ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “ወጣቶች ከሚዋዢቁ ይልቅ ጤናማ መቃተት ቢኖራቸው ይሻላል”
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሰኔ 06/2010 ዓ.ም ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ገለጹት “ወጣቶች ከሚዋዢቁ ይልቅ ጤናማ መቃተት ቢኖራቸው ይሻላል” ማለታቸው ተገለጸ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።
በእዚህ መሰረት በሰኔ 06/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የእግዚኣብሔር ሕግ-ጋት ትዕዛዛት ላይ መስረቱን ያደርገ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ወጣቶች ወዲህ ወዲያ እያሉ ከሚዋዢቁ ይልቅ ጤናማ መቃተት ቢኖራቸው ይሻላል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ በሰኔ 06/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።
13 June 2018, 11:38