ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሰኔ 24/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሰኔ 24/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “በኢየሱስ ልብ ውስጥ ሁሉም ሰው ስፍራ አለው” ማለታቸው ተገለጸ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የሰኔ 24/2010 ዓ.ም. የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከመድገማቸው በፊት በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባደረጉት አስተንትኖ እንደ “በኢየሱስ ልብ ውስጥ ሁሉም ሰው ስፍራ አለው” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንታናው እለት ማለትም በሰኔ 24/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እን የሀገር ጎብኚዎች በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመኩዘው ባደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ገለጹት “በኢየሱስ ልብ ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው የለም” ማለታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ነገር ግን አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ልብ ለመግባት ከፈለገ በቅድሚያ ፈውስን መሻት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ይኖርበታል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህ ዜና አቀናባሪ፡ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

በዕለቱ ከማርቆስ ወንጌል 5፡21-43 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ከምኵራብ አለቆች አንዱ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቆ፣ “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና ድና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ በለመነው መሰረት  ኢየሱስ የእዚህን የኢያኢሮስን ልጅ ከሙታን ማስነሳቱን፣ እንዲሁ ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የኖረችው ሴት የኢየሱስን ልብስ ጫፍ በነካች ጊዜ መፈወሱዋን በሚገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ባድርገ አስተንትኖ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ኢየሱስ "የሕይወት ምንጭ" እና "ለሚያምኑት ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ" አምላክ ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ሁሉም ሰዎች በኢየሱስ ልብ ውስጥ የገኛሉ

በእዚህ መስረት በጌታ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በእርሱ ልብ ውስጥ ይካተታሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በይበልጥ ለማስረጽ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ማንም ሰው ነዝናዛ፣ በዳይ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት መብት የሌለው መስሎት ሊሰማው አይገባውም። ወደ እርሱ ልብ ለመግባት የኢየሱስ ልብ ለማግኘት የሚያስችል አንድ አስፈላጊ የሆነ መስፈርት አለ፡ ይህም የእርሱን ፈወስ መሻት እና በእርሱ መታመን ነው። እኔ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ እፈልጋለሁ፡ ከአንዳንድ ነገር፣ ከኃጢኣት፣ ከአንዳንድ ችግር እናንተ እያንዳንዳችሁ መዳን ተፈልጋላችሁ ወይ? የእዚህ ዓይነት ስሜት የሚሰማችሁ ከሆነ በኢየሱስ ተማመኑ፣ ለመዳን የሚያስፈልጉ እና ወደ ኢየሱስ ልብ ለመግባት የሚያስችሉ ሁለት መመዘኛዎች እነዚህ ናቸው፣ ለመፈወስ መሻት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ናቸው። ኢየሱስ ከሕዝቡ መካከል እነዚህን ሰዎች ለይቶ በማውጣት ስውር ማንነታቸውን በመግፈፍ ሕይወታቸው ከነበረበት ፍርሃት ነጻ በማውጣት በድፍረት ያወጣቸዋል። እርሱ ይህንን ያደርገው እነርሱ እጅግ ብዙ ሥቃይና ውርደት ከደረሰባቸው በኋላ አትኩሮ በመመልከት እና በቃሉ የፈጸመው ተዐምር ነው። እኛም ራሳችን እነዚህን ነጻ የሚያወጡ ቃላትን እና የመኖር ፍላጎት የሌላቸው ሰዎችን ሕይወት መቀየር የሚችል እይታ ለመማር እና ለመምሰል ተጠርተናል።

የደነደነ ልብ እንደ ሞት ሊፈራ ይገባዋል

ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የኖረችም ሴት በዚያ ነበረች፤  እንደምንም ብዬ የኢየሱስን ልብስ ጫፍ ብቻ እንኳ ብነካ እፈወሳለሁ” የሚል ጠንካራ እምነት እንደ ነበራት በማስታወስ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እምነት ደኽንነትን እንደ ሚያስገኝ ጠቅሰው “የእዚህች ሴት እምነት በክርስቶስ ወስጥ የሚገኘውን የማዳን ኃይል ስቦ እንዳወጣው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። የኢያኢሮስ ልጅ ሞታላች ሕይወቷም አልፉዋል በማለት ሕዝቡ የነበረውን አመለካከት በተመለክተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በእርግጥ ኢየሱስ “ብላቴናዪቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” በማለት ተናግሮ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ኢየሱስም “ጣሊታ ቁም” ትርጉሙም “አንቺ ልጅ ተነሽ” ብሎ ከተኛችበት እንዳስነሳት ገልጸው በእዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ “የእምነት ጭብጦች እና አዲስ ሕይወት እርስ በርስ” እንደ ሚገናኙ እንረዳለን ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋ . . .

ኢየሱስ ጌታ ነው አካላዊ ሞት በእሱ ፊት እንደ እንቅልፍ ስለሚቆጠር ተስፋ መቁረጥ አይኖርብንም። ሌላኛው ደግሞ የሚፈራ የሞት ዓይነት ነው፣ ይህም  በክፉ ነገሮች የተሞላ የደነደነ ልብ ነው። ኀጢአትም እንኳን ለኢየሱስ የመጨረሻ ቃል አይደለም ምክንያቱም እርሱ የአብን ዘላለማዊ ምሕረት አምጥቶልናልና። እኛ ወደቀን ብንገኝ እንኳን የእርሱን “ተነስ እና ቁም” የሚለው ጠንካራ እና ብርቱ ድምጽ ወደ እኛ ይደርሳል።

የደነደነ ልብ እንደ አንድ በድን እንደ ሚቆጠር በመግለጽ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእምነት ጉዞዋችን ከእኛ ጋር ሆና እንድትጓዝ እና በተለይም ደግሞ ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ተጨባጭ የሆነ ፍቅር ማሳየት እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም እንድትረዳን ልንማጸናት ይገባል ካሉ በኃላ ለዕለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።

 

01 July 2018, 14:23