ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “የቅ. ስላሴ በዓል እግዚ/ር አንድ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ፣ ቀዳሽና በፍቅር የተሞላ” እንደ ሆነ ያስረዳናል
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያቱ የላከበት የጴራቂሊጦስ በዓል በተከበረ በሳምንቱ የቅድስት ስላሴ በዓል በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 19/2010 ዓ.ም ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ የቅድስት ስላሴ በዓል በግንቦት 19/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርካታ ቄሳውስት እና ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የቅድስት ስላሴ በዓል እግዚኣብሔር አንድ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ እና ቀዳሽ፣ ሁልጊዜ በፍቅር እና ለፍቅር የሚኖር መሆኑን እንድናሰላስል በማድረግ፣ እርሱን ለሚቀበሉ ፍጡራን ሁሉ የእርሱን ውበት፣ በጎነት እና እውነት እንዲያንጸባርቁ እድሉን ይሰጣቸዋል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 19/2010 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ የቅድስት ስላሤ አመታዊ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተከበረበት ወቅት በእዚያው ለተገኙ ምዕመናን ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁ በመሆን እናድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።
የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!