ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይወት መሰረት ነው”

የሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አሰተምህሮ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ እንዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለምሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው ከጥር 7/2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 26/2010 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር ረቡዕ እለት በስርዓተ ቅዳሴ ዙሪያ በተከታታይ አድርገውት የነበረው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባለፈው ሳምንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ያደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የተገጸ ስሆን “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዜና አጠናቃሪ--መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!”

“ወደ ፋሲካ በዓል እንድናመራ ያደረገው ስረዓተ አምልኮ ከተጀመረበት እነሆ ዛሬ በ50ኛው ቀን ላይ በተፈጥሮው ከክርስቶስ ራሱ በመነጨው የክርስትያን ሕይወት ዙሪይ ላይ አስተንትኖ ለማድረግ እወዳለሁ። በእርግጥ እኛ ሙሉ ክርስትያኖች ነን ለማለት የምንችለው ክርስቶስን በውስጣችን ባስገባነው መጠን ነው። ስለዚህ እዚህ ግንዛቤ ላይ ከመጀመሪያው ለመድረስ እንዲረዳን ከመጀመሪያ አንስቶ በክርስትና ሕይወት ውስጥ እንድንገባ ምክንያት የሆነንን ምስጢር የተኛው ነው? ይህ ምስጢር ምስጢረ ጥምቀት ነው። የክርስቶስን የፋሲካ በዓል በአዲስ መልክ በምስጢረ ጥምቀት አማክይነት ወደ ክርስቶስ አምሳል እንድንለወጥ በማድረግ፡ የተጠመቁ ክርስቲያኖች በሙሉ የክርስቶስ እንዲሆኑ በማድረግ እርሱ የሕይወታቸው ሕልውና እንዲሆን አድረገዋል። ምስጢረ ጥምቀት “የክርስቲያን ሕይወት መሠረት ነው” (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 1213)። የምስጢራት ሁሉ መጀመሪያ በመሆን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እኛ ውስጥ በመግባት በውስጣችን የምያድርበት እና በእርሱ ምስጢር ውስጥ እንድነገባ የሚያደርገን የመግቢያ በር ነው። ጥምቀት የሚለው ግስ በግሪክ ቋንቋ “ጠለቀ” የሚለውን ትርጓሜ ያሰማል። በውሃ የመታጠበ ስነ-ስረዓት በብዙ በተለያዩ እምነቶች ውስጥ የሚንጸባረቅ የጋራ ሐይማኖታዊ ስነ-ስረዓት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህም ከአንድ ነባራዊ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ መሸጋገርን የምያመለክት ሁኔታ ነው። በእዚህም መልኩ አንድ አዲስ ሕይወት ከመጀመሩ በፊት የሚፈጸም የመንጻት ምልክት ተድርጎ ይቆጠራል። ነገር ግን ሰውነታችን በውሃ ውስጥ በሚጠልቅበት ወቅት ነብሳችን በክርስቶስ ውስጥ በመጥለቅ የኃጢአት ስርዬት በመቀበል መለኮታዊ የሆነ ብርሀን እንደ ምታበራ እኛ ክርስቲያኖች በፍጹም መዘንጋት የሌለብን ጉዳይ ነው። በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ምስጢረ ጥምቀት በሰራነው ኃጢኣት ምክንያት ከእግዚኣብሔር ለያይቶን የነበረውን አሮጌውን ማንነታችንን በመቅበር በጌታ ሞትና ትንሳኤ ውስጥ እንድንጠልቅ በማድረግ በኢየሱስ አማክይነት እንደገና የተፈጠርን አዲስ ሰዎች እንድንሆን ያደርገናል። በእርሱ አማክይነት የአዳም ልጆች በሙሉ ወደ አዲስ ህይወት ተጠርተዋል። ስለእዚህ ጥምቀት ማለት ዳግም መወለድ ማለት ነው። እርግጠኛ ነኝ፣ ሁላችንም የእኛን የልደት ቀን በሚገባ እንስታውሳለን ብዬ አስባለሁ፣ እርግጠኛ ነኝ! እኔ ግን ትንሽዬ ጥርጣሬ ቢኖረኝም እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡ ‘እያንዳንዳችሁ መቼ እንደ ተጠመቃችሁ ታስታውሳላችሁ ወይ?’ . . . አንዳንዶቻችሁ አዎን እናውቃለን ብላችኃል፣ ይህም በጣም ጥሩ የሆነ ነገር ነው። ነገር ግን አዎን እናስታውሳለን ያሉ ሰዎች ድምጽ ግን ብዙ አይደለም፣ ይህም ብዙዎቻችሁ መቼ እንደ ተጠመቃችሁ እንደ ማታስታውሱ ያመለክታል። የልደት ቀናችንን የምናከብር ከሆንን ታዲያ ለምንድነው ዳግም የተወለድንበትን ቀን ባናክብረውም ብያንስ ብያንስ የማናስታውሰው ለምንድነው? ዛሬ ወደ ቤታችሁ ስትመለሱ ዛሬውኑ አንድ የቤት ሥራ ልሰጣችሁ እፈልጋለሁ። ከእናንተ መካከል የተጠመቀበትን ቀን የማያውቅ ሰው ካለ ወደ ቤታችሁ ስትመለሱ እናቶቻችሁን፣ አክስቶቻችሁን፣ ወይም ደግሞ የእህት የወንድም ልጆቻችሁን “መቼ እንደ ተጠመኩኝ ታውቃለህ/ታውቅያለሽ? በማለት ጠይቁ፣ እባካችሁን በፍጹም እንዳትረሱ እሺ። የተጠመቅንበትን ቀን በማስታወስ በእዚያ ቀን እግዚኣብሔርን ማመስገን ይገባናል ምክንያቱም ኢየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን የገቡበት ትክክለኛው ቀን በመሆኑ የተነሳ ነው። ወደ ቤት ስትመለሱ የምትሰሩትን የቤተ ሥራ በሚገባ ታስታውሳላችሁ አይደል? አዎን ሁላችንም የተጠመቅነበትን ቀን በሚገባ ማስታወስ ይኖርብናል። የጥምቀታችን ቀን የተወለድንበት ቀን ነው፣ ዳግም የተወልድንበት ቀን። እባካችሁን አሁንም በድጋሜ ይህንን ቀን በፍጹም መርሳት የለባችሁም። የተጠመቃችሁበትን ቀን ዳግም የተወለዳችሁበት ቀን በመሆኑ የተነሳ እንደ ልደት ቀናችሁ ባታከብርትም እንኳን ማስታውሱን እባካችሁን በፍጹም እንዳትረሱ። ከሙታን የተነሳው ታላቁ ጌታ ለደቀ-መዛሙርቱ የተናገራቸውን የመጨረሻ ቃላቶች እናስታውስ፡ እንዲህም አላቸው “ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴ 28፡19-20) እነዚህ ቅላቶች በጣም አጭር እና ግልጽ የሆኑ ቅላት ናቸው። በጥምቀት እጥበት አማካይነት በክርስቶስ ያመነ አንድ ሰው በቅድስት ሥላሴ ሕይወት ውስጥ ጠልቆ የገባል። የጥምቀት ውሃ አንድ ተራ የሆነ ውሃ ሳይሆን ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የሚገለጥበት "ሕይወት የሚሰጥ" ውሃ ነው። ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ዳግም መወለድ ይገባሃል በማለት ማብራርያ በሰጠበት ወቅት የተናገራቸውን ቃላት እናስታውስ “ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደም መንፈስ ነው (ዩሐንስ 3፡5-6)። ለእዚህም ነው ጥምቀት “ዳግም ወልደት” ማለት ነው የምንለውም በእዚሁ ምክንያት ነው፡ “ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው” (ቲቶ 3፡5) እግዚኣብሔር እንዳዳነን እናምናለን። ስለዚህ ጥምቀት አዲስ ሕይወት ለመራመድ ዳግም የመወለድ ምልክት ነው። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ “ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንድንሆን የተጠመቅን፣ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ፣ እኛም እንዲሁ በአዲስ ሕይወት እንድንኖር በጥምቀት ሞተን ከእርሱ ጋር ተቀብረናል” (ሮም 6፡3-4) በማለት ያስታውሰናል። በምስጢረ ጥምቀት አማክይነት ከኃጢኣት ነጻ በመውጣት የእግዚኣብሔር ልጆች ሆነን እንደገና ተወልደናል፣ የክርስትሶ ልጆች ሆነናል፣ ወደ በተክርቲያን ተደምረናል (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ.1213)። እኛ የተጠመቅን ሰዎች ሁሉ ብኛ ሰዎች አይደለንም፣ የክርስቶስ የአካል ክፍሎች ነንና። ከምጢረ ጥምቀት መስጫ ስፍራ የሚመነጨው ዋነኛው እና መሰረታዊ ነገር “እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በእርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል (ዩሐንስ 15፡5) በማለት ኢየሱስ የተናግረው ንግግር እንደ ሆነ እንረዳለን። በተመሳሳይ መልኩም መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ አማክይነት ተጠመቀ ሰው ውስጥ በቅባ ቅዱስ አማክይነት በመግባት የክርስቶስ አንድ አካል እንዲሆን በማድረግ ለቅዱስ ቁርባን ምስጢር የተዘጋጀ እንዲሆን ያደርገዋል። ጥምቀት ክርስቶስ በውስጣችን እንዲኖር በማድረግ እኛም ከእርሱ ጋር ሕብረት እንዲኖረን በማድረግ ከቤተ ክርስቲያን ገር በመተባበረ፣ እያንዳንዱ ሰው እንደ አቅሙ ዓለምን በመለወጥ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን ያደርጋል። ምስጢረ ጥምቀት ከተቀበልን በኃላ ሕይወታችን በሙሉ በብርሃን የተሞላ ይሆናል፣ በጉዞዋችን እየመራን እስከ ሰማያዊቷ እየሩሳሌም በምናደርገው ጉዞ ከእኛ ግራ ይሆናል። በእዚህ ረገድ ምስጢረ ጥምቀት ሁለት ዓይነት ገጽታዎች አሉት። አንድ ሰው በእመንት ለመጠንከር አስቦ ወይም በሌላ ምክንያት ምስጢረ ጥምቀትን ከጎለመሰ በኃላ ሊቀበል ይችል ይሆናል። ይህም መልካም ነገር ነው። ነገር ግን ከጥንት ጊዜ ጀመሮ ሕጻናት በወላጆቻቸው እመንት የተነሳ ገና በልጅነታቸው ይጠመቁ ነበር። በእዚህ ላይ አንድ ነገር ለማለት እፈልጋለሁ። አንዳንድ ሰዎች “ምንም የማይገባውን አንድ ሕጻን ለምን ማጥመቅ አስፈልገ?” በማለት ጥያቄ ልያነሱ ይችሉ ይሆናል። ‘እርሱ (ሕጻኑ) እያደገ በመሄድ፣ ምስጢረ ጥምቀት ምን መሆኑን ከተረዳ በኃላ እርሱ ራሱ ይህንን ምስጢር መጠየቅ ይኖርበታል’ በማለት ያስቡ ይሆናል። ይህም ማለት በመንፈስ ቅዱስ አለመተማመን ማለት ነው፣ ምክንያቱም እኛ አንድ ሕጻን ስናጠምቅ መንፈስ ቅዱስ በእዚያ ሕፃን ውስጥ የገባል፣ እናም መንፈስ ቅዱስ በእዛ ሕጻኑ ውስጥ ከልጁ ጋር አብሮ ያድጋል፣ ከልጅነቱ ጀምሮ የክርስትናን መንፈስ በውስጥ በማሳደግ ልጁ በእዚህ መንፈስ ተሞልቶ እንዲያድግ ያደርገዋል። ይህን እድል ሁሉም ህፃናት፣ ሁሉም ልጆች እንዲያገኙ በማድረግ በህይወታቸው ዘመን በሙሉ የሚመራቸውን መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው እንዲኖራቸው ማድረግ ይኖርብናል። በእዚህም የተነሳ ልጆችን በሕጻንነታቸው ማስጠመቅ በፍጹም መርሳት የለብንም። ”

    

 

11 April 2018, 15:39