ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው።

ምስጢረ ጥምቀትን በምንሳተፍበት ወቅት የተጠመቁ ክርስትያኖች ልብ ውስጥ አንድ መንፈሳዊ የሆነ ኃይል እንዲነሳ ያደርጋል፡

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ  እንዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ያደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ  በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የተገጸ ስሆን “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም ከእዚህ ቀደም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ አድርገውት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው ማለታቸው ተገልጹዋል።

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል “ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደም መንፈስ ነው።” የሚለው እና ከዩሀንስ ወንጌል 3:5-6 ላይ ተወስዶ የተነበበው እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

“ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!”

“በእዚህ አሁን ባለንበት የፋሲካ ሰሞን ባለፈው ሳምንት በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ጀምረነው የነበረውን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንቀጥላለን። የምስጢረ ጥምቀት ትርጉም በግልጽ በእዚህ ምስጢር አሰጣጥ ላይ ያደርገ በመሆኑ የተነሳ ትኩረታችንን በእርሱ ላይ እናደርጋለን። ይህ ምስጢር በሚሰጥበት ወቅት የሚከናወኑትን ምልክቶች እና የሚባሉትን ቃላት ከግምት በማስገባት ይህ ምስጢር የሚሰጠንን ጸጋ እና ተልዕኮ ሁል ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ እየፈለግን እንድንሄድ እንዲሰማን ያደርገናል። እነዚህን ቃላት በተባረከ ውሃ ወይም ጸበል የእለተ ሰንበት መስዋዕተ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት በጸበል በመረጨት ወይም ደግሞ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ምሽት ላይ በሚደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ቀደም ብሎ በጸበል መርጨት ስነ-ስረዓት የጥምቀታችንን እለት በድጋሚ እናስታውሳለን። እንዲያውም ምስጢረ ጥምቀትን በምንሳተፍበት ወቅት የተጠመቁ ክርስትያኖች ልብ ውስጥ አንድ መንፈሳዊ የሆነ ኃይል እንዲነሳ ያደርጋል፡ ይህም በቤተ ክርስትያን አማክይነት ከክርስቶስ ጋር ያለንን ሕብረት አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪ ያቀርብልናል። ወደ ክርስትና ሕይወት ሥር መሰረት እንድንመለስ በማድረግ ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበልነበት ወቅት የተቀበላናቸውን ጸጋዎች በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ በማድረግ እና የተቀበልነውን ኃላፊነት በድጋሚ በማደስ ከተሰጠን ኃላፊነት ጋር የተመጣጠነ ሕይወት መኖር እንዳለብን ያስገነዝበናል። በተለይም ደግሞ በእዚህ የምስጢረ ጥምቀት አሰጣጥ ስነ-ስረዓት ወቅት በቅድሚያ የተጠማቂው ሰው ስም ይጠየቃል፣ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ስም የአንድ ሰው መለያ መጠሪያ በመሆኑ የተነሳ ነው። በእዚህም መሰረት ተጠማቂውን ወደ አጥማቂው በምናቀርብበት ወቅት በቶሎ የክርስትና ስሙን እንናገራለን፣ ይህም በቶሎ መጠሪ እንድናገኝ ያደርገናል ማለት ነው። ያለ ስም ሰው ሊያውቀን አይችልም፣ መብት ሊኖረን አይችልም፣ ግዴታም ሊኖረን አይችልም። እግዚኣብሔር እያንዳንዳችን የሚጠራው በስማችን ነው፣ እያንዳንዳችንንም ይወደናል፣ ካለን የሕይወት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሳይቀር እያንዳንዳችንን የወደናል። ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና ጥሪያችንን በግልሰብ ደረጃ እንድንመልስ ያነሳሳናል። በእርግጥ የክርስትያን ሕይወት በተከታታይ ጥሪዎች እና መልሶች የተሳሰረ ነው። እግዚኣብሔር ከአለፉት አመታት ጀምሮ ስማችንን በተከታታይ መጥራቱን ቀጥሉዋል፣ በተለያዩ ከሺ በላይ በሚሆኑ መነገዶች የእርሱ ልጅ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመስል ይጠራናል። ስለእዚህም የክርስትና ስም በጣም አስፈላጊ ነው ማለት ነው። ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጡትን የመጠሪያ ስም የሚያወጡት ሕጻኑ ከመወለዱ በፊት ሲሆን በእዚህም መልኩ የልጅነት መጠሪያ ስም በማግኘት በእዚህ ስም አማክይነት የእዚህ ሕጻን መሰረታዊ ማንነት እንዲታወቅና በክርስትና ሕይወት ከእግዚኣብሔር ጋር የተሳሰረ እንዲሆን ያደርጋል። ክርስትያን መሆን ማለት ከላይ የሚሰጠን ትልቅ ጸጋ ነው። እምነት ሊሸመት የሚችል ጉዳይ ሳይሆን፣ ነገር ግን የእኛን አዎንታ የሚጠይቅ እና አዎንታዊ ምላሽ የሚያስገኝ ነው። በእርግጥ “ምስጢረ ጥምቀት የሰው ልጆች በመነፈስ ቅዱስ ጸጋ አማክይነት ተነሳስተው ለክርስቶስ ወንጌል ምላሽ የሚሰጡበት ምስጢር ነው። አንድ እውነተኛ የሆነ እምነት ለማነሳሳት እና ለመቀስቀስ በእዚህም ተግባር ለቅዱስ ወንጌል ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ይህ የምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስረዓት ከመካሄዱ በፊት ተጠማቂው እና የተጠማቂው ቤተሰብ ቅዱስ ወንጌልን በሚገባ ያድምጡ ዘንድ በቂ የሆነ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይደረጋል። ምስጢረ ጥምቀትን የሚቀበለው ሰው ራሱን በሚገባ የሚያውቅ ጎልማሳ የሆነ ሰው ከሆነ ይህንን የቤተ ክርስትያን ጸጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን በራሳቸው አንደበት ሊገልጹ ይችላሉ፣ ነገር ግን ምስጢረ ጥምቀት የሚቀበለው ሰው ሕጻን የሆነ እንደ ሆነ በቤተሰቡ ይወከላል፣ ቤተሰቡ/የክርስትና አባት ወይም እናት በሕጻኑ ስም ሆነው ምላሽ ይሰጣሉ ።ከእነርሱ ጋር የሚደርገው ይህ ውይይት ሕጻኑ ይህንን ምስጢር ለመቀበል መፈለጉን በመጠየቅ ቤተ ክርስትያንም በእዚህ ረገድ ይህንን ምስጥር ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑዋን ለማሳየት ነው። “ይህም ፍቀደኝነት የሚገለጸው በሕጻኑ ግንባር ላይ አጥማቂው እና የሕጻኑ ቤተሰቦች በምያደርጉት የመስቀል ምልክት ይገለጻል”። “በአከባበሩ መግቢያ ላይ የሚደርገው የመስቀል ምልክት የክርስቶስን አሻራ የእርሱ ሊሆን በተዘጋጀው ሰው ላይ የሚያትምና ክርስቶስ በመስቀሉ ያስገኘልንን የደኅንነት ጸጋ ያሳያል’ (የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 1235)። መስቀል ማን እንደሆንን ምን እንደ ምናወራ፣ ምን እንደ ምናስብ፣ ምን እንደ ምንመለከት፣ በመስቀል ምልክት ሥር ሆነን ተግባራችንን እንድናከናውን በአጠቃላይ እስከመጨረሻው ጊዜ ድረስ በክርስቶስ ፍቅር ውስጥ ሆነን እንድንኖር የሚያደርገን የመለያ ምልክታችን ነው። ሕጻናት በሚጠመቁበት ወቅት ይህ የመስቀል ምልክት የሚደርግላቸው በግንባራቸው ላይ ነው። የጎለመሱ ሰዎች በሚተመቁበት ወቅት ይህ የመስቀል ምልክት በተመሳሳይ መልኩ የሚደርገው ከግንብራቸው ጀምሮ በስሜት ሕዋሳቶቻቸው ላይ ሲሆን ይህም “የጌታን ድምፅ ለመስማት ያስችልህ ዘንድ ይህንን ምልክት ጆሮህ ላይ ተቀበል፣ ለእግዚኣብሔር ቃል በቂ ምላሽ ለመስጠት ያስችልህ ዘንድ ይህንን የመስቀል ምልክት በአፍህ ላይ ተቀበል፣ ክርስቶስ በእዚህ እምነት አማክይነት በልብ ውስጥ እንዲገባ ይህንን የመስቀል ምልክት በደረትህ ላይ ተቀበል፣ የክርስቶስን ቀንበር ለመሸከም ያስችልህ ዘንድ ይህንን የመስቀል ምልክት በትክሻህ ለይ ተቀበል” በማለት በቃላት የታጀበ የመሰቀል ምልክት ይደርግለታል። በእዚህም መሰረት የጠመቅን ሁላችን ክርስትያኖች በመሆን የፋሲካው ምስጢር ምልክት የሆነው በሰውነታችን ላይ ያታተማል፣ ይህንንም በሚታይ መልኩ በምስክርነት በመግለጽ በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙንን ፈተናዎች በሙሉ ክርስትያናዊ በሆነ መንገድ እንድንወጣ ያግዘናል ማለት ነው። ከእንቅፋችን ስንነሳ፣ ከምግብ በፊት፣ በጣም አስደንጋጭ የሆነ ሁኔታ በሚገጥመን ወቅት፣ ክፉ መንፈስ በሚገጥመን ወቅት፣ ማታ ከመተኛታችን በፊት የመስቀል ምልክት የምናደርግ ከሆንን ይህ ለእኛ ለራሳችን እና ለሚያዩን ሰዎች ሁሉ የክርስቶስ መሆናችንን፣ ወይም የክርስቶስ ለመሆን እንደ ምንፈልግ የሚያሳይ ምልክት ነው። ቤተ ክርስትያን እና ቤታችንም ሳይቀ በምንገባበት ወቅት፣ በትንሽዬ ጎድጓዳ ሰዓን ላይ ጸበል በማድረግ በእዚህም መልኩ ወደ ቤት ይሁን ወደ ቤተ ክርስትያን በምንገባበት እና በምንወጣበት ወቅት ሁሉ ይህን ጸበል በመንካት የመስቀል ምልክት በምናደርገበት ወቅት ምስጢረ ጥምቀት መቀበላችንን ሁል ጊዜ እንድናስታውስ ያደርገናል።”

18 April 2018, 09:57