ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ያደረጉት በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ባተኮረው የክፍል አንድ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሁለት አስተምህሮ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በሚያዝያ 18/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት ክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው” ማለታቸውን ቀደም ባሉት ዝግጅቶቻችን መዘገባችን ይታወሳል። በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ አገለጹት “አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም” ማለታቸው ተገልጹዋል።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።