ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቤተሰብ ውስጥ ትዕግስት፣ ምስጋና ማቅረብ እና ይቅርታ መደረረግ ያስፈልጋል አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 06/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በእየለቱ በሕይወት ጎዳና ላይ አብረውን የሚጓዙትን ሰዎች በልባችን ውስጥ ስፍራ ልንሰጣቸው እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን እነዚህን ሰዎች ልናመሰግናቸው እና ከበደልናቸው ደግሞ ይቅርታን ልንጠይቅ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያደረጉት ስብከት የቅድስት ማርታ ቤት ተብሎ በሚታወቀው እርሳቸው በሚኖሩበት ቤት ውስጥ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ብዙ አስተዋጾ በማበርከት ላይ የሚገኙ ሰዎች እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም የተነሳ “አንድ ትልቅ ቤተሰብ” ሊባል በሚችል መልኩ በፍቅር እና በመተሳሰብ የሚያገለግሉ ብዙ ሰራተኞች እንዳሉ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ጨምረው እንደ ገለጹት በህይወት ጉዞ ላይ አብረውን የሚጓዙ፣ በየቀኑ በሥራ የሚተጉ፣ ሰዎች ከታመሙ የሚረዱ እና ሐዘን ላይ በሚሆኑበት ወቅት አብረው የሚያዝኑ እና የሚያጽናኑ ሠራተኞች እንደ ሚገኙም ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው እርሳቸው እና የሥራ ባለሟሎቻቸው የሆኑት ቄሳውስት በሚኖሩበት የቅድስት ማርታ ቤት ተብሎ በሚታወቀው ቤት ውስጥ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ምዕመናን እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህ ሰራተኞች መካከል አንዷ የሥራ ጊዜዋን አጠናቃ በጡረታ በተሰናበቱበት ወቅት እርሳቸውን ለማሰብ በተደረገው የምስጋና መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ሥረተኞቻችን የሚያሳዩን ፈገግታ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ታትሞ ይቀራል ያሉት ቅዱስነታቸው በወቅቱ በጡረታ ከሥራቸው የተሰናበቱት አንዲት ሴት በነበራቸው የሥራ ዘመን ለተደረገላቸው ነገሮች በሙሉ አመስግነው እና ላጠፉት ጣፋት ደግሞ ይቅርታ መጠየቃቸው ተገልጹዋል።

ራስ ወዳድነት ኃጢአት ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ጨምረው እንደ ገለጹት ራስ ወዳድነት ኃጢአት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ቤተሰብ ማለት “አባት፣ እናት፣ ወንድም፣ እህት፣ አጎት፣ አክስት ቅድመ አያት” ወዘተ ብቻ ማለት እንዳልሆነ የገለጹ ሲሆን “በሕይወት ጉዞ ላይ አብረውን የሚጓዙን ሰዎች በሙል የቤተሰባችን አባላት በመሆን ትልቅ የሆነ ቤተሰብ” መመስረት እንደ ሚቻል ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

እኛን ብቻችንን ስላልተወን ጌታን አመሰግናለሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ጨምረው እንደ ገለጹት የታመሙ ሰዎችን የሚንከባከቡ ብዙ የሥራ ባልደረቦቻችንን ማስታወስ ተገቢ እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን ከእያንዳንዱ ሰው ስም በስተጀርባ ታሪክ ጥለውት የሚያልፉት መልካም አሻራ እንደ ሚገኝ ገልጸዋል። በእዚህ መልኩ በሰዎች ልብ ውስጥ አሻራ አስቀምጠው የሚያልፉ ሰዎች እንደ ሚገኙ የገለጹ ሲሆን መልካም ያደረጉልንን ሰዎች ማመስገን ቅር ያሰኙንን ሰዎች ደግሞ ይቅርታ ማድረግ አስፈላጊ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ኃጢአት መሥርት፣ ትዕግሥት ማጣት ከዚያም ይቅርታ መጠየቅ እነዚህ ሦስቱ ነገሮች በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በእየለቱ የሚታዩ ነገሮች እንደ ሆኑ የገለጹት ቅዱስነታቸው ለበደልነው በደል ይቅርታ መጠየቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ መሆኑን፣ ለተደረገልን መልካም ነገር በሙሉ ምስጋናን ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን እና  ለበደልነው በደል ደግሞ ይቅርታን መጠየቅ ተገቢ መሆኑን ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

14 February 2020, 15:55
ሁሉንም ያንብቡ >