ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ኢየሱስ ያሰተማረን የትህትናን መንገድ ነው” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ለተገኙ ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 6፡14-29 ላይ ተወስዶ በተነበበውና የመጥምቁ ዮሐንስ መሰየፍ በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ኢየሱስ ያስተማረን የትህትናን መንገድ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ክርስቲያኖች የኢየሱስ እና የመጥምቁ ዮሐንስን አብነት መከተል እንደ ሚገባቸው የገለጹ ሲሆን ኢየሱስ እና መጥምቁ ዮሐንስ በሕይወታቸው ያሳዩትን ከፍተኛ ትህትና ክርስቲያኖች ሊከተሉት የሚገባው መንገድ ነው ብለዋል። የቤተክርስቲያን አባቶች ሳይቀር ለዓለማዊ ክብር ሳይገዙ በሕይወት ሂደት የሚያጋጥማቸውን ፈተና በትህትና መጋፈጥ እንደ ሚገባቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ለክርስቶስ ስንል “ውረደትን መቀበል” በፍጹም መፍራት የለብንም፣ ትሁታን እንሆን ዘንድ እንዲረዳን ጌታን ልንጠይቀው ይገባል፣ በእዚሁ መልኩ ብቻ ነው ኢየሱስን መምሰል የምንችለው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ትሁት ያልሆነ ክርስቲያን ክርስቲያን ነኝ ሊል በፍጹም አይችልም ብለዋል።

የኢየሱስ መንገድ

በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት መጥምቁ ዮሐንስ የኢየሱስን “መንገድ” እንዲያስተካክል በእግዚኣብሔር መላኩን የገለጹ ሲሆን “የመጨረሻው ነቢይ”  የሆነው እርሱ ኢየሱስ መሲህ መሆኑን እንደ መሰከረ ጨምረው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጽናት በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

 የመጥምቁ ዮሐንስ እጅግ መሰረታዊ እና ዋና ተግባር የነበረው ኢየሱስ እንደ ሚመጣ መስብከ እና ሕዝቡን ማዘጋጀት ብቻ አልነበረም፣ ነገር ግን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ለመስጠት እና በገዛ ሕይወቱ ይህንን ምስክርነት ለማጽናት ተላከ እንጂ። ለደህንነታችን እግዚአብሔር የመረጠውን መንገድ ለመመስከር መጣ- የውርደትን መንገድ ተጓዘ። ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ በግልፅ አስቀምጧል “ኢየሱስ ራሱን በመስቀል ላይ እስከ ሚሞት ድረስ ራሱን አዋርዱዋል”          ይለናል። እናም ይህ የመስቀል መንገድ፣ ይህ ራስን የማዋረድ መንገድ የእኛም መንገድ ሊሆን ይገባል እግዚአብሔር ክርስቲያኖች እንዲጓዙበት ያሳየው መንገድ ይህ ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ “እንዲታበዩ እና ኩራተኛ እንዲሆኑ” የሚያደርጋቸው ፈተና ገጥሙዋቸው ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  ኢየሱስ በበረሃ አርባ ቀን ያህል ከጾመ በኋላ “በዲያቢሎስ መፈተኑን” መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ “አንተ መሲህ ነህ” ብለው የሕግ መምህራን ጠይቀውት እንደ ነበር ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “አዎን መሲህ ነኝ” ብሎ መመለስ ይችል ነበረ፣ ነገር ግን ራሱን ዝቅ በማድረግ የጫማውን ማሰሪያ እንኳን ለመፍታት የማልችል ሰው ነኝ በማለት ራሱን ዝቅ አድርጎ ምላሽ እንደ ሰጠ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ሁለቱም አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ “በሕዝቡ ፊት ስልጣን ነበራቸው” ስብከታቸውን ያከናውኑ የነበሩት “እንደ ባለስልጣን ነበር”፣ ነገር ግን ሁለቱም “ራሳቸውን ዝቅ የሚያድርጉበት ጊዜ ነበራቸው” ብለዋል።  ሁለቱም “እንደ ሰው አዝነዋል መነፈሳዊ ጭንቀት ገጥሞዋቸዋል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በደብረ ዘይት የአትክልት ስፍራ፣ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ በእስር ቤት ውስጥ በነበረበት ወቅት “ኢየሱስ በእውነት መሲህ ነው ወይ?” የሚል ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ እንደ ነበረ ገልጸዋል። ሁለቱም እንደገና ሕይወታቸው የሚጠናቀቀው “በጣም በተዋረደ መልኩ” እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንደ አንድ ወንጀለኛ ተስቅሎ በመሞት አካላዊ እና መንፈሳዊ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን “በሕዝቡ እና በእናቱ ፊት ሳይቀር ራቁቱን” በመስቀል ላይ እንዲሆን መገደዱን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። መጥምቁ ዮሐንስ “በዳንኪራ ጩኸት እና በአንዲት አመንዝራ ሴት ጥላቻ የተነሳ” በንጉሡ ትእዛዝ “ጠባቂው በእስር ቤት ውስጥ ጭንቅላቱን ቆርጦ ለሄሮዲያዲያ እና ለሴት ልጇ ጭንቅላቱን ማስረከቡን” ጨምረው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ሐሳባቸውን ለማጥናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ነቢዩ ከሴት ከተወለዱ ሰዎች ሁሉ ታላቅ የነበረ ነቢይ ነው፣ በእዚህ መልኩ ነበር ኢየሱስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ብቃት የመሰከረው፣ የእግዚአብሔር ልጅ የውርደትን መንገድ መረጠ። እርሱ ለእኛ ክርስቲያኖች የሚያሳየው እና እኛ ክርስቲያኖች ልንከተለው የሚገባን መንገድ ነው። በእውነቱ በተራራ ላይ ሆኖ በሰበከው ስብከት ውስጥ መንገዱ የትሕትና መሆኑን በጥብቅ ገልጹዋል።

ዓለማዊ የሆነ መንገድ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደገለፁት “ያለውርደት የዋህ መሆን በፍጹም አይቻልም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ሲሆን እግዚኣብሔር ዛሬ ለእኛ ክርስቲያኖች የሚያቀርብልን ጥሪ ትሁታን እንድንሆን ነው ብለዋል። ይህንን ሐሳባቸውን ቅዱስነታቸው ለማጠናከር በማሰብ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

በቤተክርስቲያን እና በማህበረሰቡ ውስጥ ሳይቀር ራሳችንን ለማሳየት ከፍ ያለ ቦታ ወይም ነገር ለማግኘት ወይም እንዲኖረን ለማድረግ ስንሞክር እየተጓዝንበት የምንገኘው መንገድ የዓለም መንገድ ይሆናል እንጂ የኢየሱስ መንገድ አይደለም። ይህ ፈተና በቤተክርስቲያን አባቶች ላይም እንዲሁ ሊከሰት ይችላል። “ይህ ኢፍትሐዊነት ነው ፣ ይህ ውርደት ነው ፣ ልታገሰው አልችልም”። ነገር ግን እረኛው ይህንን መንገድ የማይከተል ከሆነ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር አይደለም ።  ያለ ውርደት ትሁት ሊኮን በፍጹም አይቻልም።

07 February 2020, 15:47
ሁሉንም ያንብቡ >