ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን በቫቲካን የኢትዮጲያ ልዑክ ሆነው ተመረጡ ወቅት የሹመት ደብዳቤያቸውን በተቀበሉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን በቫቲካን የኢትዮጲያ ልዑክ ሆነው ተመረጡ ወቅት የሹመት ደብዳቤያቸውን በተቀበሉበት ወቅት 

ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን በቫቲካን የኢትዮጲያ ልዑክ ሆነው ተመረጡ

ሰላም፣ እርቅ፣ ስደተኞችን መቀበል እና መጠበቅ ይገባል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቫቲካን የቅድስት መንበር ልዑካን ሆነው የተመረጡ የተለያዩ ሀገራት አባስዳሮች የሹመት ደብዳቤ በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅሌሜንጦስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ።

እነዚህ የተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን በመወከል በቫቲካን የቅድስት መነበር ልዑክ በመሆን የተሾሙት አንባሳድሮች የተውጣጡት ከታንዛኒያ፣ ከሌሴቶ፣ ከፓኪስታን፣ ከሞንጎሊያ፣ ከዴንማርክ፣ ከኢትዮጲያ እና ከፊንላንድ ሀገራት የተውጣጡ አንባሳድሮች እንደ ሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ የእነዚህን ሀገራት መንግሥታት የሚወክሉ አዳዲስ የተሾሙ አባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ከተቀብሉ በኃላ ቅዱስነታቸው ባስሙት ንግግር እንደ ግለጹት በዓለማችን ውስጥ ፍትህ እና ስምምነትን ለማስፋፋት ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ በታልቅ ትዕግሥት የሚሰራው ሥራ የእኛን ሰብአዊ የቤተሰብ አንድነት እና የእያንዳንዱን አባል ውስጣዊ ክብር ባማከለ መልኩ በጋራ እምነት ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው መጥቀሳቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ በቅድስት መንበር የተለያዩ ሀገራርት መንግሥታን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የሹመት ደብዳቤ በቫቲካን በሚገኘው በቅልሜንጦስ የስብሰባ አዳራሽ በይፋ በተቀበሉበት ወቅት ያደርጉት ንግግር ትኩረርቱ አድርጎ የነበረው ሰላም፣ እርቅ፣ ስደተኞችን መቀበል እና መጠበቅ ይገባል በሚሉ ጭብጦች ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

በዓለማቀፍ ደረጃ የሚደረገው የዲምሎማሲ ግንኙነት በዓለማቀፍ ደረጃ ፍትህ እና ስምምነት እንዲፈጠር የሚያግዝ እንደ ሆነ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህም ሊከናወን የሚገባው  ሰብአዊ ቤተሰብ አንድነት እና የእያንዳንዱ አባላቱ ስብዕና ክብር ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህ ምክንያት  የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛው ዓላማ እያንዳንዱን ወንድ እና ሴት፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያን ማዕከል ያደረገ ልማት መሆን እንደ ሚገባው ቤተክርስቲያን አጥብቃ እንደ ምታምን በግንኙነቱ ወቅት ባድርጉት ንግግር የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም በዓለማቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውይይቶች እና ማዕቀፎች ማዳበር እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ከተደነገገ እነሆ ሰባት አመታትን እንዳስቆጠረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ድንጋጌ አሁንም በታደሰ መንፈስ ተግባርዊ በማድረግ  "ለሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በተለይም ደግሞ በድኽነት፣ በበሽታ እና በጭቆና ውስጥ ተዘፍቀው  እየተጎሳቆሉ ከሚገኙ ሰዎች ጋር አንድነትን በመፍጠር ከእዚህ ችግር ይላቀቁ ዘንድ የደኅንነት መንፈስ ተግባራዊ ማድረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ በግድዬለሽነት መነፈስ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ የሚገኘውን እና አጣዳፊ ምላሽ የሚሻውን ኢፍታዊ የሆኑ ሁኔታዎችን የመቃወም እና የማጋለጥ ግበረ-ገባዊ ግድቴታችንን ማንም ቢሆን ችላ ሊለው የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየተከሰተ የሚገኘውን የስደተኞች እና የጥገኝነት ተያቂዎችን ሁኔታ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ በቅድስት መንበር የተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የገዛ ሀገራቸውን አስገዳጅ በሆነ መልኩ በጦርነት እና በርሃብ እንዲሁም በተፈጥሮኣዊ ክስተቶች ይተነሳ ከሀራቸው ተሰደው በክፍተኛ ድኽነት ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች በማገዝ ጥረት ውስጥ ተሳታፊ መሆን እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በቫቲካን የቅድስት መንበር የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር በመሆን የተመረጡት በአሁኑ ወቅት በፈረንሳይ የኢትዮጲያ መነገሥት አንባሳደር የሆኑት ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ እንደ ሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ እንድጎርጎሮሳዊያኑ የቀን ቆጣጠር በጥር 13/1953 ዓ.ም በኢትዮጲያ የተወለዱ፣ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1986 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ የሕግ ትምህርት ተከታትለው መመረቃቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በተጨማሪም ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ በኢትዮጲያ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ሀገራቸውን መገልገላቸው የታወቀ ሲሆን በእዚህም መሰረት 1987-1994 የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛው፣ 1994-1996 የአማራ ቢሔራዊ ክልል ጠቃላይ ፍርድበት ዳኛ፣ 1997-2001 የአማራ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ 2001-2005 ዓ.ም የፍትህ ሚንስቴር ምክትል ሚንስቴር፣ ከ2005 ጀምሮ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነር ኮሚሽነር እና የፀረ-ሙስና ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ በመሆን መገልገላቸውን ከቅድስት መንበር የዜና እና የሕትመት ቢሮ ካገኘንው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በፈረንሳይ የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ በተመሳሳይ መልኩም ቫቲካን የኢትዮጲያን መንግሥት አንባሳደር በመሆን ከዛሬ ጀምሮ በይፋ አገልግሎታቸውን መጀመራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

17 May 2018, 13:27