ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት ነፍሰ ጡር ለሆኑ ሴቶች ጸሎት አደረጉ።

በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት በሚያዝያ 9/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ትኩረት ሰጥተው የጸለዮት በዚህ እርግጠኛ ባልሆንበት አደገኛ  ወቅት ላይ ነፍሰ ጡር ለሆኑ ሴቶች በእዚህ የእርግዝና ወቅት እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ጸሎት ያቀረቡ ሲሆን በእለቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት እውነተኛ የሆነ ማኅበራዊ እና ሰብዓዊ ግንኙነት የሌለበት በግለሰብ ደረጃ ብቻ የሚመሰረት ምናባዊ የሆነ መንፈሳዊነት በእምነት ላይ ስጋት እንደ ሚፈጥር የገለጹ ሲሆን ይህም የሚሆንበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በተፈጥረው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕዙቡ ቅዱሳት ምስጢራትን ቤተክርስቲያን ድረስ ሂደው ለመቀበል ባለመቻላቸው እና ማነኛውንም መንፈሳዊ አግልግሎት በየቤታቸው ሆነው በማሕበራዊ የመገናኛ አውታሮች አማካይነት ምናባዊ በሆነ መልኩ ብቻ ለመከታተል በመገደዳቸው እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደርጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ የጀመሩት በአሁኑ ወቅት ነፍሰ ጡር የሆኑ ሴቶችን በጸሎት በማስታወስ እንዲህም በማለት ነበር -

ዛሬ ነፍሰ ጡር ለሆኑ ሴቶች እና  በማህጸን ውስጥ የሚገኙ ጨቅላ ልጆቻቸው እስኪወለዱ ድረስ በጭንቀት በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ እናቶች ለመጸለይ እፈልጋለሁ። “ልጄ በምን ዓይነት ዓለም ውስጥ ነው ሊኖር የሚችለው?” በማለት ጥያቄ ሊያነሱ ይችሉ ይሆናል። ጌታ በእርግጥ እነዚህ ሴቶች በእርሱ በመተማመን እነዚህን ልጆች ለማሳደግ የሚያስችል ድፍረት ይሰጣቸው ዘንድ እኛ እንጸልይላቸው፣ በጪው ጊዜ ሁል ጊዜም ጌታ በጣም የሚወድው ዓለም ይሆናል።

በዕለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የተወሰደው ከዮሐንስ ወንጌል 21፡1-14 ላይ የተጠቀሰው ሲሆን ከሙታን የተነሳው ጌታ  ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር ዓሣ በማጥመድ ላይ ለነበሩ ደቀ መዝሙርት እንደ ገና መገለጹን የሚገልጽ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ነበር። እንዲህም ይላል “ሲነጋም ኢየሱስ በባሕሩ ዳርቻ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም ነበር። እርሱም “ልጆች፣ ዓሣ አላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “የለንም” አሉት እርሱም፣ “መረባችሁን ከጀልባው በስተ ቀኝ ጣሉ፤ ዓሣ ታገኛላችሁ” አላቸው። እነርሱም በጣሉ ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ መረቡን መጐተት አቃታቸው። ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙርም፣ ጴጥሮስን፣ “ጌታ እኮ ነው!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም፣ ‘ጌታ እኮ ነው!’ የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ አውልቆት የነበረውን መደረቢያ ልብስ ታጠቀና ዘሎ ወደ ባሕሩ ገባ” በማለት በሚተርከው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ ነበር። 

 ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእዚህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት ስብከት ደቀ መዛሙርቱ መረባቸውን እንደገና እንዲጥሉ በጌታ ሲጋብዙ መረቦቻቸው በዓሳ እንደ ተሞሉ የገለጹ ሲሆን ይህ ተአምር የተፈጸመው ደቀ መዛሙርቱ ከእዚህ ቀድም ዓሳ የማጥመድ ልምድ ስለነበራቸው እነርሱ በለመዱት መልኩ እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን ምክንያቱም ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር የተዋወቁት ዓሳ በማጥመድ ላይ በነበሩበት ወቅት እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። እኛም ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ሕይወታችን ማደግ የሚገባን የግል ማንነታችን ብቻ ይዘን ሳይሆን ነገር ግን የሚታወቀውን የጋራ ማንነታችንን ይዘን ልናድግ ይገባል ብለዋል። ያለ ማህበረሰብ ፣ ያለ ቤተክርስትያን ፣ ያለ ቅዱስ ቁርባን ክርስትያናዊ የሆነ እውቃና ለማግኘት መሞከር አደገኛ ነው ፣ ግለሰባዊ የሆነ መንፈሳዊነት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ሊለየን ይችላል። በእዚህ ወረርሽኝ የተነሳ አሁን እያስተዋልን እንደ ምንገኘው እርስ በእርሳችን የምንገናኘው፣ አሁን ይህንን መስዋዕተ ቅዳሴ በመከታተል ላይ እንደ ምተገኙት ዓይነት ማለት ነው፣ የምንገናኘው ምናባዊ በሆነ መልኩ በመገናኛ ብዙሃን አውታሮች አማካይነት ነው ብለዋል። ምዕመናን የስርዓተ አምልኮ ስነ-ስረዓቶችን በአካል ተገኝተው መከታተል ባለመቻላቸው የተነሳ በመንፈስ ብቻ ሕብረት እንዲፈጥሩ መገደዳቸውን በስብከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህ ሁኔታ ደግሞ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል። አንድ ላይ ተሰባስበን ለመቀጠል ከዚህ ሸለቆ መውጣት አለብን ምክንያቱም በእዚህ ዓይነት መልኩ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች አማካይነት ምናባዊ በሆነ መልኩ የሚደረጉ ግንኙነቶች እውነተኛውን ቤተክርስትያን ሊወክሉ አይችሉም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ሲሆን ጌታ ይህንን ተጨባጭ በሆነ መልኩ እንዲያስተምረን፣ ከእርሱ ጋር ያለን ቁርኝት እና ቅርበት ምን ያህል አስፈላጊ እንደ ሆነ እንድንረዳ እንዲያግዘን፣ በቤተክርስትያን ውስጥ ከምሰጡ ቅዱሳን ምስጢራት እና ከቅዱሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መገናኘት አስፈላጊ መሆኑን ጌታ እንዲያስተምረን ልንጠይቀው የገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉት ስብከት ከሞላ ጎደል የምከተለውን ጭብጥ የያዘ ነበር. . .

ደቀ መዛሙርቱ ዓሣ አጥማጆች ነበሩ -ኢየሱስ እነርሱን የጠራቸው ዓሳ በማጥመድ ላይ በነበሩበት ወቅት ነበር፣ ጴጥሮስ እና እንድሪያስ የዓሳ ማጥመጃ መረቦቻቸውን ሲያበጃጁ ነበር ኢየሱስ የጠራቸው። መረባቸውን ትተው ኢየሱስን ተከትለው ነበር፣ ዮሐንስ እና ያዕቆብ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ አባታቸውን እና ከእነርሱ ጋር ሲሰሩ የነበሩትን ወጣቶች ትተው ኢየሱስን ተከትለው ነበር፡፡ ኢየሱስ ሲጠራቸው እለታዊ የሆነ የዓሳ የማጥመድ ሥራቸውን በማከናወን ላይ ነበሩ። የዛሬው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ውስጥ የተጠቀሰው ይህ ተዓምር፣  በተዓምራዊ መንገድ ዓሣ አጥምደው ብዙ ዓሳ መያዛቸውን የሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት ወስጥ የተጠቀሰውን በተአምራዊ መንገድ ዓሳ አጥምደው እንዳገኙ የምገልጸውን ታሪክ እንድናስብ ያደርገናል፣ እዚያም ተመሳሳይ ነገር ተፈጥሯል። ምንም ዓይነት ዓሳ እናገኛለን ብለው ተስፋ ባላደረጉበት ወቅት እጅግ በጣም ብዙ ዓሳ ለመያዝ ቻሉ። ኢየሱስ የስምዖን ጀልባ ላይ ሆኖ ሕዝቡን አስተምህሮ ከጨረሸ በኋላ “ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በሉና ዓሣ ለመያዝ መረባችሁን ጣሉ” አለው። ስምዖንም መልሶ፣ “መምህር ሆይ፤ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም” አለው። ከእዚያም በመቀጠል “አንተ ካልህ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው፣ መረቡንም ጣለ።

 ቅዱስ ወንጌል እንደ ምነግረን እጅግ በጣም ብዙ ዓሳ ለመያዝ ቻሉ፣ በእዚህ ተአምር የተነሳ “እጅግ በጣም ተደነቁ”። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ዮሐንስ 21፡ 1-14) የተጠቀሰውና በተመሳሳይ መንገድ ዓሣ ማጥመዳቸውን በምገልጸው ታሪክ ውስጥ “እጅግ በጣም ተደነቁ” የምለው ዐረፍተ ነገር አልተገለጸም። አንድ የተወሰነ ተፈጥሮአዊ ነገር እንደ ተከሰተ ለማየት እንችላለን፣ እነርሱ ማለትም ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ባላቸው ቅርበት የተነሳ ስለጌታ ያላቸው ግንዛቤ እና እውቀት እያደገ እና እየጨመረ መሄዱን እንመለከታለን፣ ይህንን በሌላ መልኩ ስንገልጽ እነርሱ ከጌታ ጋር የነበራቸው ትውውቅ ወይም መግባባት እየጨመረ መሄዱን እናያለን። ሐዋርያው ዮሐንስ ይንን ተአምር ካየ ነኋላ “ጌታ እኮ ነው!” አለ፣ ስምዖን ጴጥሮስም፣ ‘ጌታ እኮ ነው!’ የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ አውልቆት የነበረውን መደረቢያ ልብስ ታጠቀና ዘሎ ወደ ባሕሩ ገባ። ከእዚህ ቀደም በነበረው ሂደት ግን በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት ላይ እንደ ተጠቀሰው በተአምር ዓሳ ከያዙ በኋላ ጴጥሮስ በኢየሱስ ፊት ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ  እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ አርቅ” (ሉቃስ 5፡8) በማለት ተናግሮት ነበር።  አሁን ግን ምንም አላለም ነበር፣ ምክንያቱም የበለጠ ተቀራርበው ስለነበረ ነው። ማንም ሰው “አንተ ማነህ?” ብሎ ጥያቄ ልያነሳ አልደፈረም ነበር፣ ምክንያቱም ሁሉም ጌታ መሆኑን አውቀው ስለነበረ ነው። ሐዋርያቱ ከጌታ ጋር የነበራቸው ቅርርብ ጨምሮ ነበር።

እኛ ክርስትያኖች በሕይወት ጉዞ ውስጥ በእዚሁ መልኩ ልንጓዝ የሚገባን ሲሆን ከጌታ ጋር ያለን ቅርበት እና የምንፈጥረው ዝምድና እየጨመረ ሊሄድ ይገባዋል። ጌታ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ይጓዛል፣ ምክንያቱም ከእኛ ጋር ስለሚሄድ እርሱ እንደ ሆነ እናውቃለን፣ ማንም ሰው “አንተ ማነህ?” ብሎ ልጠይቀው የደፈረ የለም፣ ጌታ መሆኑን ያውቁ ነበር። ክርስትያኖች በእየለቱ ከእርሱ ጋር ያላቸው ቅርርብ እያደገ ልሄድ ይገባል፣ ይህ የክርስትያኖች መለያ ነው። ሐዋርያቱ በእርግጥ ከኢየሱስ ጋር የነበራቸው ቅርበት በመጨመሩ የተነሳ ዓሳ እና ዳቦ ተመግበው ቁርስ ከአርሱ ጋር በልተዋል፣ በእዚያም ብዙ ነገሮችን አንስተው እንደ ተነጋገሩ ግልጽ ነው።

ይህ ክርስትያኖች ከጌታ ጋር ያላቸው ቅርርብ ሁልጊዜም ቢሆን ግላዊ ሳይሆን ማሕበረሰባዊ ነው። አዎን ያለማኅበረሰብ፣ ያለ ቅዱስ ቁራን፣ ያለ ቤተክርስትያን፣ ያለ ሕዝብ፣ ያለ ቅዱሳን ምስጢራት እንዲያው በግለሰብ ደረጃ ቢቻ ከኢየሱስ ጋር የምደርገው  ቅርብት አደገኛ ነው። የእግዚአብሔርን ሕዝብ ባላማከለ መልኩ በግለሰብ ደረጃ ብቻ የሚደረግ ቅርበት አደገኛ ነው። ሐዋርያቶች ከጌታ ጋር የነበራቸው ቅርበት ሁሌም ማኅበራዊ በሆነ መልኩ ነበር፣ ሁል ጊዜም ጠረጴዛው ዙሪያ ይሰበሰቡ ነበር፣ ይህም የአንድነት እና የሕብረት ምልክት ነበር። ሁልጊዜም ከቅዱሱ ቁርባን እና ከእንጀራ ጋር የተገናኘ ነበር።

ይህንን የምልበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ይህ ወረርሽኝ አደጋ በደቀንበት በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት አንድ ሰው በእዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሰላስል ስላስቻለኝ ነው፣ ይህ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ እንዳይገናኝ ማደረጉ የሚታወቅ ሲሆን ማነኛውም መንፈሳዊ የሆነ አገልግሎት ለምሳሌም መስዋዕተ ቅዳሴ የምትከታተሉት የመገናኛ ብዙሃን አውታሮችን በመጠቀም ምናባዊ በሆነ መልኩ ሲሆን እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች እኛን ሁላችንንም የሚያገናኙት ምናባዊ በሆነ መልኩ በመንፈስ እንጂ በአካል እንዳልሆነ ይታወቃል። 

ቅዱስ ቁርባን እንኳን ሳይቀር የምንሳተፈው በእያለንበት ሆነን በምንፈጥረው መንፈሳዊ ኅብረት አማካይነት ብቻ ነው። እናም ይህ ቤተክርስትያን አይደለም- ይህን ጌታ የምፈቅደው አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ በምንገባበት ወቅት ብቻ ነው፣ ነገር ግን ትክከለኛዋ ቤተክርስትያን የምትገለጸው ቅዱሳን ምስጢራት በምገኙበት እና ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ሕዝብ በምሰበሰቡበት ስፋር ብቻ ነው። ሁሌም እንዲህ ነው።

ከፋሲካ በፊት እኔ ይህንን የፋሲካ በዓል ባዶ በሆነው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መስዋዕተ ቅዳሴ በማደረግ እንደ ማከብር የሚያመለክት ዜና በወጣበት ወቅት መልካም ባሕርህ ያለው አንድ ጳጳስ በላከልኝ መልእክት ይህንን ሐሳቤን ገስጾት ነበር። “ነገር ግን እንዲህ እጅግ በጣም ትልቅ የሆነው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰዎች ተራርቀው ቢቀመጡ እና የሚካሄደውን መስዋዕተ ቅዳሴ ሰዎች በእየቤታቸው ሁነው በማኅበራዊ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ምናባዊ በሆነ መልኩ ቢከታተሉ ምን አለበት?” ብዬ አሰብኩኝ። ነገር ግን እርሳቸው ይህንን  ለመናገር እና በአእምሮ ለማሰብ የቻሉት እንዴት ነው? በማለት በወቅቱ ጥያቄ አንስቼ ነበረ፣ በወቅቱ አልገባኝም ነበር። ይህንን ነገር ያሉኝ ጳጳስ ለሕዝባቸው እጅግ በጣም ቅርብ የነበሩ መልካም የሆኑ ሰው ናቸው። እርሳቸውን ሳገኛቸው እጠይቃቸኋለሁ ብዬ አስበኩኝ። ከእዚያን በኋላ ግን  ጉዳዩ ተገለጸልኝ። እርሳቸው ሊሉኝ የፈለጉት ነገር ቢኖር “ቤተክርስትያን፣ ቅዱስ ቁርባን ፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ተጨባጭ የሆኑ ነገሮች ናቸው። ስለሆነም ይህ ወረርሽኝ ካለፈ በኋላ እንኳን ሕዝቡ መስዋዕተ ቅዳሴ በእዚህ መልኩ በማኅበራዊ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ምናባዊ በሆነ መልኩ መከታተል ልምዱ አድርጎ እንዳይቀጥል ተጠንቀቅ” ለማለት ፈልገው የተናገሩት ነው። እውነት ነው፣ በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ቅርበት ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ እንዲህ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ጌታ በዕለት ተዕለት ኑሮ በቅዱሳን ምስጢራት አማካይነት በእግዚአብሔር ህዝብ መካከል የገኛል። ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ግንኙነት እዲጎለብት አድርጉ። ቤተክርስትያን፣ ቅዱሳን ምስጢራት እና የእግዚአብሔር ሕዝብ ተጨባጭ የሆኑ ነገሮች ናቸው። አሁን ያለው ወረርሽኝ ሲጠናቀቅ ሁሉም ወደ ቦታው ይመለሳል። ጌታ ከእርሱ ጋር፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከምስጢራት እና ቅዱስ ከሆነው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ያለን የጠበቀ ወዳጅነት ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲያስተምረን እንጠይቀው።  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከእዚህ በላይ የተጠቀሰውን ስብከት አድርገው መስዋዕተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኋላ የቅዱስ ቁርባን አምልኮ ተደርጎ ካበቃ በኋላ በቅዱስ ቁርባን ባርከው ስረዓት ቅዳሴው መጠናቀቁ ተገልቱጿል።

17 April 2020, 18:25
ሁሉንም ያንብቡ >