ስደተኞች በጣሊያን የወደብ ከተማ በላፔዱዛ ስደተኞች በጣሊያን የወደብ ከተማ በላፔዱዛ  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ በሜዲተራኒያንን ባሕር ሕይወታቸውን ያጡ ስደተኞችን በጸሎታቸው አስታወሱ

ስደተኞች በጣሊያን የወደብ ከተማ በላፔዱዛ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ በሜዲተራኒያንን ባሕር ሕይወታቸውን ያጡ ስደተኞችን በጸሎታቸው አስታወሱ  

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፣ ነገ አርብ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ. ም. ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ የሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ፣ ከአምስት አመት በፊት፣ በርካታ ስደተኞች ወደ አውሮጳ በሚያደርጉት የባሕር ላይ ጉዞ ሕይወታቸውን ያጡበትን ዕለት ለመዘከር እንደሆነ ታውቋል። የቅድስት መንበር የዜና ክፍል ዳይረክተር የሆኑት ግረግ ቡርኬ እንደገለጹት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ስደተኞች፣ ከአደጋው ለተረፉትና በአደጋው ወቅት በሕይወት ማዳን ለተሳተፉት ጭምር ነው ብለዋል። የቅድስት መንበር የዜናና ሕትመት ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ግረግ ቡርኬ እንደገለጹት፣ በመስዋዕተ ቅዳሴው ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች የሚካፈሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በዘርፉ አገልግሎትን በማበርከት ላይ የሚገኙ ግለ ሰቦች ናቸው ብለዋል።

የዜናው አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ከአምስት ዓመታት በፊት ታሪካዊ የሆነውን የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ያደረጉት፣ የሜድተራንያንን ባሕር የሚያቋርጡ በርካታ ስደተኞችን በመቀበል ወደ ምትታወቀው፣ የኢጣሊያ ደሴት ወደ ሆነችው ወደ ላምፔዱሳ እንደነበር ይታወሳል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ከደቡብ አሜሪካ አህጉር ተነስተው፣ ስደተኞች የተሻለ ሕይወትን ተስፋ ወዳደረጉባት ወደ አውሮጳ ድረስ መምጣታቸው፣ የላምፔዱሳ ደሴት ነዋሪዎች ካሳዩት የደግነትና የርሕራሄ ተግባር ጋር ተገናኝቷል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በላምፔዱሳ ደሴት በምትገኘው ትንሿ ስታዲየም ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ባሳረጉበት ዕለት፣ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞችና የደሴትቱ ምእመናን ተገኝተው እንደ ነበር ይታወሳል።

ያንን ታሪካዊ ዕለት ያስታወሱት የቫቲካን ሬዲዮ ጋዘጤኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ እንደገለጹት፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ላምፔዱሳ ለመምጣት ተመኝተው ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከልብ የመነጨ እንደነበር ገልጸው፣ በእርግጥም በየዕለቱ የሚሰቃዩትን ሰዎች መከራ ለመጋራት፣ እቦታው በመገኘት፣ እጃቸቸውን ዘርግተው ለመቀበል ያደረጉት የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ እንደ ነበር ገልጸዋል። የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ የሆኑት አለሳንድሮ ጂሶቲ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላምፔዱሳ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ያሳረጉበት መንበረ ታቦት በጀልባ ቅርጽ መዘጋጀቱ የስደተኞችን አስጊ የባሕር ላይ ጉዞን ለማጉላት እንደነበር አስረድተዋል። በማከልም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዕለቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፣ በስደተኞች ላይ የደረሰው አደጋ በስደተኞች ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳዛኝ ክስተት እንደነበር ገልጸዋል። በማከልም ልብን በመውጋት ስቃይን እንደሚያስከትል እሾህ ያህል ነው ብለዋል። ስደተኞቹ የተጓዙባቸው ጀልባዎች መልካም ተስፋን ከመስጠት ይልቅ የሞትና የጥፋት መንገድ ሆነው ተገኝተዋል ብለዋል።

በዕለቱ በስደተኞች ላይ የተከሰተውን አስቃቂ አደጋን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዕለቱ ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፣ ወደ ላምፔዱሳ ደሴት የመጡበትን አብይ ምክንያት ሲገልጹ፣ ከስደተኞች እና ከመላው ምዕመናን ጋር በጸሎት ለመተባበር፣ ይህን የመሰለ አደጋ እንዳይደገም መልዕክቴን ለማስተላለፍ ነው ብለዋል።  ቅዱስነታቸው በዕለቱ ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፣ የላምፔዱሳ ነዋሪዎች ለስደተኞች የሚያደርጉትን አቀባበልና መስተንግዶን በማስታወስ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። በቁጥር ጥቂት ብትሆኑም ያላችሁትን ሁሉ በማካፈል፣ ለስደተኞች አክብሮትን፣ ፍቅርንና አንድነትን ገልጻችኋል በማለት ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዕለቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ያሰሙትን ቃለ ምዕዳን ሲያጠቃልሉ፣ በሰዎች መካከል ለሚደረገው ልዩነትና ማግለል፣ በልበ ደንዳናነታችን ለሚከሰቱት ጥፋቶች በሙሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትን ለምነው፣ ለተከሰተው የብዙ ሰዎች ሕይወት መጥፋት በቀዳሚነት ለሚጠየቁት በሙሉ ይቅርታን ተማጽነዋል። በመጨረሻም የአግሪጀንቶ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፍራንቸስኮ ሞንተነግሮ፣። በሃገረስብከቱ ምዕመናን ስም፣ በመላው የላምፔዱሳ ነዋሪዎችና በደሴቷ ተጠልላአው በሚገኙ ስደተኞች ስም ሆነው ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምስጋናን አቅርበው ወደ ስፍራው ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጽናናትን፣ የደስታንና የፍቅር መልዕክት በማከፈላቸው ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።            

05 July 2018, 10:26