Pacem in Teris “ሰላም በምድር ይሁን” 55ኛ አመት እዩቤሊዩ Pacem in Teris “ሰላም በምድር ይሁን” 55ኛ አመት እዩቤሊዩ 

Pacem in Teris “ሰላም በምድር ይሁን” 55ኛ አመት እዩቤሊዩ

የዛሬ 55 አመት ገደማ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዚያ 11/1963 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ዩሐንስ 23ኛ የተጽፈ በላቲን ቋንቋ “Pacem in Teris” “በአማሪኛው “ሰላም በምድር ይሁን” በሚል አርእስት የተጻፈ አንድ ሐዋሪያዊ መልእክት ለንባብ መብቃቱ ይታወቃል።

Pacem in Terris “ሰላም በምድር ይሁን” 55ኛ አመት እዩቤሊዩ

የዛሬ 55 አመት ገደማ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዚያ 11/1963 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ዩሐንስ 23ኛ የተጽፈ በላቲን ቋንቋ “Pacem in Terris” “በአማሪኛው “ሰላም በምድር ይሁን” በሚል አርእስት የተጻፈ አንድ ሐዋሪያዊ መልእክት ለንባብ መብቃቱ ይታወቃል። የእዚህ “ሰላም በምድር ይሁን” በሚል አርእስት የዛሬ 55 አመት ገደማ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ 23ኛ የተጻፈው ሐዋሪያዊ መልእክት ሰላም ልረጋገጥ የሚችለው “እውነት፣ ፍትህ፣ ፍቅር እና ነጻነት” ሲኖር ብቻ እንደ ሆነ የሚገልጽ ሐዋሪያዊ መልእክት እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት ለየት የሚያደርገው ቀደም ባሉት ጊዜያት በካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚጻፉ ሐዋሪያዊ መልእክቶች በቀጥታ የሚመለከቱት ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ብቻ የነበረ ሲሆን ይህ Pacem in Terris ሰላም በምድር ይሁን የሚለው ሐዋሪያዊ መልእክት ግን ምንም እንኳን የተጻፈው በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ተደራሽነቱ በጎ ፈቃድ ላላቸው የዓለማችን ማሕበረሰቦች በሙሉ እንደ ነበረ ይታወሳል።  ሰላም ልረጋገጥ የሚችለው “እውነት፣ ፍትህ፣ ፍቅር እና ነጻነት” ሲኖር ብቻ ነው!

ይሀ Pacem in Terris የተሰኘው ሐዋሪያዊ መልእክት የተጻፈው በወቅቱ የነበረውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ እና በወቅቱ የነበረውን የውጥረት ምልክት በመገንዘብ ይህ ውጥረት (ለምሳሌ በአሜርክ እና በቬትናም መካከል ለ20 አመታት ያህል በተደርገው ደም አፋሳሽ ጦርነት) ተከትሎ የነበረውን የሕዝብ ሰቆቃ የተመለከተ እና በተለይም ደግሞ በወቅቱ በሁለቱ ኃያላን በሚባሉ አሜርካ እና ራሻ መካከል በተፈጠረው የኒውክለር የጦር መሳሪያ ፍጥጫን ከግምት ባስገባ መልኩ ይህ በወቅቱ የነበረው ፍጥጫ ሦስተኛ የዓለም ጦርነት ልያስነሳ የሚችል ጉዳይ እንደ ሆነና ከእዚህ የኒውክለር ጦርነት ማንም ተጠቃሚ እንደ ማይሆን አውዳሚ እና በዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ሁሉ ለአደጋ የሚያግልጥ አደግኛ ክስተት በመሆኑ የተነሳ ፍጥጫው እንዲረግብ ሰላም በምድር እንዲሆን የሚማጸን ሐዋሪያዊ መልእክት ነው።

ይህ “Pacem in Terris” የተሰኘው በዩሐንስ 23ኛ የተጻፈ ሐዋሪያዊ መልእክት በአጠቅላይ በወቅቱ ይታዩ የነበሩትን “ወቅታዊ ምልክቶችን” ከግንዛቤ ያስገባ ሐዋሪያዊ መልእክት የነበረ ሲሆን እነሆ ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት የተጻፈበት 55ኛው አመት በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. በተዘከረበት ወቅት ከ55 አመታት በኃላም በሁለቱ የዓለማችን ኃያላን በሚባሉ አሜሪካ እና ራሻ መካከል በአጠቃላይ በምህራባዊያን እና በራሻ መካከል ያለው ፍጥጫ አሁንም ቢሆን ተጋግሎ የቀጠለበት እና በብዙዎች ዘንድ ሦስተኛ የዓለም ጦርነት ያስነሳል የሚል ስጋት መደቀኑ ይታወቃል።

ይህ Pacem in Teriss ሰላም በምድር ይሁን የተሰኘው ሐዋሪያዊ መልእክት በሚያዚያ 01/2010 ዓ.ም.  በቫቲካን 55ኛው አመት በተዘከረበት ወቅት እንደ ተገለጸው ይህ ሰላም በምድር ይሁን በሚል አርእስት የዛሬ 55 ዓመት የተጻፈው ሐዋሪያዊ መልእክት የሐይማኖት እና የዘር ልዩነት ሳያደርግ በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ የተላላፈ መንፈሳዊ ይዘት ያለው መልእክት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ድንበር የለሽ በመሆኗ ቤተ ክርስቲያን የምስራቃዊያን ወይም የምህራባዊያን ብቻ ሳትሆን የሁሉ በዓለማችን ውስጥ የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች እንደ ሆነች እና በእዚህ የሁላችን በሆነው ዓለማችን ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነው ሰላም በመሆኑ ይህ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ሁሉም የማኅብረሰብ ክፍል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ የሚያቀርብ ሐዋሪያዊ መልእክት እንደ ሆነም ተገልጹዋል።

“ሰላም በእውነት ላይ የተመሠረተ፣በፍትህ ስርዓት የተገነባ፣ ሕያው እና በፍቅር የተዋቀረ እና ነጻነት በስፊዊ የሚንጸባረቅበት ካል ሆነ ሰላም እንዲሁ ቃል ወይም ወሬ ሆኖ ብቻ ይቀራል” በማለት ሁሉ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በዓለማችን ውስጥ ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ የሚያቀርብ ሐዋሪያዊ መልእክት እንደ ሆነም በስፊው መገለጹ ታውቁዋል።

10 July 2018, 13:24