ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይበሳንታ ማሪይ ማጆሬ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይበሳንታ ማሪይ ማጆሬ ባዚሊካ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በደብሊን የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማርያም በአደራ ሰጡ።

ከባለፈው ከነሐሴ 15 እስከ ነገ ነሐሴ 20/2010 ዓ.ም በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን “የቤተሰብ መልካም ዜና ለዓለም ሁሉ ደስታ ነው” በሚል መሪ ቃል 9ኛው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን በመከበር ላይ እንደ ሚገኝ ቀደም ሲል በነበሩን ዝግጅቶቻችን መግለጻችን ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በነሐሴ 20/2010 ዓ.ም በሚጠናቀቀውን 9ኛ ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ ለመሳተፍ በነሐሴ 19/2010 ዓ.ም ወደ እዚያው ማቅናታቸው ታውቁዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን የሚያደርጉትን 24ኛውን ዓለማቀፍ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት እንደ ተለመደው ማንኛውንም ዓይነት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ከሮም ከተማ በሚወጡበት እና ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሮም በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እምብርት ላይ በምትገኘው እና በአውሮፓ በማሪያም ስም ከተሰየሙት ባዚልካዎች መካከል በትልቅነቱ በሚታወቀው፣ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ግንባታው እንደ ተጠናቀቀ በሚነገርለት በሳንታ ማሪያ ማጆሬ (Sanat Maria Maggiore) ባዚሊካ ተገኝተው ይህ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው የሰመረ ይሆን ዘንድ፣ በሚጎበኝዋቸው ሀገራት ውስጥም ሳይቀር ሰላም እና ፍቅር ይስፈን ዘንድ ጉዞዋቸውን ለማርያም በደራ በመስጠት የእንደ ሚጀምሩ፣ በተመሳሳይ መልኩም ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅትም ሳይቀር በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ለእግዚኣብሔር ምስጋና እንደ ምያቀርቡ ይታወቃል።

በዚህም መስረት በነሐሴ 18/2010 ዓ.ም አመሻሹ ላይ በዚሁ በሳንታ ማሪይ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ይህ 24ኛው ዓለማቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት የሰመረ እና ፍሬያማ ይሆን ዘንድ በእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ጸሎታቸውን ወደ እግዚኣብሔር አምላክ አሳርገው ይህንን ጉዞዋቸውን ለማርያም በአደራ መስጠታቸውን ከስፍራው የደረሰ ዜና ያስረዳል።

24 August 2018, 16:32