ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ ቤተ ክርስቲያን እንድትስፋፋ የሚረዳት ምስጢረ ሜሮን ነው
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ “ቤተ ክርስቲያን እንድትስፋፋ የሚረዳት ምስጢረ ሜሮን ነው”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።
በእዚህ መሰረት በግንቦት 15/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ምስጢረ ሜሮን “የምድር ጨው እና ብርሃን እንድንሆን ኃይልን የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስን የምቀበልበት ምስጢር ነው” ማለታቸው መዘገባችን ይታወሳል።
በግንቦት 22/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ባለፈው ሳምንት ከጀመሩት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ክርስቶስን በሚገባ መቀበል እንችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲቀባን ልንፈቅድለት ይገባል” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በግንቦት 29/2010 ዓ.ም አሁንም በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ላይ ባደረጉት የክፍል ሦስት አስተምህሮ “ቤተ ክርስቲያን እንድትስፋፋ የሚረዳት ምስጢረ ሜሮን ነው” ማለታቸውን ለመራዳት ተችሉዋል።
የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
የዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን
በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
“በዚያኑ ዕለት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ፣ ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ አላቸው” (ዩሐንስ 20፡19.22)።
ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 29/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!