ቅዱነታቸው “ቅዱስ ቁርባን በመንግሥተ ሰማይ አስቀድመን ቦታ እንድንይዝ የሚረዳን ምስጢር ነው” አሉ
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ቅዱስ ቁርባን በመንግሥተ ሰማይ አስቀድመን ቦታ እንድንይዝ የሚረዳን ምስጢር ነው”።
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 26/2010 ዓ.ም የደኽንነታችን ምንጭ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በትላንትናው እለት በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።
ይህ በዓል በግንቦት 26/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሆስቲያ በሚባል ስፍራ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእርሳቸው መሪነት በቅድስት ሞኒካ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ በጊዜያዊነት በተሰራ መንበረ ታቦት ላይ በመሆን መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ በኃላ የክርስቶስን ክቡር እና ቅዱስ የሆነውን ሥጋ የሚገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በመያዝ መንፈስዊ ስግደት እና አምልኮ ከተድረገ በኃላ በጸሎት የታገዘ ሁደት እንደ ተድረግ አለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ቅዱስ ቁርባን በመንግሥተ ሰማይ አስቀድመን ቦታ እንድንይዝ የሚረዳን ምስጢር ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 26/2010 ዓ.ም የደኽንነታችን ምንጭ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በተከበረበት ወቅት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያድረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።