የኖክ የእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ የኖክ የእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ 

የደብሊን ሀገረ ስብከት ታሪክ በጣም በአጭሩ

ደብሊን የአየርላን ዋና ከተማ መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን 1,345,302 ነዋሪዎች የሚኖሩባት ከተማ ስትሆን በአምስተኛው ክፈለ ዘመን በኖረው እና የአየራላንድ ጠባቂ ቅዱስ በማባል በሚታወቀው በቅዱስ ፓትሪክ አማካይነት የክርስትና እምነት በሀገሪቱ መስፋፋቱ ያታወቃል። ደብሊን እ.አ.አ ከ1170 ዓ.ም ጀምሮ  በእንግሊዛዊያን ቅኝ ግዛት ሥር እንደ ነበረች የሚታወስ ሲሆን በርካታ ሕይወት የቀጠፈ መራራ ትግል ከተደረገ እና በጣም ብዙ መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ እ.አ.አ 1921 ዓ.ም አየርላንድ ነጻነቷን መጎናጸፏ ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን የደብሊን ሀገረ ስብከት እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በደብሊን ከተማ ከሚኖሩ አጠቃላይ ነዋሪዎች መካከል 1.154,298 (በመቶኛ ሲሰላ 85% ገደባ ማለት ነው) የካቶሊክ እመነት ተከታዮች እንደ ሆኑ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በደብሊን ሀገረ ስብከት ውስጥ ብቻ 199 ቁምስናዎች፣ 30 ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ 362 የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 728 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት ካህናት፣ 23 ቋሚ ዲያቆናት፣ 1008 የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተቋማት፣ 2245 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት ገድማዊያት፣ እንደ ሚገኙባት በተለይ ለቫቲካን ሬዲዮ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

25 August 2018, 11:39