GAUDETE ET EXSULTATE”  “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” GAUDETE ET EXSULTATE” “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” 

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” ለቅድስና የቀረበ ጥሪ

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በአሁኑ ዓለማችን ውስት የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የምያቀርብ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ክፍል ሁለት “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን አጠቃላይ ይዘቱን ስንመለከት በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሙሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የምያቀርብ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

“GAUDETE ET EXSULTATE”

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ”

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን

በአሁኑ ዓለማችን ውስት የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የምያቀርብ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን

መግቢያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአምስት አመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን ሦስት ሐዋሪያው ቃለ ምዕዳኖችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእዚህ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሕዳር 24/2013 ዓ.ም. Evagelii Gaudium (አቫንጄሊ ጋውዲዩም) በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ” የሚል አርእስት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ይፋ በማድረግ አሁን በምገኘው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን እንዴት መስብከ እንደ ሚገባ፣ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የምገኙትን ክርስትያናዊ እሴቶችን በሕይወታችን ለመኖር በምንጥርበት ወቅት ልናገኘው የምንችለውን እውነተኛ ደስታ በዝርዝር የሚገልጽ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም. በላቲን ቋንቋ “Amoris Laetitia” አሞሪስ ላይቲሲያ በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት በቤተሰብ ዙሪያ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር እና የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች በቤተሰብ ውስጥ የምፈጥሩትን የተለያየ ዓይነት ተግዳሮቶችን እንዴት መፍታት እንዳለባቸው የምያመልክት ቃለ ምዕዳን እንደ ነበረ የምታወቅ ቃለ ምዕዳን ስሆን፣ ከእዚያም በመቀጠል በሦስተኛ ደረጃ የሚገኘው ደግሞ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው በላቲን ቋንቋ “Gaudete ed Exultate” በአማሪኛው “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በምል አርእስት ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአምስት አመታት የጵጵስናቸው ዘመን ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት የተጻፈ አንድ ቃለ ምዕዳን በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ማብቃታቸውን ቀደም ስል መገልጻችን የምታወቅ ስሆን ይህ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን የመጥሪያ አርእስቱን የወሰደው በማቴዎስ ወንጌል 5፡12 ላይ በተጠቀሰው “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” ከምለው የወንጌል ክፍል የተወስደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የምኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የሚያቅርብ ቃል ምዕዳን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት ቅዱስነታቸው በይፋ ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በአምስት ምዕራፎች እና 177 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ቃለ ምዕዳን እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉዋል።

ኢየሱስ በእርሱ ምክንያት የሚስደዱ እና የሚዋረዱ ሰዎችን በሙሉ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በማለት የማበረታቻ ቃል ተናግሮዋቸው እንደ ነበረ፣ እግዚኣብሔር ሕይወታችንን ወደ እርሱ እንድንመልስ ጥሪ እንደ ሚያቀርብልን እና በአንጻሩም እርሱ ለእኛ እውነተኛ የሆነ ሕይወት እንደ ሚሰጠን የምያወሳ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ስሆን ትክክለኛውን ደስታ የምሰጠን እግዚኣብሔር ብቻ እንደ ሆነም በስፊው የሚያትት ቃለ ምዕዳን ነው። የቅድስና ሕይወት እንድንኖር መጠራታችንን የምገልጹ መልእክቶች እና ጥሪዎች ከመጽሐፍ ቅዱሳችን የመጀመሪያው ገጽ አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ በስፊው መጥቀሱን የምያትተው ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴት አድርጉ’ የተሰኘው የቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳን ይህም እግዚኣብሔር ራሱ ለአብርሃም ተገልጦለት እንደ ነበረ እና  “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ” (ኦ.ዘፍጥረት 17:1) በማለት እንደ ሚጀምር ያትታል።

ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ የበቃው ቃለ ምዕዳን አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የምኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ ከማድረጉ ባሻገር ወደ ቅድስና ሕይወት ለመመለስ የምያስችሉ መንገዶችን በመጠቆም በእነርሱ ላይ ማብራሪያ የምሰጥ ቃለ ምዕዳን ሲሆን የተለያዩ ዓይነት የቅድስና መንገዶችን በመጠቆም፣ በተለይም ደግሞ አሁን ባለንበት በእኛ ዘመን “እግዚኣብሔር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና” (ኤፌሶን 1:4) በማለት ለምያቀርብልን ጥሪ በቂ የሆነ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉንን መንገዶች የምያመላክት ቃለ ምዕዳን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ” በምል አርእስት በቅዱስነታቸው ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ቀድም ሲል እንደ ገለጽነው በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለ እና 177 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

በምዕራፍ አንድ በአሁን ወቅት ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እግዚኣብሔር ለእነርሱ ስላቀረበው የቅድስና ጥሪ ያመለክታል። በምዕራፍ ሁለት ላይ ደግሞ ሁለት ቀንደኛ የቅድስና ጠላቶችን ያትታል። በምዕራፍ ሦስት  በጌታ ብርሃን እይታ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ተቀምጡዋል፣ በምዕራፍ አራት ላይ ደግሞ በዛሬው ዓለማችን ውስጥ የምታዩ የቅድስና ምልክቶች የምል አርእስት የተሰጠው ሲሆን በአምስተኛው እና በመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ መንፈሳዊ ውጊያ ማድረግ፣ ነቅቶ መጠበቅ እና በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ በምል አርእስት ስፊ ትንታኔ ይዞ ቀርቡዋል። የተጻፈ

“GAUDETE ET EXSULTATE”

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ”

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን

በአሁኑ ዓለማችን ውስት የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የምያቀርብ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን

ክፍል ሁለት

 “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን አጠቃላይ ይዘቱን ስንመለከት በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሙሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የምያቀርብ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

አንተ ወይም አንቺ በኑሮህ ወይም በኑሮሽ ደስተኛ ያልሆንሽ ወይም ያልሆንክ ሰው ከሆንክ እነሆ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በምል አርእስት የጻፉት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ተገቢውን ምላሽ ይሰጥሃል/የስጥሻል።

በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ዓለማችን ውስጥ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የምትገኙ፣ የተለያዩ የሕይወት ተግዳሮቶች እየገጠሙዋችሁ የምትገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እንዲሁም አሁን ባለው ዓለማችን ውስጥ ያለውን መልካም እድል መጠቀም ያልቻላችሁ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ልጆቻችሁን በታላቅ ፍቅር ተንከባክባችሁ እያሳደጋችሁ የምትገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ለቤተሰባችሁ የምሆን እንጀራ በእየለቱ ለማግኘት የምትኳትኑ፣ የምትለፉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ የምትሰሩ የማኅበረስብ ክፍሎች፣ በእድሜያችሁ ዘመኑ ሁሉ ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ ለሀገራችሁ፣ በአጠቃላይ ለማኅበረሰቡ መልካም የሆነ ተግባር ያከናወናችሁ አረጋዊያን ሁላችሁ ይህ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በምል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዚያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ሁላችሁንም ወደ ቅድስና ሕይወት በመጋበዝ ደስተኛ የሆነ ሕይወት መኖር የምያስችላችሁን ሐሳቦች በስፊው ይተነትናል፣ ምክንያቱም ሁላችንም በፈጣሪያችን ቅዱስ የሆነ ሕይወት እንድንኖር ተጠርተናልና።

ለእናንተ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት፣ ለቄስውስት እና ለዲያቆናት፣ እንዲሁም የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በሙሉ ይህ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት የተጻፈው ቃለ ምዕዳን እናንተንም ወደ ቅድስና መንገድ የምታደርጉትን ጉዞ በደስታ እንድትጓዙ ጥሪ የምያቀርብላችሁ እና ደስተኝ ለመሆን የምያስችላችሁን መንገዶች የሚጠቁማችሁ ቃለ ምዕዳን ነው።

ለእናንተ ምሁራን፣ አዋቂዎች እና ተመራማሪዎች፣ እናንተ ብዙ ነገሮችን የምታውቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ብዙ ያወቀ ሰው ብዙ የጠበቅበታልና ባላችሁ እውቀት እና ክህሎት ታግዛችሁ ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን ዓለማችን ደስተኛ የሆነ ማኅበረሰብ የምኖርባት ዓለም በማደርግ የሰው ልጆች የተሰጣቸውን ሰብዐዊ ክብር በመጠቀም ደስተኛ እና ፍትሃዊ የሆነ የማኅበረሰብ ክፍል እንድትፈጥሩና ግብረገባዊ ያልሆነ እና በፍቅር ያልታጀበ እውቀት ከንቱ በመሆኑ የተነሳ በፍቅር እና በግብረገብ የታጀበ እውቀት አስፈላጊ እንደ ሆነ እንድትገነዘቡ በማድረግ  ይህንንም በተግባር ላይ ለማዋል የምያስችላችሁን መንገዶች በማመላከት በእግዚኣብሔር ጸጋ በታጀበ እውቀት ወደ ቅድስና መንገድ እንድታመሩ የሚያግዝ መሆኑን በመጥቀስ አስፈላጊ የሆኑ መንገዶችን የምጠቁም ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

ይህ “ደስ የበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት በሚያዚያ 01/2010 ዓ.ም በይፋ ለንባብ የበቃው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ከላይ ለመጥቀስ እንደ ሞክርነው መላው የዓለማችን ሕዝቦች በደስታ የተሞላ ሕይወት ይኖራቸው ዘድን፣ ከእዚያም በመቀጠል የቅድስና ሕይወት ለመኖር ይሞክሩ ዘንድ ጥሪ በማቅረብ ይህንን የቅድስና መንገድ ለመከተል ለምፈልግ የሰው ልጅ ሁሉ መነገዱ ክርስቶስ ብቻ እንደ ሆነ ብቻ በስፊው የምገልጽ ሲሆን በዛሬው ዓለማችን ውስጥ  እርሱን (ኢየሱስን ማለት ነው) መከተል  አሁን ካለው ዓለማችን በሰፊው እየተነጸባረቀ ከምገኘው ገንቢ ያልሆነ አስተሳሰብ በተቃራኒው መጓዝ ማለት በመሆኑ የተነሳ በእዚህ ዓለም ውስጥ በአሁን ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እይተከሰቱ የሚገኙትን መከራዎች እና ፍትሃዊ ያልሆኑ ተግባርትን ከእነርሱ መሸሽ ማለት ሳይሆን በከፍተኛ ብርታት እነዚህን ነገሮች ሰላምዊ በሆነ መልኩ መዋጋት፣ ትሁት መሆን እና የርኅራኄን መንፈስ በመላበስ ወደ ቅድስና መንገድ ያለምንም ፍርሃት መጓዝ እንደ ሚገባ የሚገልጽ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

 

10 July 2018, 13:04