ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “ባልንጄራዎቻችንን መጉዳት እግዚኣብሔርን እንደ ማሳዘን ይቆጠራል”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 07/2010 ዓ.ም. “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” ከሚለው ጸሎት በፊት በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ “ ባልንጄራዎቻችንን መጉዳት እግዚኣብሔርን እንደ ማሳዘን ይቆጠራል” ማለታቸው ተገለጸ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳኤ በዓል ከተከበረ እነሆ ሦስተኛው ሳምንት ላይ እንደ ምንገኝ ይታወቃል። ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ሦስተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በታላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 07/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት ባልንጀራችንን መጉዳት እግዚኣብሔርን እንደ ማሳዘን ይቆጠራል ማለታቸው ተገለጸ። 

የእዚህ ዜና አቀናባሪ፡ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 07/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!”

“በእዚህ ሦስተኛው የፋሲካ ሰንበት ቀን የእርሱ የነበሩ ደቀ-መዛሙርት በሙሉ በአንድነት ተሰብስበው በነበረበት ወቅት ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ተገልጦላቸው እንደ ነበረ በመኣከልነት ተገልጾ ይገኛል። ይህም በተለይም ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ በመገለጥ እንደገና "ሰላም ለእናንተ ይሁን!" በማለት ሰላምታ አቅርቦላቸው እንደ ነበረ ቅዱስ ወንጌል ይመሰክራል። ሰላም ለእናንተ ይሁን በማለት ሰላምን የሚሰጠን ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ነው። ይህም ውስጣዊ የሆነ ሰላምን እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በምናደርገው ግንኙነት የምንመስርተው ዓይነት ሰላም ነው። ወንጌላዊው ሉቃስ ያቀረበው ምስክርነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ከሙታን መነሳቱን ያሳያል። ኢየሱስ በመንፈስ ብቻ አልነበረም የተገለጠው። በእርግጥ ይህ ታሪክ ኢየሱስ በመንፈስ ብቻ አለመገለጡን በማውሳት ሙሉ በሙሉ ከሙታን የተነሳው ከእውነተኛ አካሉ ጭምር እንደ ሆነ ያሳያል። ደቀ-መዛሙርቱ እርሱን ባዩ ወቅት ደንግጠው በፍርሀት መዋጣቸውን ኢየሱስ ተርድቶ የነበረ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት የትንሳሄውን ሁኔታ በወቅቱ እነርሱ ሊረዱት ያዳገታቸው እውነታ በመሆኑ የተነሳ ነው። እነርሱ ግን ደንግጠው በፍርሀት ተዋጡ፤ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ መንፈስ ብቻ አይደለም፣ በአካል እና በመንፈስ ነው የተገለጠው። ይህንን እንዲያምኑም ለማድረግ በማሰብ “እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ንኩኝና እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና ዐጥንት የለውምና” (ሉቃስ 24፡39) በማለት ያስረዳቸውም በእዚሁ ምክንያት የተነሳ ነው። ይህ ደግሞ ደቀ-መዛሙርቱን ለማሳመን በቂ አልነበረም። ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ደቀ-መዛሙርቱ ከመደሰታቸው እና ከመገረማቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው እንደ ነበረ በመጥቀስ አንድ የምያስገርም ነገር ይናገራል፣ “በፍጹ ሊሆን የማይችል ነገር ነው፣ በታላቅ ደስታ በፍጹም ይህ ነገር ሊሆን የማይችል ነገር ነው!” ይሉ ነበር። እነርሱም ይህንን እውነታ በይበልጥ እንዲረዱት ለማድረግ በማሰብ ኢየሱስ “በዚያ ቦታ አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው። እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራሽ ሰጡት፤ እርሱም ተቀብሎ በፊታቸው በላ (ሉቃስ 24፡41)። ይህንንም ያደርገው እንዲያምኑ ለማድረግ አስቦ ነበር። የእርሱ ትንሳኤ እውነታ አፅንዖት የሰጠው አካልን በተመለከተ ክርስቲያኖች ያላቸውን የአመለካከት ገጽታ የሚያነጸባርቅ ነው፣ አካል እንቅፋት ወይም ደግሞ ነብሳችን የምትቀመጥበት እስር ቤት አይደለም። አካላችን በእግዚኣብሔር በመፈጠሩ የተነሳ አንድ ሰው በአካል እና በነብስ በሁለቱም ሕብረት ካልተዋቀረ ሙሉ ሰው ነው ለማለት አንችልም። ሞትን ድል በማድረግ በአካል እና በነፍስ ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ስለ አካላችን አወንታዊ አስተሳሰብ ሊኖረን እንደሚገባን ያስገነዝበናል። አካላችን ኃጢያት እንድንሰራ አጋጣሚ የሚፈጥር ወይም መሳሪያ ሊሆን ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ኃጢአት በአካላችን ድክመት የተነሳ የሚከሰት ነገር ሳይሆን ነገር ግን ከእኛ ግብረ-ገብ ድክመት የመነጨ ነው። አካላችን ከነብሳችን ጋር ሕብረት በመፍጠር የእርሱን አርዕያ እና አምሳያን ለመግለጽ ከእግዚኣብሔር የተሰጠን ድቅ ስጦታ ነው። ስለዚህ እኛ የእኛንም ሆነ የሌሎችን ሰዎች አካል ታላቅ ክብር ልንሰጥ እና እንክብካቤ እንድናደርግ ተጠርተናል። በማንኛውም መንገድ በባልንጀራችን እና በራሳችን አካል ላይ የምናደርሰው ጉስቁልና፣ ቁስል ወይም ግፍ ፈጣሪ በሆነው በእግዚኣብሔር ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው። በዛሬው ቀን በተለየ ሁኔታ በአካላቸው ላይ በተለያየ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰባቸው የሚገኙ በተለይም ልጆች፣ ሴቶች እና በአረጋውያን ለማሰብ እፈልጋለሁ። በእነዚህ ሰዎች አካል ውስጥ እኛ የክርስቶስን አካል እናገኛለን። የቆሰለውን፣ የተፌዘበትን፣ የተዋረደውን የተገረፈውን እና የተሰቀለውን ክርስቶስን እናገኛለን። ኢየሱስ ፍቅርን አስተምሮናል። ይህም ፍቅር በእሩስ ትንሳሄ ከኃጢኣት እና ከሞት በላይ ኃይል ያለው መሆኑን በመግለጽ አሁን እኛ ባለንበት ዓለማችን ውስጥ በባርነት ቀነበር ስር ወድቀው አካላቸው እየተጎዳ ያሉትን ሰዎች በሙሉ ለማዳን ይፈልጋል። አቅመ ደካማ በሆኑት ሁሉ ላይ በተደጋጋሚ በኃያላኑ አማክይነት አሁን ባለንበት ዓለማችን እየተነሰራፋ ባለው ጭቆና እና መንፈሳችንን አንቆ በያዘው ለቁሳዊ ነገሮች ብቻ የምናሳየው ፍላጎት የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እነዚህን ነገሮች በጥልቀት እንድንመለከት እኛን በመጋበዝ በታላቅ አግራሞትና ደስታ ከሙታን የተነሳውን ክርቶስ እንድንገናኝ ይጋብዘናል። እርሱ በታሪክ ውስጥ በዘራቸው ወደ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር መጓዝ የሚያስችሉንን ነገሮች ብቻ መርምረን የምናውቅ ሰዎች እንድንሆን ይፈልጋል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእዚህ መነገድ ላይ በምናደርገውን ጉዞ እንድትረዳን እና በእናትነት አማላጅነቷ ከእኛ ጋር ትሆን ዘንድ በመተማመን እንማጸናለን። ”

15 April 2018, 15:24