ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ክርስቲያኖች ተጨባጭ በሆነ መልኩ ሕይወታቸውን ሊገልጹ ይገባል” አሉ።

የእግዚአብሔር ትዕዛዛት "ተጨባጭ የሆኑ ትዕዛዛት ናቸው" ስለዚህም “ተጨባጭ የሆነ ሕይወት መኖር ደግሞ” የክርስትና ሕይወት አንዱ "መስፈርት" ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 29/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የእግዚኣብሔር ልጅ የሆነው “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ከሴት ተወልዱዋል፣ ተጨባጭ የሆነ ሕይወት ኖሯል፣ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ሞቱዋል፣ ስለዚህም እኛም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ተጨባጭ በሆነ መልኩ እንድንወድ ይጠይቀናል” ብለዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የእግዚአብሔር ትዕዛዛት "ተጨባጭ የሆኑ ትዕዛዛት ናቸው" ስለዚህም “ተጨባጭ የሆነ ሕይወት መኖር ደግሞ” የክርስትና ሕይወት አንዱ "መስፈርት" ነው ብለዋል።
ቅዱሳን በሙሉ “ተጨባጭ የሆነ ሕይወት ኑረው ማለፋቸውን” በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛም በዚህ መንገድ ላይ እንድንጓዝ እና ጌታ የሚፈልገውን ተጨባጭ የሆኑ ነገሮችን መገንዘብ እንደ ሚገባን ቅዱሳን እንደ ሚመክሩን” የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም በእለቱ (ከ1ኛው ዮሐ. 3፡22-4፡6) ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ከተጠቀሰው በሐሰት እና በቅዠት መንፈስ ከተሞሉ ሐሰተኛ ተነብያት አቋም በተቃራኒው የሚገኝ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
እግዚኣብሔር እና ባልንጀሮቻችን
እኛ ከጌታ ለመቀበል የምንፈልገው ነገር ሁሉ እኛ የእርሱን ትዕዛዛት ከመጠበቅ እና እኛ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር በተግባር ከመፈጸም ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ረገድ በቀዳሚነት የሚቀመጠው ጉዳይ እግዚኣብሔር የእኛን ሥጋ ለብሶ እንደ እኛ ሰው የሆነውን፣ ተጨባጭ በሆነ መንገድ በተገለጸው፣ በማርያም ማሕጸን ውስጥ በነበረው፣ በቤተልሔም በተወለደው፣ እንደ ማነኛውም ሕጻን ባደገው፣ ወደ ግብፅ በተሰደደው፣ ወደ ናዝሬት ተመልሶ በሄደው፣ በዚያው ባደገው እና ስብከተ ወንጌልን ባስፋፋው በኢየሱስ ማመን ይጠበቅብናል ይህም የመጀመርያው መስፈርት ነው” ብለዋል።
የክርስትና ሕይወት መገለጫ ባህሪያት ከሆኑት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በሁለተኛነት የሚቀመጠው እና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ኢየሱስ እንድንፈጽመው የሚጠይቀን መስፍረት እርስ በእርሳችን መዋደድ እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ፍቅር ተጨባጭ በሆነ መልኩ እንጂ እንዲሁ ለይስሙላ በሚደረጉ ተግባሮች መገለጽ እንደ ሌለበት ገልጸው ፍቅር መገለጽ የሚገባው “እወድኃለሁ/ሻለሁ በማለት እንዲሁ በቀላል ሽንገላ ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ በሆነ መልኩ ሊገለጽ ይገባዋል ብለዋል።
“ፍቅር ተጨባጭ በሆኑ ነገሮች ሊገለጽ እንደ ሚገባ አጽኖት ሰጥተው” የገለጹት ቅዱስነታቸው “የእግዚኣብሔር ትዕዛዛት ተጨባጭ የሆኑ ትዕዛዛት በመሆናቸው የተነሳ በዚህ ምክንያት የአንድ ክርስቲያን መመዘኛ ባህሪይ ሊሆን የሚገባው ደግሞ ተጨባጭ በሆነ መልኩ የእግዚኣብሔርን ትዕዛዛት በትግባር ላይ ማዋል ነው” ብለዋል።
ነቅቶ መጠበቅ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በመቀጠል እንደ ገለጹት እምነታችንን ተጨባጭ በሆነ መልኩ ከመግለጽ ባሻገር የበጎ አድራጎት ተግባራትን ተጨባጭ በሆነ መልኩ እንድናከናውን ኢየሱስ እንደ ሚጠይቀን የገለጹት ቅዱስነታቸው ከዚህም ባሻገር በመሄድ የክርስትና ሕይወታችንን መንፈሳዊ በሆነ መልኩ በመኖር ነቅተን መጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል።
በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት በእያንዳንዱ ቀን ማብቂያ ላይ ሕሊናችንን በመመርመር በእለቱ ምን ዓይነት ኃጢኣቶችን እንደ ፈጸምን በመገምገም፣ በልባችን ውስጥ ምን እንደ ተፈጠረ በመገንዘብ እኛ ክርስቲያኖች ኃጢያት እንድንሰራ የሚያደርጉን ተግባራት ምን እንደ ሆኑ ለይተን በማወቅ፣ ከእነዚህ ክፉ ነገሮች ለመላቀቅ ያስችለን ዘንድ በእግዚኣብሔር አነሳሽነት እና እርዳታ በማስተዋል ጥበብ የተሞሉ ውሳኔዎችን በማድረግ ሕይወታችንን ማስተካከል ይገባናል ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

07 January 2019, 14:48
ሁሉንም ያንብቡ >