ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም

የሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ያደረጉት በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ባተኮረው የክፍል አንድ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሁለት አስተምህሮ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በሚያዝያ 18/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት ክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው” ማለታቸውን ቀደም ባሉት ዝግጅቶቻችን መዘገባችን ይታወሳል። በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ አገለጹት “አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም.  በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፍዳችሁ”

“ከእዚህ ቀደም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ የጀመርነውን አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ የእዚህ ምስጢር ሰነ-ስረዓት በሚሰጥበት የማጥመቂያ ስፍራ ላይ ለማተኮር እወዳለሁ። በቅድሚያ መንፈስ ቅዱስ በውሃ ላይ እንደ ሚወርድ እና እደአዲስ እንድንወለድ በማድረግ አዲስ ሕይወትን የሚሰጠንን ውሃ እንመለከታለን። (ዩሐንስ 3፡5 ቲቶ 3፡5)። ውኃ ማለት የሕይወት እና የደኅንነት ማእቀፍ ነው፣ ውሃ ከሌለ ደግሞ ልክ እንደ ምድረበዳ ፍሬያማነትን ያጠፋል፡ ይሁን እንጂ ውሃ ከመጠን በላይ በሚሆንበት ጊዜ እና በጣም ከመጠን በላይ በሚሆንበት ወቅት ውስጡ ገብተን እንድንሰጥም ሰለሚያደርገን የሞት መንስሄ ሊሆንም ይችላል፣ በአጠቃላይ ግን ወሃ የማጠብ፣ የማጥራት እና የማንጻት ኃይል አለው። ከእዚህ ቀደም ካለው መላው ዓለም ከሚያውቀው እና የውሃ ተፈጥሮአዊ ተምሳሌት በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስ ውሃን በምልክትነት በመጠቀም እግዚአብሔር በውሃ አማክይነት ያደረገውን ጣልቃ ገብነት እና ቃልኪዳን ይገልፃል። ነገር ግን ኃጢኣትን የማስተሰረይ ኃይል ያለው በውሃ ውስጥ እንዳልሆነ ቅዱስ አብሮሲዮስ ለንዑስ ክርስቲያኖች እንዲ በማለት አስረድቶዋቸው ነበር “ውሃውን አይታችኋል፣ ነገር ግን ውሃ ሁሉ አይፈውስም፣ ውሃ የሚፈውሰው የክርስቶስ ጸጋ ሲታክልበት ብቻ ነው። (. . .) ውሃ ሊፈውስ የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው” ማለቱ ይታወሳል። ለእዚህም ነው ታዲያ “ምስጢረ ጥምቀትን የሚቀበሉ ሰዎች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር ሞተው እንዲቀበሩ እና ከእርሱ ጋር ለዘለዓለም ለመኖር ከሞት እንዲነሱ” በማሰብ ነው ቤተክርስቲያንም የመንፈስ ቅዱስን ተግባር በውኃ ላይ ይወርድ ዘንድ የምትማጸንው በእዚህ ምክንያት ነው። የምስጢረ ጥምቀት ውሃ የመባረክ ስነ-ስረዓት በሚደርግበት ወቅት እግዚኣብሔር ውሃን “የምስጢረ ጥምቀት ምልክት እንዲሆን” አዘግጅቱዋል በማለት የሚጸልይ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ እንደ ተጠቀሰው በመጀመሪያ እግዚኣብሔር ዓለምን ሲፈጥር መንፈስ በውሃዎች ላይ ያንዣብብ ነበረ (ኦ. ዘፍጥረት 1:1-2) የሚለውን ያስታወሰናል፣ የጥፋት ውሃ የኀጢአት መጨረሻ እና የአዲስ ህይወት መጀመርያን ያመለክታል (ዘፍጥረት 7፡6-8,22)፣ በቀይ ባሕር በኩል የአብርሃም ልጆች ከግብፅ ባርነት ነጻ ወጥተዋል (ዘጸዐት 14:15-31)። ከኢየሱስ ግራ በተያያዘ መልኩ ደግሞ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቁን ያስታውሰናል (ማቴዎስ 3፡23-27) ከኢየሱስ ጎን የፈለቀውን ውሃ እና ደም ያስታውሰናል (ዩሐንስ 19:31-17)፣ ደቀ-መዛሙርቱ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ መላካቸውንም ያስታውሰናል (ማቴ 28፡19)። በእነዚህ ትውስታዎች በመበረታታት የሞተውን እና ከሙታን የተነሳው ክርስቶስ ጸጋ እንዲልክልን ለእግዚኣብሔር የመማጸኛ ጸሎት ይቀርባል። እናም ይህ ውሃ በውስጡ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚገኝበት ይሆናል ማለት ነው። በእዚህ ውሃ አማካይነት ነው እንግዲህ ንዑሰ ክርስቲያን የሆኑ ሰዎችን፣ ጎልማሶችን፣ እና ሕጻናትን የምናጠምቀው በእዚሁ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ባለው ውሃ አመካይነት ነው። ለምስጢረ ጥምቀት የሚሆነው ውሃ ከተባረከ በኃላ አሁን ደግሞ ልብ ምስጢረ ጥምቀትን ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይኖርበታል። ይህም የሚሆነው “ሰይጣንን እና ተግባሩን በሙሉ እክዳለሁ” የሚለውን እና ጸሎተ ሐይማኖት በመድገም ይፈጸማል፣ እነዚህ ሁለቱ ጸሎቶች ተዛማጆች እና እርስ በርስ በቅርበት የተያያዙ ናቸው። ከእግዚኣብሔር የሚለያየንን ሰይጣንን እና ተግባሩን ሙሉ በሙሉ እክዳለሁ ባልንበት ልክ በሐሳብ እና በተግባር እርሱን እንድንመስል ለሚጠራኝ ለእግዚኣብሔር “አዎንታዊ” ምላሽ እየሰጠሁኝ ነው ማለት ነው። ሰይጣን ሁል ጊዜ ይከፋፍላል፣ እግዚኣብሔር ደግሞ ሁል ጊዜ ኅብረትን ይፈጥራል፣ ማኅበርሰቡን በሙሉ አንድ ሕዝብ ያደርጋል። ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል አይችላም። የተሻሉ ነገሮችን ለመያዝ የተወሰኑ ነገሮችን መተው ይኖርብናል፣ ከእግዚኣብሔር ጋር መሆን ነው ወይስ ከሰይጣን ጋር መሆን ነው የምሻልህ? ስለእዚህ አንድን ነገር መካድ እና ለሌላው የለንን ታማኝነት መግለጽ አብሮ የሚሄዱ ነገሮች ናቸው። ስለእዚህ የክርስቶስ የሆነውን አዲስ መንገድ ለመከተል ወደ ኃላ የሚያስቀሩንን ድልድዮችን መቁረጥ እና ወደኋላ መተው አስፈላጊ ነው። “ሰይጣንን፣ ሥራዎቹን ሁሉ እና ሴራዎቹን ሁሉ ትክዳላችሁ ወይ?” ተብሎ እያንዳንዱ ንዑሰ ክርስቲያን በሚጠየቅበት ወቅት “አምናለሁ” በማለት ይመልሳል። አንድ ነገር በመካድ እና ሌላ ነገር ማመን ይህ የምስጢረ ጥምቀት ምስጢራዊ እሴት ነው። አንድ በኃላፊነት መንፈስ የሚደረግ ምርጫ፣ በእግዚኣብሔር በመተማመን ወደ ተግባር ሊለወጥ ወይም በተግባር ሊተረጎም የገባዋል። ምስጢረ ጥምቀት በእምነት የሚደረግ ተግባር በተለያዩ ሁኔታዎች እና ፈተናዎችን ተግዳሮት ስገጥመው ጸንተን ወደ ፊት እንድንጓዝ ቆራጥ እንድንሆን አስቀድሞ ያግዘናል። “ልጄ ሆይ እግዚኣብሔርን ለማገልግለ እርስህን ስታዘጋጅ፣ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ” (ሲራክ 2፡1) የሚለውን የጥንት የእስራኤልን ሕዝብ ጥበብ እናስታውሳለን። ይህም ማለት ለትግል ራስህን አዘጋጅ ማለት ነው። ይህንን ትግል በሚገባ ለመዋጋት እንችል ዘንድ ኃይል የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ ነው። የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ ወደ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በምንገባበት ወቅት ጣቶቻችንን በተባረከ ውሃ ወይም በጸበል በምናስነካበት እና በመስቀል ምልክት ራሳችንን በምናማትብበት ወቅት በደስታ እና በምስጋና መንፈስ ሆነን ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበልንበትን ቀን እናስታውሳለን-ይህ የተባረከ ውሃ ወይም ጸበል ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበልንበትን ቀን በሚገባ እንድናስታውስ ያደርገናል፣ “አሜን” ብለን የገባነውን ቃለ መሓላ እናስታውስ፣ በቅድስት ስላሴ ውስጥ ሰጥሞ መኖር በጣም የሚያስደስት ነገር ነው። ”

02 May 2018, 11:26