ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ እግዚኣብሔር ገዢ ሳይሆን አባት ነው።
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ እግዚኣብሔር ገዢ ሳይሆን አባት ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።
በእዚህ መሰረት በሰኔ 13/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የእግዚኣብሔርን ቃል ኪዳን በሕይወታችን በመተግበር ለመኖር የሚያስችሉንን 10 ቃላት ዙሪያ ያተኮረ አስተምህሮ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በሰኔ 13/3010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።
በእለቱ የተነበበው የእግዚኣብሔር ቃል፡
“ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም። 6እርሱም በፊደል ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የተመሠረተውን የአዲሱ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አደረገን፤ ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ ነጻነት አለ” (1ቆሮ. 3፡ 5-6, 17)።