የቅ. በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር ውህደት የተፈጠሩበት 125ኛው አመት በቫቲካን በተከበረበት ወቅት የቅ. በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር ውህደት የተፈጠሩበት 125ኛው አመት በቫቲካን በተከበረበት ወቅት  

የቅ. በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር ውህደት የተፈጠሩበት 125ኛው አመት ተከበረ

የበኔዲክታዊያን ገዳማዊያን ማኅበር ሕበረት የፈጠረበት 125ኛውን አመት ኢዩቤሊዩ በዓል ለማክበር እዚህ በመገኘታችሁ እያመሰገንኩኝ በተጨማሪም የገዳሙ አበ ምንዬት እዚህ ተገኝተው ላደረጉልን ንግግር ከልብ ለማመስገን እወዳልሁ።

የቅ. በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር ውህደት የተፈጠሩበት 125ኛው አመት ተከበረ

የቅዱስ በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር ከክርስቶስ ልደት በኃላ 480 ዓ.ም. በተወለደው ቅዱስ በነዴክቶስ ዘ ኖርቺያ የተመሰረተ ማኅበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ከእዚያም ጊዜ በኃላ ባሉት አመታት ውስጥ በቅዱስ በኔደክቶስ ዘ ኖርቺያ ስም እና መነፈሳዊ ዓላም የተቋቋሙ በርካት ማኅበራይ እንዳሉ ያታወቃል። በቅዱስ በነዴክቶስ ዘ ኖርቺያ ስም እና መንፈሳዊ ዓላማን በማንገብ በርካታ መንፈሳዊ መኅበራት በአንድ ቅዱስ ስም እና መነፈሳዊ ዓላማ በማንገብ በተለያዩ ጊዘያት የተቋቋሙ  በመሆናቸው የተነሳ የዛሬ 125 አመት ገደማ ውሕደትን በመፍጠር የቅዱስ በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር በሚል መጠሪያ ሕበረት መመስረታቸው ይታወቃል። ይህ ውህደት የተፈጠረበት 125ኛው አመት ኢዩቤሊዩ በሚያዚያ 12/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅለሜንጦስ አዳራሽ ተከብሮ ማለፉ የተገለጸ ሲሆን በእዚህም መሰረት የበነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር አባላት እና ወዳጆቻቸው ዛሬ ረፋዱ ላይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው ታውቁዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶ የበኔዴክቶስ መንኩሳት ማኅበር ሕበረት የፈጠሩበትን 125ኛው ኢዩቤሊዩ በዓል በተከበረበት በዛሬው ቀን ለመነኩሳቱ እና ለወዳጆቻቸው አድርገውት የነበረውን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን። አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንናጋብዛለን።

የተከበሩ አበምኒዬት የተከበራችሁ መነኩሳት የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

የበኔዲክታዊያን ገዳማዊያን ማኅበር ሕበረት የፈጠረበት 125ኛውን አመት ኢዩቤሊዩ በዓል ለማክበር እዚህ በመገኘታችሁ እያመሰገንኩኝ በተጨማሪም የገዳሙ አበ ምንዬት እዚህ ተገኝተው ላደረጉልን ንግግር ከልብ ለማመስገን እወዳልሁ። የቅዱስ በነዲክቶስ ማኅበር ላለፉት 1500 ዓመታት (የቅዱስ በኔዲክቶስ መነኩሳት ማኅበር ከክርስቶስ ልደት በኃላ 480 ዓ.ም. በተወለደው ቅዱስ በነዴክቶስ ዘ ኖርቺያ የተመሰረተ ማኅበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ከእዚያም ጊዜ በኃላ ባሉት አመታት ውስጥ በቅዱስ በኔደክቶስ ዘ ኖርቺያ ስም እና መነፈሳዊ ዓላማ የተቋቋሙ በርካት ማኅበራት እንዳሉ ያታወቃል እነዚህ በርካታ ማኅበራት በአንድ ቅዱስ ስም የሚጠሩ እና አንድ ወጥ የሆነ ዓላማ ያነገቡ በመሆናቸው የዛሬ 125 ዓመት ገደማ ውሕደት ፈጥረዋል) ያህል ለቤተ ክርስትያን ሕይወት ስላበረከቱት ጠቃሚ ድርሻ ያለኝን አጠቃላይ ምስጋና እና እውቅና ለመግለጽ እወዳለሁ። ይህ የበነዲክታዊያን የመነኩሳት መኅበር ውሕደት የፈጠሩበት 125ኛው ኢዮቤልዩ በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት ለየት በላ አሁኔታ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ልዮ 13ኛ 1893 ዓ.ም. ይህ ውሕደት እንዲፈጠር፣ አንድ የጋራ የሆነ የጸሎት ቤት እና የጋራ የነገረ መልኮት ትምህርት የሚሰጥበት ስፍራ እዚሁ በሮም እንዲመሰረት ላደርጉት ጥረት ከፍተኛ ምስጋና ልናቅርብላቸው የገባል። ይህ ውሕደት እንዲፈጠር ያነሳሳውን  እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ ምክንያቱም የመላው ዓለም የበኔዲክታዊያን መነኩሳት ማኅበር እርስ በእርሳቸው የጠለቀ የኅብረት መንፈስ እንዲኖራቸው እና ከቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ጋር ሳይቀር ሕበረት እንዲፈጥሩ አድርጓዋቸዋል። የበነዴክታዊያን የመነኩሳት ማኅበር በላቲን ቋንቋ “Ora et labora et lege” በአማሪኛው ጸሎት፣ ሥራ እና ትምህርት የሚሉትን ሦስት መንፈሳዊ እሴቶችን በዋነኛነት መርህ አድጎ የሚንቀሳቀስ ማሕበር ነው። ጸሎት፣ ሥራ እና ትምህርት። በአስተንትኖ ሕይወት ውስጥ ብዙን ጊዜ እግዚኣብሔር ባልተጠበቀ መንገድ እግዚኣብሔር በእዛ መኖሩን ይገልጻል። በስተንትኖ እና በእለታዊ ጸሎት አማክይነት የእግዚኣብሔር ቃል ማሰላሰላችን በቋሚነት እና በደስታ በመታዘዝ መነፈሳዊ የሆኑ ድምጾችን በመከተል እንድንኖር ተጠርተናል። በየዕለቱ ሥራዎቻችን ወደየ ገዳሞቻችሁ እግዚኣብሔርን በመፈለግ የሚመጡ ሰዎችን እና በየትምህርት ቤቶቻችሁ፣ በየኮሌጆቻችሁ እና በየዩኒቬርሲቲዎቻችሁ የሚማሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን የጥበብ ስጦታዎች ለእነርሱ ለማካፈል እንዲረዳን፣ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ሌሰጠን የተዘጋጀውን ድንቅ ስጦታዎች ለመቀበል ፈቃደኛ እንድንሆን ልባችንን ያነሳሳል። በዚህ መንገድ ሁሌም የታደሰ እና የተገነባ መንፈሳዊ ሕይወት ይፈጠራል። አሁን ባለበት እና እየኖርንበት በምንገኘው የፋሲካ በዓል ሰሞን ፈጣን ምላሾች እና የእግዚኣብሔርን ስጦታዎች ለመቀበል ዝግጁ እንድንሆን ልብ የሚነካ የበዓለ-ትንሣኤ በዓል ስነ-ስርዓት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባህሪያት በእርግት በየቀኑ የቤኔድክታዊያን መነኩሳት ማኅበር እለታዊ በሆነ መልኩ የሕይወታቸው አካል ነው። ቅዱስ በኔድክቶስ በሰጣችሁ ሕግ ውስጥ “ከክርስቶስ በላይ የሆነ ነገር በሕይወታችሁ አይኑር” የሚል ሕግ የሚገኝ ሲሆን ምክንያቱም ሁሌም ጠንቃቃ ሁናችሁ፣ ለማዳመጥ ዝግጁ እና በትህትና እርሱን ትከተሉ ዘንድ ለማሳሰብ በማሰብ የተናግረው ነው። ለስርዓተ አምልኮ ያላችሁ ፍቅር በመነኩሳን ሕይወት ውስጥ ያለ በጣም መስረታዊ እና አስፈላጊ የሆነ ነገር ሲሆን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ጌታ ሕይወ በሆነ መልኩ በእናንተ እንዲኖር የሚያደርግ በመሆኑ የተነሳ ለእናንተ በጣም አስፍላጊ የሆነ ነገር ሲሆን ለዘመናት በቤተክርስትያን ውስጥ ውድ በሆነ መልኩ ለብዙ መቶ ዓመታት እንደ ምንጭ ውሃ የሚያጠጣ እና ፍረያማ የሚያደርግ በመሆን፣ በግልና በማህበረሰብ ውስጥ ከሞት የተነሳው ጌታን ለመገናኘት አስችሉዋል።

ትላቁ ቅዱስ ግሪጎሮዮስ ቅዱስ በኔድክቶስን የምያበራ ኮኮበ በማለት ይጠርው እንደ ነበር የሚታወቅ ሲሆን ምክንያቱም በጊዜው የሥነ-ምግባር እሴቶች እና ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ተከስቶ የነበረ ሲሆን ይህንንም ለመፍታት በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ እና ሁለተኝእ የሆኑ ነገሮችን መለየት የቻለበት ምክንያት ጌታን በጥብቅ በመከተሉ የተነሳ ነው። እናንተ የእርሱ ተከታይ የሆናችሁ ልጆቹ በእኛ ዘመን ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣውንና ከዓለም መንፈስ ወይም ከዲያቢሎስ መንፈስ የሚመጣውን ነገር ለይታችሁ ለማወቅ አስተዋይ መሆን ይኖርባችኃል። የማመዛዘን ችሎታ ምክንያትዊ የመሆን ችሎታን አይጥይቅም ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ስጦታ ነው እንጂ። የማመዛዘን ችሎት የለለን ከሆንን ግን በጊዘው ባለው ሁኔታ እየተነዳን እንሄዳለን ማለት ነው። በዚህ ዘመን ሰዎች በጣም ሥራ ስለሚባዝብን  የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት በቂ ጊዜ የለኝም በሚሉበት በአሁኑ ወቅት፣ የእናንተ ገዳማት በበረሃ መካከል የሚገኝ አንድ በውሃ የተሞላ ሥፍራ ነው፣ የተለያየ የእድሜ ደረጃ ያላቸው፣ ከተለያዩ ባህሎች እና እምነቶች የተውጣጡ ሰዎች በእዛ የሚገኘውን ውብ የሆነ ጸጥታ እንዲያጣጥሙ እና ራሳቸውን እንዲያገኙ፣ ከፈጣሪ ጋር በመሆን ከእርሱ ጋር በመስማማት የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል። እናንተ በኔዲክታዊያን ሰዎችን ለመቀበል ያላችሁ መነፈሳዊ ጥሪ አሁን ባለንበት ዓለማችን ውስጥ እየተደረገ ላለው ወንጌልን የማስፋፋት ሂደት በጣም ተቃሚ የሆነ ነገር ሲሆን፣ ይህም እያንዳንዱን ሰው አማካይነት ክርስቶስን ለመቀበል ለመቀበል የሚያስችላችሁ በመሆኑ እና ክርስትሶን በመፈለግ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ክርስትሶ ለእያንዳንዳችን የሚሰጠንን መነፈሳዊ ስጦታ እንዲቀበሉ ስለምታስችሉ ነው በለዋል። የበነዲክታዊያን መነኩሳት ማኅበር ከሌለኦች ኃይማኖቶች ጋር ይደርጉ የአበሩ ውይይቶችን እና ድርድሮችን በተመለከተም ከፍተኛ አስተዋጾ አድርገዋል። በእዚህ በጀመራችሁት ጎዳና መጓዛችሁን በመቀጠል ለቤተ ክርስቲያናችሁ እና ለመላው ዓለም የነበራችሁን መልካም አቀባባል የማድረግ ባሕላቹን በመቀጠል ይህንን አስተዋጾ ማድረጋችሁን መቀጠል ይኖርባችኃል። የበኔዲክታዊያን ማኅበር በከተማ ውስጥ ይሁን በገጠርማ ቦታ የእናንተ ገዳማት የጸሎት እና መልካም አቀባበል የሚደርግበት ሥፍራ ነው። የእናንተ መረጋጋት እናንተን ለማግኘት ለሚመጡ ሰዎች አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በእዚህ ግንኙነት ውስጥ ክርስትሶ ይገኛል፣ ክርስትሶ በመነኩሴው ውስጥ የግኛል፣ ክርስቶስ በተቸገረ ሰው ውስጥ ይገኛል።

በሮም ከተማ ውስጥ በትምህርት ኣና በሕነጻ ዘርፍ እያበረከታችሁት ለምትገኙት አገልግሎት እንዲሁም በመላው ዓለም እያደርጋችሁት ለምትገኑት አገልግሎት ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።የበኔዲክታዊያን መነኩሳት ማኅበር “የጌታ ትምህርት ቤተ” በመባል ይታወቃሉ። ለተማሪዎቻችሁ፣ አስፈላጊውን እውቀት በመስጠት እና የእውቀት ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆን ተማሪዎቹ በሕይወታቸው እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ እንዲፈልጉ የሚያነሳሳቸውን፣ በጥበብ እንዲበለጽጉ እና እንዲጎለብቱ ማድረግ እንደ ሚገባቹ እመክራችኃለሁ።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ በመጨረሻም ውህደት የፈጠራችሁበት 150ኛ አመት ኢዩቤሊዩ እግዚኣብሔርን እና የእርሱን ጥበብ እንዴት መፈለግ እንደ ሚገባ፣ የእርሱን ብርቅ የሆኑ እሴቶች ብቃት ባለው ሁኔታ ለመጪው ትውልድድ ማስተላለፍ እንደ ሚገባችሁ እንድታሰላስሉ አጋጣሚ ይፈጥርላችኃል ቢዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የቤተ ክርስትሲያን እናት በሆነችሁ በእመቤተች ን ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት፣ ከሰማያዊቷ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር እና ከቅዱስ በኔዴክቶስ ጋር በመሆን በእያንዳዳችሁ ላይ ሐዋሪያዊ ብራኬዬ ይወርድላችሁ። አባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ። አመስግናለሁ። 

19 April 2018, 10:24