ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የራሳቸውን ሕይወት ለአደጋ አጋልጠው ሌሎችን በመርዳት ላይ ለሚገኙ ደናግላን ጸሎት አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 16/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት በአሁኑ ወቅት እየተከሰተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተጠቁትን ሰዎች በተለያየ መልኩ በመርዳት ላይ የሚገኙትን ገዳማዊያን/ገዳማዊያት በጸሎታቸው ያሰቡዋቸው ሲሆን በተለይም ደግሞ በእዚህ ወረርሽኝ የጠቁትን ሰዎች፣ ድሆችን እና አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት ላይ የሚገኙትን ደናግላን አመስኘው እና በጸሎታቸው ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ የገለጹ ሲሆን በተለይም ደግሞ እርሳቸው ማለትም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት መኖሪያ በሆነው በቅድስት ማርታ ቤት የሚገኙትን የፍቅር ሥራ ልጆች ማሕበር ደናግላን ላለፉት 98 ዓመታት ለድሆች እና ለአቅመ ደካሞች አስፈላጊውን እለታዊ እርዳታ በማቅረብ ላይ እንደ ሚገኙ ገልጸው ለእዚህ አንድ ምዕተ አመት ሊሞላው 2 ዓመት ብቻ ለቀረው የበጎ ሥራ ተግባራቸው ቅዱስነታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ሀ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበስረበት እና የኢየሱስ መወለድ አስቀድሞ የተገለጸበት እለት ዓመታዊ በዓል ተክብሮ ያልፈ ሲሆን “እግዚአብሔር መልአኩ ገብርኤልን በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ናዝሬት ከተማ ላከው፤ የተላከውም ከዳዊት ዘር ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል ነበር፤ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም እርሷ ወዳለችበት ገብቶ፣ “እጅግ የተወደድሽ ሆይ፤ ሰላም ለአንቺ ይሁን፤ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” አላት። ማርያምም በንግግሩ እጅግ በጣም ደን ግጣ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሰላምታ ይሆን?” እያለች ነገሩን ታሰላስል ጀመር፤ መልአኩም እንዲህ አላት፤ “ማርያም ሆይ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” (ሉቃስ 1፡26 38) በማለት ማርያምን ያበሰረበት ዓመታዊ በዓል ተክብሮ ማለፉ ተገልጹዋል።

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ይህንን አመታዊ በዓል ከግምት ባስገባ መልኩ ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት “ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም ሥጋ ለብሶ እንደ ሚውለደ የተነገረበት ቀን በምናከብርበት ወቅት በቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ሆነው ለባለፉት 98 አመታት ያህል ድሆችን፣ በሽተኞችን እና አቅመ ደካሞችን ደከመኝ ሰለች ሳይሉ የማሕበራቸውን መክሊት ጠብቀው ሲያገለግሉ የነበሩ በቅዱስ ቪንሰንት እና በቅድስት ሉዊዛ አማካይነት የተመሰረተው የፍቅር ሥራ ልጆች ማሕበር አባላትን በጸሎታቸው ያስታወሱ ሲሆን ለእዚህ መተኪያ ለሌልው የበጎ ሥራ ተግባራቸው ቅዱስነታቸው ምሥጋና አቅርበው፣ በእለቱ ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ እነርሱን በማሰብ መከናወናቸው ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው ከላይ በተጠቀሰው እና ከሉቃስ ወንጌል (1፡ 26 38) ላይ ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

“ወንጌላዊው ሉቃስ ይህንን ታሪክ ልያውቀው የቻለው ከማርያም ብቻ ነው። ቅዱስ ሉቃስ የጻፈውን ይህንን ታሪክ በማዳመጥ ይህንን ምስጢር የተናገረችው ማርያም መሆኑዋን እንገለዘባለን። ምስጢሩ ፊት ለፊ ቆመን እንገኛለን። ምናልባት አሁን ማደረግ የምንችለው ይህንን ታሪክ የተናግረችው እመቤታችን ማርያም ናት ብለን  በማሰብ ይህንን ምንባብ እንደገና ማንበብ ነው” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በካቶሊክ ቤተክርስቲያ ስርዓተ አምልኮ ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከፍተኛ የሆነ ቦታ እንደሚሰጣት ይታወቃል። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዶግማ (ቀኖና) ወይም የማይሻር የማይለወጥ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውስጥ ማርያምን የሚመለከቱ 4 (አንቀጸ እምነቶች) ዶግማዎች ይገኛሉ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ እናት ብቻ ሳትሆን እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “በባሕርዩ አምላክ በመሆኑ” (ፊል 2፡6) የተነሳ “የእግዚኣብሔር እናት ናት” የሚለው ማርያምን በተመለከተ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን አንቀጸ እምነት ውስጥ የተካተተ የእምነት አስተምህሮ ሲሆን (Mary Mother of God) ዓመታዊ በዓሉም በፈረንጆቹ አዲስ አመት መጀመርያ ላይ ይከበራል፣ በኢትዮጲያ የቀን አቆጣጠር በታኅሳስ 22/2012 ዓ.ም ዓመታዊ በዓሉ በድምቀት የከበራል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በኅዳር 28/2012 ዓ.ም. የሚከበረው የጽንሰተ ማርያም ዓመታዊ በዓል ሲሆን ይህ “የጽንሰተ ማርያም” በዓል ማርያም “ያለአዳም ኃጢአያት የተጸነሰች ናት፣ ምክንያቱም እግዚኣብሔር የልጁ እናት እንድትሆን አስቀድሞ የመረጣት በመሆኑ የተነሳ እኛ ሰዎች ሁላችን ይዘነው የምንወለደው እና ምስጢረ ጥምቀት በምንቀበልበት ወቅት ከሚደመሰሰው (ከሚሰረየው) ኃጢአት  ነጻ ሆና እንድትወለድ እግዚኣብሔር አድርጓታል” የሚለው በሁለተኛ ደረጃ የምናገኘው ዶግማ (ቀኖና) (Imaculate conception) ነው።

በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የጸነሰቺው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት ነው፣ እርሱንም የወለደቺው በድንግልና ነው፣ ከወለደችሁም በኋላ እንኳን ለዘልዓለም ድንግል ሆና ትኖራለች” የሚለው 3ኛው ዶግማ (ቀኖና)  ነው (The Perpetual Virginity of Mary) (ሉቃስ 2፡22-40)።

በአራተኛ ደረጃ የምናገኘው ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ሰማይ በክብር ያረገችበትን ሁኔታ የሚገልጽ ቀኖና (Dogma) ሲሆን ይህ “የፍልሰታ ማርያም” በዓል በሀገራችን የቀን አቆጣጠር በእየዓመቱ በነሐሴ 16 የሚከበረው በዓል ነው፣ “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ የነበራት ቆይታ ካበቃ በኋላ በነፍስ እና በሥጋ ወደ ሰማይ ተወሰደች” በማለት ማርያም በነፍስ እና በሥጋ ወደ ሰማይ መፍለሷን የሚያመልክት ቀኖና ነው (The Assumption of Mary into heaven)።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
25 March 2020, 16:34
ሁሉንም ያንብቡ >