ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ የዕርገት በዓል “ የቤተክርስቲያን ተልእኮ ጅማሬን ያሳስበናል”
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ያረገበት የዕርገት በዓል በትላንትናው እለት ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በግንቦት 05/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙት ስብከት መሰረቱን አድጎ የነበረው ኢየሱስ ሐዋሪያቱን “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” (ማርቆስ 16፡15-20) በሚለው የቅዱሱ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የእርገት በዓል ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንዳሉት ገልጸው በአንድ በኩል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ክብር በቀኝ በኩል ወደ ተቀመጠበት ወደ ሰማይ ዓይናችንን እንዲያመራ ያደርጋል በሌላ በኩል ደግሞ የቤተክርስቲያን ተልእኮ ጅማሬ ያሳስበናል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 05/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።