ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “በፋሲካ በዓል የተሰጠን የወንድማማችነት መንፈስ የክርስቲያኖች የሕይወት መገለጫ ሆኖ ሊቀጥል ይገባል!”
የመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” ጸሎት
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ባለፈው እሁድ በመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. በድምቀት ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 24/2010 ዓ.ም. ደግሞ መልኣኩ “ክርስቶስ ከሙታን ተንስቱዋል” በማለት ለማሪያም እና ለመቅደላዊት ማሪያም ያበስረበት ቀን በታላቅ መንፈሳዊነት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ መከበሩ ታውቁዋል። በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በፋሲካ በዓል ወቅት የተሰጠን የወንድማማችነት መንፈስ የክርስቲያኖች የሕይወት መገለጫ ሆኖ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸው ተገልጹዋል።
የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-- ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
01 April 2018, 15:03