“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” “GAUDETE ET EXSULTATE” በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፈ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” “GAUDETE ET EXSULTATE” በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፈ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን 

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” “GAUDETE ET EXSULTATE”

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በአሁኑ ዓለማችን ውስት የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቅድስና መንገድ እንዲመለሱ የሚጋብዝ ጥሪ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፈ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” “GAUDETE ET EXSULTATE” 

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፈ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን

በአሁኑ ዓለማችን ውስት የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቅድስና መንገድ እንዲመለሱ የሚጋብዝ ጥሪ

መግቢያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአምስት አመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን ሦስት ሐዋሪያው ቃለ ምዕዳኖችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእዚህ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሕዳር 24/2013 ዓ.ም.  Evagelii  Gaudium አቫንጄሊ ጋውዲዩም በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም በወንጌል የሚገኝ ደስታ የሚል ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ይፋ በማድረግ አሁን በሚገኘው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ በቅዱስ ወንጌልን እንዴት መስብከ እንደ ሚገባ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የሚገኙትን ክርስትያናዊ እሴቶችን በሕይወታችን ለመኖር በምንጥርበት ወቅት ለናገኘው የምንችለውን እውነተኛ ደስታ በዝርዝር የሚገልጽ ሐዋሪያዊ ቃለ ሞዳን ነው።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም. በላቲን ቋንቋ Amoris Laetitia አሞሪስ ላይቲሲያ በአማሪኛው የፍቅር ሐሴት በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት እና በቤተሰብ ዙሪያ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጥሩትን የተለያየ ዓይነት ተግዳሮቶችን እንዴት መፍታት እንደአለባቸው የሚያመልክተው ቃለ ምዕዳን በቀዳሚነት የሚገልጽ ሲሆን፣ ከእዚያም በመቀጠል በላቲን ቋንቋ በሦስተኛ ደረጃ የሚገኘው ደግሞ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም ለንባብ የበቃው በላቲን ቋንቋ Gaudete ed Exultate በአማሪኛው “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ደግሞ ሦስተኛው ሐዋሪያዊ ቃለ ሞዳን ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት የተጻፈ አንድ ቃለ ምዳን በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ማብቃታቸው ተገለጸ። ይህ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን የመጥሪያ አርእስቱን ያገኘው በማቴዎስ ወንጌል 5፡12 ላይ በተጠቀሰው “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” ከሚለው የወንጌል ክፍል የተወስደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የሚያቅርብ ቃል ምዕዳን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በሚል አርእስት ቅዱስነታቸው በዛሬው ቀን በይፋ ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በአምስት ምዕራፎች እና 177 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ቃለ ምዕዳን እንደ ሆነም ለመረዳት ትችሉዋል።

ኢየሱስ በእርሱ ምክንያት የሚስደዱ እና የሚዋረዱ ሰዎችን በሙሉ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በማለት የማበረታቻ ቃል ተናግሮዋቸው እንደ ነበረ፣ እግዚኣብሔር ሁሉም ነገሮቻችን ወደ እርሱ እንድንመልስ ጥሪ እንደ ሚያቀርብልን እና በአንጻሩም እርሱ ለእኛ እውነተኛ የሆነ ሕይወት እንደ ሚሰጠን የሚያወሳ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ሲሆን ትክክለኛውን ደስታ የሚሰጠን እግዚኣብሔር ብቻ እንደ ሆነም በስፊው የሚያትት ቃለ ምዕዳን ነው። የቅድስና ሕይወት እንድንንሮ መጠራታችንን የሚገልጹ መልእክቶች እና ጥሪዎች ከመጽሐፍ ቅዱሳችን የመጀመሪያው ገጽ አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ በስፊው መጥቀሱን የሚያትተው ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ’ የተሰኘው የቅድስነታቸው ቃለ ምዕዳን ይህም እግዚኣብሔር ራሱ ለአብርሃም ተገልጦለት እንደ ነበረ እና  “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ” በማለት እንደ ሚጀምር ያትታል።

ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በሚል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በዛሬው እለት በይፋ ለንባብ የበቃው ቃለ ምዕዳን አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ ከማድረጉ ባሻገር ወደ ቅድስና ሕይወት ለመመለስ የሚያስችሉ መንገዶችን በመጠቆም በእነሩሱ ላይ ማብራሪያ የሚሰጥ ቃለ ምዕዳን ሲሆን የተለያዩ ዓይነት የቅድስና መንገዶችን በመጠቆም በተለይም ደግሞ አሁን ባለንበት በእኛ ዘመን እግዚኣብሔር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና” በማለት ለሚይቀርብልን ጥሪ በቂ የሆነ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉንን መንገዶች የሚያመላክት ቃለ ምዕዳን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ” በሚል አርእስት በቅዱስነታቸው ተጽፎ በዛሬው እለት በይፋ ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ቀድም ሲል እንደ ገለጽነው በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለ እና 177 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ነው።

በምዕራፍ አንድ እግዚኣብሔር በአሁን ወቅት ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እግዚኣብሔር ለእነርሱ ስላቀረበው የቅድሳና ጥሪ ያመለክታል። በምዕራፍ ሁለት ላይ ደግሞ ሁለት ቀንደኛ የቅድስና ጠላቶችን ያትታል። በምዕራፍ 3  በጌታ ብርሃን እይታ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ተቀምጡዋል፣ በምዕራፍ 4 ላይ ደግሞ በዛሬው ዓለማችን ውስጥ የሚታዩ የቅድስና ምልክቶች የሚል አርእስት የተሰጠው ሲሆን በአምስተኛው እና በመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ መንፈሳዊ ውጊይ ማድረግ፣ ነቅቶ መጥበቅ ኣና በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ይዞ ቀርቡዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ ለንባብ በይፋ የቀረበው በላቲን ቋንቋ GAUDETE ET EXSULTATE “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን  ከላይ ለመጥቀስ እንደ ተሞከረው በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮችን በመዳሰስ አሁን በምንገኝበት ዘመናዊ ዓለማችን የሚገኙ የሰው ልጆችን ወደ ቅድስና ሕይወት የሚጋብዝ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው። ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ከዛሬው እለት ጀምሮ በተከታታይ “ደስ የበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ ለንባብ የበቃውን ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ጥቅላላ ይዘት በተከታታይ ወደ እናንት የምናቅርብ መሆኑ ከወዲሁ እንገልጻለን አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ”

“ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን አጠቃላይ ይዘቱን ስንመለከት በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሙሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የሚያቀርብ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

አንተ ወይም አንቺ በኑሮህ ወይም በኑሮሽ ደስተኛ ያልሆንሽ ወይም ያልሆንክ ሰው ከሆንክ እነሆ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትፍራንቸስኮ “ደስ የባላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት የጽፉት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ተገቢውን ምላሽ ይሰጥሃል/የስጥሻል።

በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ዓለማችን ውስጥ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የምትገኙ፣ የተለያዩ የሕይወት ተግዳሮቶች እየገጠሙዋችሁ የምትገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እንዲሁም አሁን ባለው ዓለማችን ውስጥ ያለውን መልካም እድል መጠቀም ያልቻላችሁ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ልጆቻችሁን በታላቅ ፍቅር ተንከባክባችሁ እያስደጋችሁ የምትገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ለቤተሰባችሁ የሚሆን እንጀራ በእየለቱ ለማግኘት የምትኳትኑ፣ የምትለፉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ የምትሰሩ የማኅበረስብ ክፍሎች፣ እድሜያችሁ ዘመኑ ሁሉ ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ ለሀገራችሁ፣ በአጠቃልይ ለማኅበረሰቡ መልካም የሆነ ተግባር ያከናወናችሁ አረጋዊያን ሁላችሁ ይህ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በሚያዚያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ሁላችሁንም ወደ ቅድስና ሕይወት በመጋበዝ ደስተኛ የሆነ ሕይወት መኖር የምያስችላችሁን ሐሳቦች በስፊው ይተነትናል፣ ምክንያቱም ሁላችንም በፈጣሪያችን ቅዱስ የሆነ ሕይወት እንድንኖር ተጠርተናልና።

ለእናንተ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት፣ ለቄስውስት እና ለዲያቆናት፣ እንዲሁም የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በሙሉ ይህ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት የተጻፈው ቃለ ምዕዳን እንንተም ወደ ቅድስና መንገድ የሚደርገውን ጉዞ በደስታ እንድትጓዙ ጥሪ የሚያቀርብላችሁ እና ደስተኝ ኣለምሆን የምያስችላችሁን መንገዶች የሚጠቁማችሁ ቃለ ምዕዳን ነው።

ለእናንተ ምሁራን፣ አዋቂዎች እና ተመራማሪዎች እናንተ ብዙ ነገሮችን የምታውቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ብዙ ያወቀ ሰው ብዙ የጠበቅበታልና ባላችሁው እውቀት እና ክህሎት ታግዛችሁ ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን ዓለማችንን ደስተኝ የሆነ ማኅበረሰብ የሚኖርባት ዓለም በማደርግ የሰው ልጆች የተሰጣቸውን ሰብዕዊ ክብር በመጠቀም ደስተኛ እና ፍትሃዊ የሆነ የማኅበረሰብ ክፍል እንድትፈጥሩና ግብረገባዊ ያልሆነ እና በፍቅር ያልታጀበ እውቀት ከንቱ በመሆኑ የተነሳ በፍቅር እና በግብረገብ የታጀበ እውቀት አስፈላጊ እንደ ሆነ ጥሪ የሚያቀርብላችሁ እና መንገዶችን በማመልከት በእግዚኣብሔር ጸጋ የታጀበ እውቀት ወደ ቅድስና መንገድ እንድታመሩ የሚያግዝ መሆኑን በመጥቀስ መንገዶችን የሚጠቁም ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

ይህ “ደስ የበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት በሚያዚያ 01/2010 ዓ.ም በይፋ ለንባብ የበቃው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ከላይ ለመጥቀስ እንደ ሞክርነው መላው የዓለማችን ሕዝቦች በድስተታ የተሞላ ሕይወት ይኖራቸው ዘድን ከእዚያም በመቀጠል የቅድስና ሕይወትን ለመኖር ይሞክሩ ዘንድ ጥሪ በማቅረብ ይህንን የቅድስና መንገድ ለመከተል ለሚፈልግ የሰው ልጅ ሁሉ መነገዱን ክርስትሶስ እንደ ሚያሳየው እና መንገዱም ኢየሱስ ብቻ መሆኑን በስፊው የሚገልጽ ሲሆን በዛሬው ዓለማችን ውስጥ  እርሱን ኢየሱስን ማለት ነው መከተል ማለት አሁን ካለው የዓለማችን በሰፊው እየተነጸባረቀ ከሚገኘው ገንቢ ያልሆነ ሐሰተሳብ በተቃራኒው መጓዝ ማለት በመሆኑ የተነሳ በእዚህ ዓለም ውስጥ በአሁን ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እይተከሰቱ የሚገኙትን መከራዎች እና ፍትሃዊ ያልሆኑ ተግባርትን ከእነርሱ መሸሽ ማለት ሳይሆን በከፍተኛ ብርታት እነዚህን ነገሮች ሰላምዊ በሆነ መልኩ መዋጋት፣ ትሁት መሆን እና የርኅራኄን መንፈስ በመላበስ ወደ ቅድስና መንገድ ያለምንም ፍርሃት መጓዝ እንደ ሚገባ የሚገልጽ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

 

09 April 2018, 09:40