ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሊያጠፋን የሚፈልገውን የዲያቢሎስ መንፈስ መዋጋት እንችል ዘንድ ጸጋውን እዲሰጠ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በመጋቢት 02/2012 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እና እንዲሁም በጣሊያን በስፋት በመስተዋል ላይ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክያት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን በተለይም ይህ ቫይረስ እንዳይዛመት ሰዎች በተቻላቸው መጠን በአንድ ቦታ መሰብሰብ የለባቸውም የሚለውን የጤና ባለሙያ ምክር ከግምት በማስገባት ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት በርካታ ሰዎች ተሰብስበው የሚኖሩባቸው ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ሁኔታ አስጊ በመሆኑ የተነሳ ጸሎት ሊደረግላቸው እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ የጀመሩት በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን የሕግ ታራሚዎች በማሰብ እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለማረዳት የተቻለ ሲሆን “በተለይ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሚገኙ ወንድሞች እና እህቶች መጸለይ እፈልጋለሁ፣ በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ወንድሞችን እና እህቶቻችንን ጌታ እዲያጽናናቸው በጸሎታችን ለእነርሱ ቅርብ መሆን አለብን” ማለታቸው ተገልጹዋል።
በወቅቱ በተደርገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከትንቢተ ኤርሚያስ 18፡18-20 እና ከማቴዎስ ወንጌል 20: 17-28 ላይ ተወስዶ በተነበበው ምንንባባት ላይ ትኩረቱን ባደርገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት
ዲያቢሎስ የጌታን ሳይሆን የራሱን እቅድ እንድንቀበል እንደ ሚፈተተነን የገለጹ ሲሆን ልክ በነቢዩ ኤርሚያስ ላይ እንዳደረገው ሁሉ ዲያቢሎስ በመንገዳችን ላይ እንቅፋቶችን ያኖራል ያሉ ሲሆን በእዚህ ፈተና ውስጥ በገባበት ወቅት ነቢዩ ኤርሚያስ የጌታውን ስቃይ ትንቢት መሳክሪ ሆኖ ነበር ብለዋል።
ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት “በየቦታው የዲያቢሎስን መንገድ በመዝጋት መሰናክል እንሁነበት፣ … ዲያቢሎስ ‘እሱን እናሸንፈው’ ወይም ደግሞ ከሕይወታችን አሽቀንጥረን አውጠተን እንጣለው። 'ህይወቱን አስቸጋሪ እናድርግበት” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ተግባራችን ዲያቢሎስ ውርደቱን እንዲከናነብ ያደርገዋል ብለዋል።
የዲያቢሎስ የመጀመሪያ ዘይቤ
ክርስቲያኖችን በሚያሳድድበት ጊዜ ዲያቢሎስ ሁለት መንገዶችን ይከተላል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጀመሪያ “የመዳን ዕቅድን እንዲለውጡ በማድረግ” በአለማዊነት መንፈስ እንዲሞሉ ሊያሳስት ይሞክራል ብለዋል። በዘብዴዎስ ልጆች እናት አፍ ላይ የተገለፀው ይህ ዓለማዊ መንፈስ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከንቱነት፣ ዓለማዊነት፣ አዋቂነት እና ስኬት “ዲያብሎስ ከክርስቶስ መስቀል እንድንርቅ የሚያቀርብልን” ዓለማዊ መስፈርቶች ናቸው ብለዋል።
የዲያቢሎስ ሁለተኛ ዘይቤ
ዲያቢሎስ ከእዚህ በላይ የተጠቀሰውን የመጀመሪያ የማሳሳቻ መንገድ እርሱ ባስበው መልኩ የማይሄድ ሆኖ ካገኘው ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠውን እቅዱን ተግባራዊ በማደረግ ግለሰቡን ለማጥፋት ይሞክራል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የዲያቢሎስ ኩራት በጣም ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ በሰዎች ላይ በሚፈጽመው ክፋት እና ጥፋት እጅግ በጣም ስለሚደሰት ሕይወታቸውን ያበላሻል” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተናግረዋል። ይህ የዲያቢሎስ ተግባር በብዙ ቅዱሳን እና የክርስቲያኖች ስደት ላይ ተንፀባርቋል፣ እነርሱ ወዲያሁኑ አልተገደሉም፣ ነገር ግን ለከፍተኛ ስቃይ እንዲዳረጉ ሁነዋል፣ እነሱ በየትኛውም ዓይነት ውርደት አልፎ ተርፎም በሞት እንዲሰቃዩ ተደርገዋል ብለዋል።
“ይህ ኢየሱስንም ቢሆን ያጋጠመው ሁኔታ ነው፣ ከኢየሱስ ጋር የተሰቀሉት ሁለቱ ሌቦች እንደ እርሱ አልተሰቃዩም። እነርሱ በሰላም እንዲሞቱ ነበር የተደርገው። ማንም ሰው እነዚህን ሁለት ሌቦች አልተሳደባቸውም ነበር። ለእነሱ ማለትም ለሁለቱ ሌቦች ለእነሱ ምንም ፍላጎት አልነበራቸውም ”ብለዋል።
ማስተዋል ዲያብሎስን እንድናሸንፍ ያደርጋል
“ዲያቢሎስ በእኛ ላይ እንዴት እየሠራ እንዳለ መገንዘብ ዲያቢሎስ እኛ በምንጓዝበት የአንድ ደቀመዝሙር መንገድ ላይ ያስቀመጠውን መሰናክሎች ለማሸነፍ የሚያስችል መንገድ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ ሰው ስደት ሲደርስበት የዲያቢሎስ “በቀል” እንዳጋጠመው ሊቆጥር የገባዋል ምክንያቱም እሱን ድል አድርገውታል ማለት ነው ብለዋል። ይህ “በጭካኔ በመሰደድ ላይ በሚገኙ” ብዙ ክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ይህ ዛሬ በግልፅ ታይቷል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አሲያ ቢቢ በመባል የምትታወቀው አንድ በፓኪስታናዊ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመን ላይ ለዘጠኝ አመታት ያህል በእስር ቤት ውስጥ በደረሰባት ስቃይ ላይ ቅዱስነታቸው አስተንትኖ አድርገዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ይህ የሰይጣን ተንኮል ወጤት ነው” ብለዋል።
የሊቀ ጳጳሱ ጸሎት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት ያጠናቀቁት የዲያቢሎስን ፈተና በምን ዓይነት ሁኔታ እና አግባብ ማሸንፈ እንደ ሚቻል ምክረ ሐሳብ በመስጠት ሲሆን የዲያቢሎስን ፈተና መሻገር እንችል ዘንድ “ሊያጠፋን የሚፈልገው መንፈስ የሚገኝበትን ስፍራ እንዴት መለየት እንደምንችል የምናውቅበትን ጸጋ ጌታ ይስጠን… እናም ከንቱ በሆነው በአለም እይታዎች ውስጥ ገብተን እንድንጽናና የሚፈልገውን ያ ተመሳሳይ መንፈስ የምንዋጋበትን ኃይል ስጠን” ብለን ልንጸልይ የገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጅቱትን ስብከት አጠናቀዋል።