በፍቅር የሚገኝ ደስታ የቤተ ክርስቲያን ደስታ ነው” በሚል መርዕ ሐሳብ ጸሎት በማድረግ ተጀምሩዋል። ይህ ጸሎት በአየርላንድ በሚገኙ 26 የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከቶች ውስጥ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ይህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን እስከ ሚጠናቀቅበት ቀን ድረስ በዕየለቱ በምሽት የሚደረግ የጸሎት ሐሳብ እንደ ሆነም ተገልጹዋል።

“የቅዱሳንን እና እምነትን ለእኛ ያስተላለፉ ሰዎችን መልካም አብነት በመከተል ያለማቋረጥ ብርሃኑን የሚያበራልንን ክርስቶስን በዜማ፣ በውዳሴ ጸሎት፣ በእልልታ እና መልካም መዐዛ ያለውን እጣን በማጬስ በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ አባታችን በሆነው በእግዚኣብሔር ፊት ሆነን እንጸልይላቸው” የሚል መልእክት ከእዚሁ ከዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን አዘጋጆች መተላለፉን ለቫቲካን ዜና ከደረሰው ዘገባ ለመረዳት ተችሉኋል።

የዳብሊን የሐዋርያዊ ሥራዎች አስተባባሪ ምክር ቤት ይህንን 19ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በማሰብ በተካታታይ በሦስት ቀናት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚሰጡ 60 አወደ ርዕይዎችን ማዘጋጀቱን የገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ Amoris Laetitia” አማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “በፍቅር የሚገኝ ሐሴት” በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነቸስኮስ ለንባብ ባበቁት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ዙርያ ውይይቶች እና ክርክሮች እንደ ሚደረጉ ገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዚህ ቀደም ለዚህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን የሚሆን መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደ ገለጹት በዚህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን  እርሳቸው ከዚህ ቀደም በላቲን ቋንቋ Amoris Laetitia” “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ለንባብ ባበቁት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ውስጥ የተጠቀሱትን ፍሬ ሐሳቦች በጥልቀት ለመመርመር  እድሉን የሚከፍት አጋጣሚ እንዲሆን ምኞታቸው መሆኑን ገልጸው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን በዚህ “Amoris Laetitia” የተሰኘው ቃለ ምዕዳን በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚታየው ፍቅር ለዚያ ቤተሰብ እና ከእዚያ ቤተሰብ ባሻገር ላሉ ቤተሰቦች ሁሉ ሳይቀር የደስታ ምንጭ ነው፣ በቤተሰብ ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ተግዳሮት ሊፈጠር ይችላል፣ እነዚህ ተግዳሮቶች እና ችግሮች በውይይት መፈታት ይኖርባቸዋል፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በቤተሰብ ውስጥ የሚከተስቱትን ማነኛውም ዓይነት ችግሮች በተመለከተ በችኮላ እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ጉዳዩን በጥንቃቄ መርምረው በማስተዋል ጥበብ የተሞላ እና በእግዚኣብሔር መለኮታዊ ምሕረት ላይ ተመስርተው አዎንታዊ የሆኑ መፍትሄዎችን እንድያስገኙ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ቤተሰብን በተመለከተ ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የሚረዳቸው የሕነጻ ትምህርቶችን በተከታታይ መውሰድ እንደ ሚገባቸው፣ በተጨማሪም ቤተሰብን የተመለከቱ አስተምህሮች ለዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በተገቢው መልኩ መስጠት ያስፈልጋል የሚል ጭብጥ የያዘ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
21 August 2018, 10:49