ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (ANSA)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “በቅርቡ በአሜርካ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል የሚደረገው ውይይት መልካም ጅማሬ ነው”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሰኔ 03/2010 ዓ.ም የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በቅርቡ በአሜርካ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል የሚደረገው ውይይት መልካም ጅማሬ እንደ ሆነ ገለጹ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ቀደም ሲል ያስነበብናችሁን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ ካደርጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ደንግል ማሪያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነው፣ ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ የሚደገመው የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን እንዳበሰራት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሰለመሆኑ በሚዘክረው የገብርኤል ብሥራት ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በቅርብ ጊዜ ውስጥ በአሜሪካ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል በሲንጋፖር የሚደርገው ውይይት ገንቢ በሆነ መልኩ እንደ ሚደረግ እና በኮሪያ ልሳነ -ምድር ዘላቂ በሆነ መልኩ ሰላም የሚያረጋግጥ ውይይት እንዲሆን ምኞታቸው እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በሳምንታዊ መልእክታቸው ገልጸው ይህ ውይይት የተሳክ ይሆን ዘንድ ሁላችንም ጸሎታችንን ለእመቤታችን ለቅድስት ማሪያም ልናቀርብ ይገባል ካሉ በኃላ እንደ ተለመደው መልካም እለተ ሰንበት ለሁላችሁም እንዲሆን እመኛለሁ ብለው “እባካችሁን ለእኔ ጸሎት ማድረግ እንዳትረሱ” ካሉ በኃላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መሰናበታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

10 June 2018, 11:20