ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት እውነተኛ ፍቅር እግዚአብሔር እንዲሰጠን እንጸልይ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 07/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ  ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በአሁኑ ወቅት በእዚህ በኮርኖ ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለታመሙ ሰዎች መጸለያቸውን የቀጠሉ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች ሁሉ ቅዱስነታቸው ተጸሎታቸውን አቅርበዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት በትዕቢት ተወጥረን እንዳንወድቅ እግዚአብሔር ያሳየንን ትህትና ልንላበስ የገባል ያሉ ሲሆን በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት እውነተኛ ፍቅር እግዚአብሔር እንዲሰጠን ልንጸልይ ይገባል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ሀ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባደረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ቤተክርስቲያን ሂደው መስዋዕተ ቅዳሴ ማስቀደስ ያልቻሉ ሰዎች እራሳቸው ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ በቴሌቪዢን በቀጥታ ምዕመኑ ለመከታተል ያስቸልው ዘንድ ታስቦ በቪዲዮ መተላለፉ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ በኮርኖ ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተጠቁ ሰዎች ሁሉ ቅዱስነታቸው ጸሎት አድርገዋል፣ ለታመሙ ቤተሰቦች መጸለያቸውን ቀጥለዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ “ለታመሙ ሰዎች መጸለያችንን እንቀጥላለን ፡፡ ስለ ቤተሰቦች ፣ ተገልለው ስለሚገኙ ሰዎች፣ ትምህርት ቤት መሄድ ላልቻሉ ልጆች፣ ከቤት መውጣት ላልቻሉ ሰዎች በሙሉ ጸሎታችንን ማቅረብ መቀጠል ይኖርብናል” ብለዋል። ይህ አጋጣሚ “አዲስ መንገዶችን ፣ አዲስ የፍቅር መግለጫዎችን፣ በአዲስ ሁኔታ እና መልኩ አብሮ የመኖር ክህሎት የምናዳብርበት አጋጣሚ ይሆን ዘንድ ጌታ እንዲረዳን” ልንጸልይ ይገባል ብለዋል። በቤተሰብ ውስጥ አብሮ በመኖር እውነተኛ ፍቅርን ለማግኘት ጥሩ አጋጣሚ ነው” በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በቤተሰብ ውስጥ አሁን ያለው ግንኙነት ሁል ጊዜም በጎ እና  መልካም እንዲሆን ለቤተሰብ እንጸልይ” ብለዋል።

በወቅቱ በተደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከሁለተኛው መጽሐፈ ነግሥት (2 ነገሥት 5 ፣ 1-15) ተወስዶ በተነበበው እና በመቀጠልም ከሉቃስ ወንጌል (ሉቃስ 4 ፣ 24-30) ተስዶ በተነበበው የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ቅዱስነታቸው ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት “ዛሬ በተነበቡልን በሁለቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ትኩረትን የሚስብ አመለካከት አለ ፣ መልካም ያልሆነ ነገር የሰውን አስተሳሰብ የሚወክል አንድ ነገር አለ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን መስማት ጀመሩ፣ የእርሱን አነጋገር እጅግ በጣም ወደውት ነበር፣ ከእነርሱ መካከል የነበረ አንድ ሰው እንዲህ አለ፣ ለመሆኑ ይህ ሰው ‘በየትኛው ዩኒቨርሲቲ ነው የተማሩው? ይህ የማርያም እና ዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ! የአናጺው ልጅ ነው! ምን ሊነግረን ይሆን?’” በማለት ሕዝቡ በተስበሰበበት ቦታ መናገሩን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በአዚህ ምክንያት ሕዝቡ የቁጣ ስሜት ውስጥ ገብቶ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህ ቁጣ ወደ ዓመፅ ሕዝቡን እንደ መራ የገለጹት ቅዱስነታቸው በስብከቱ መጀመሪያ ላይ ኢየሱስን አድንቀውት የነበሩት ሰዎች፣ በመቀጠልም ኢየሱስን ከተማቸው ከተሠራችበት የተራራ ጫፍ ላይ አውጥተው ሊጥሉት እንደ ፈለጉ ጨምረው ገልጸዋል።

በመጀመሪያው ምንባብ ውስጥ የተጠቀሰው ከለምጽ የነጻው ንዕማን ደግሞ ራሱን ለእምነት የከፈተ ጠንክራ እመነት የነበረው ሰው እንደ ሆነ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ነቢዩ ከለምጹ ይነጻ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ እንዲታጠብ በነገው ወቅት በጣም ተቆጥቶ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው “ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ ‘እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። ለዚህ ለዚህ የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋር ከየትኞቹም የእስራኤል ውሆች አይሻሉምን? ለመታጠብ ለመታጠብማ በእነርሱ ታጥቤ መንጻት አልችልምን?” ስለዚህ በቍጣ ተመለሰ” 2 ነገሥት 5፡11 12) በማለት በንቀት ተናግሮ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

“በናዝሬት ውስጥ እንኳን ጥሩ ሰዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እነዚህን ሰዎች ወደ ቁጣ እንዲያመሩ የሚያደርጋቸው ከእነዚህ ጥሩ ሰዎች በስተጀርባ ያለው ነገር ምንድነው?” በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በናዝሬት የተደረገው ነገር ንዕማን ካደርገው ነገር የሚብስ እንደ ሆነ ገልጸው ንዕማን እና በናዝሬት በሙክራብ ውስጥ የነበሩ ሰዎች እግዚአብሔር እራሱን የሚገልጸው እነርሱ እንደ ለመዱት “ባልተለመዱ ነገሮች ውስጥ ብቻ ነው” ብለው ያስቡ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

“እግዚአብሔር በህይወት ውስጥ በተለመዱ ልማዳዊ ነገሮች እና በቀላሉ በምናያቸው ነገሮች ተግባሩን ሊያከናውን እንደሚችል አልተገነዘቡም ነበር፣ በእዚህም የተነሳ ነው እግዚአብሔር ተግባሩን ቀልል ያሉ ነገሮችን ተጠቅሞ ሲያከናውን ሕዝቡ ቀለል ያሉ ነገሮችን ስለሚንቁ ወደ ቁጣ ስሜት ውስጥ የገቡት በእዚህ ምክንያት መሆኑን” የገለጹት ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር ግን ተግባሩን ሁልጊዜ የሚያከናውነው ቀልል ያሉ ነገሮችን ተጠቅሞ ነው ብለዋል። አምላካችንም ሁልጊዜ ቀልል ባለ ሁኔታ እንደ ሚሠራ፣ ኢየሱስ በናዝሬት በነበረበት ወቅት እለታዊ ተግባሩን ቀልል ባለ ሁኔታ እንደ ማንኛውም ሰው ያከናውን እንደ ነበረ፣ እንደ ማነኛውም ሰው ቀለል ያሉ ጸሎቶችን ያዘወትር እንደ ነበረ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይልቁኑ የዓለም መንፈስ ወደ ከንቱነት እና ወደ ትዕይንቶች እንደ ሚያመራ ጨምረው ገልጸዋል።

“በሁለቱም ማለትም በመጀመሪያው ምንባብ ውስጥ የተጠቀሰው እና እንዲሁም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው ጭብጥ የተጠናቀቀው በቁጣ” እንደ ነበር በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ንዕማን በጣም ጨዋ ሰው የነበረ ቢሆንም ቅሉ በንዴት በሩን በነቢያቱ ፊት ላይ ወርውሮ እንደ ዘጋ ገልጸዋል። “ንዴት የጥቃት ምልክት ነው፣  በናዝሬት በምኩራብ የነበሩ ሰዎች ቀስ በቀስ እየሞቁ እየጋሉ ሂደው ከእዚያም ኢየሱስን ለመግደል ውሳኔ ማድረግ ጀመሩ፣ የሚያደርጉትን ተግባር በሚገባ ሳያስተውሉ እሱን ለመግደል ከተማቸው ወደ ተሰራችበት አፋፍ ላይ ወስደው ወደ ታች ሊጥሉት ፈለጉ” ያሉት ቅዱስነታቸው  ንቀት ወደ ዓመፅ የሚያመራ አስቀያሚ የሆነ ሙከራ ነው ብለዋል።

“ይህ በእኛ ላይ ሊከሰት የሚችል ተግባር ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የስነ መለኮት ሙሁራን እንደ ሚገልጹት “እግዚአብሔር ቀልል ባለ ሁኔታ የሚፈጽማቸው ተግባራት ለእኛ ፈተና ሊሆኑብን እንደ ሚችሉ” ገልጸው እግዚአብሔር ነገሮችን ቀለል ባለ ሁኔታ በሚፈጽምበት ጊዜ ‘የእኛ አምላክ ጠበበኛ ነው፣ የእኛ አምላክ እንዲህ ቀልል ያሉ ነገሮችን አያድርግም’ የሚለው አስተሳሰብ አንዳንዴ አይሎ እንደ ሚወጣ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። “የእኛ አምላክ ታላቅ ነው፣ እንዲህ ቀለል ያሉ ነገሮችን አያደርግም፣ እንዲህ አይሆንም፣ አምላካችን ይበልጥ የተዋጣለት ፣ ጥበበኛ ፣ እና አስፈላጊ የሆኑ ድንቅ ሥራዎችን የሚሰራ አምላክ ነው። በዚህ ቀልል ባለ መልኩ እግዚአብሔር እርምጃ ሊወስድ አይችልም” ብለን በመናገር እና በማሰብ ሁልጊዜ ወደ ቁጣ እናመራለን፣ ቁጣችን ደግሞ ወደ ዓመፅ  ይቀየራል” ያሉት ቅዱስነታቸው ቁጣ አካላዊ እና እንዲሁም በቃላት የተደገፈ ጥቃት በሰው ላይ እንድንፈጽም ያነሳሳናል ብለዋል።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ “እነዚህን ሁለት እርምጃዎች እስቲ እንመልከት-በናዝሬት ምኩራብ ውስጥ የነበረው የሰዎች ቁጣ እና የንዕማን ተስፋ መቁረጥ በተመለከተ እናስብ፣ አምላካችን ነገሮችን ቀልል ባለ መልኩ እንደ ሚያከናውን እንድንረዳ ሊረዱን የሚችሉ ተግባራት ናቸው” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
16 March 2020, 16:13
ሁሉንም ያንብቡ >