ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “በቅናት ላይ የተመሠረቱ የሐሰት ክሶች ገዳይ የሆኑ መርዞች ናቸው”
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሰኔ 03/2010 ዓ.ም የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከመድገማቸው በፊት በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባደረጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት “በቅናት ላይ የተመሠረቱ የሐሰት ክሶች ገዳይ የሆኑ መርዞች ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።
ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 03/2010 ዓ.ም እለተ ሰንበት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ምዕመናን ዘንድ በላቲን ስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማርቆስ ወንጌል ከምዕራፍ 3፡20-35 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም፣ “ኢየሱስን ብዔልዜቡል አድሮበታል፤ አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” በማለት ስለኢየሱስ በተናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰርቱን ያደርገ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 03/3010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥርስ አደባባይ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን ዝግጅቶቻችንን በሙሉ እንድተከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።
10 June 2018, 11:14