ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ካህናት እንደ ዶን ቦስኮ ደስተኞች መሆን ይኖርባቸዋል” አሉ!

“ካህናት እውነታን በሰው ዓይን ብቻ መመልከት አይኖርባቸውም፣ ወይም እውነታን በእግዚኣብሔር ዓይን ብቻ መመልከትም ተገቢ አይሆንም”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ዛሬ በጥር 23/2011 ዓ.ም መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ የተዘክረውን የቅዱስ ዶን ቦስኮ አመታዊ በዓለ ከግምት ባስገባ መልኩ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ካህናት ባለስልጣኖች አይደሉም፣ ነገር ግን ሕዝቡን በሰብዓዊ እና አምላካዊ በሆነ እይታ በመመልከት ካህናት እንደ ዶን ቦስኮ ደስተኞች መሆን ይኖርባቸዋል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ዶን ቦስኮ በሕይወት ዘመኑ እውነታን በአባትዊ ልብ እና በመንፈሳዊ ዓይን ተመልክቶ ነበር፣ ይህ አመለካከቱ ደግሞ ለሰዎች የሕይወት መንገድ አመላክቶ ነበር፣ በጎዳና ላይ የነበሩ ታዳጊ ወጣቶችን በተመለከተበት ወቅት ልቡ በርኅራኄ ተሞልቶ እነዚህን ታዳጊ ወጣቶች ከጎዳና ላይ ሕይወት እንዴት ማላቀቅ እንደ ሚገባው ማሰብ ጀመረ፣ ከታዳጊ ወጣቶች ጋር አብሮ ተጉዙዋል፣ ሐዘናቸውን በመካፈል እንደ እነርሱ አልቅሶ ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ካህናትም የዶን ቦስኮን አብነት መከተል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

“ማዕረገ ክህነት በተቀበልኩበት ቀን በግብርና ሥራ ላይ ተሰማርታ የነበርች በጣም ትሁት የነበረችው እናቴ፣ ምንም ዓይነት የነገረ መለኮት ትምህርት ያልቀሰመቺው እናቴ ወደ እኔ መጥታ ‘ከዛሬ ጀምሮ መሰቃየት ትጀምራለህ’” በማለት መናገራቸውን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እናቴ ይህንን በመናገራቸው ስለእውነታው አጽኖት ሰጥተው ለማናገር በማሰብ እና ልጇ ምንም ዓይነት ስቃይ የሌለበት ሕይወት ነው ብሎ ሕይወቱን እንዳያስብ ለማድረግ አስባ የተጠቀመችሁ ቃል እንደ ሆነ” ገልጸው ምንም ዓይነት ስቃይ የሌለበት ሕይወት በራሱ ጥሩ ዓይነት ሕይወት እንዳልሆነ ለማስገንዘብ አስባ የተናገረቺው እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

“ሰለዚህ የካህን ሥቃይ ካህኑ ጥሩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ምልክት ነው፣ ነገር ግን ይህ ‘ፉከራ’ ሊሆን ግን አይገባም፣ በእውነትና በእግዚአብሔር ዓይኖች ውስጥ እውነታን ለመመልከት ድፍረት ያገኘውን ዶን ቦስኮን መሆን ማለት ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ዶን ቦስኮ የነበረበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ድህነት የሰፈነበት፣ በጣም ብዙ የሚባሉ ታዳጊ ወጣቶች በጎዳና ላይ ተጥለው የሚገኙበት ወቅት እንደ ነበረ” አስታውሰው እርሱ ግን ይህንን እውነታ “እያየ እንዳላየ ሆኖ ማለፍ እንዳልፈለገ” ገልጸው ይህንን አሰቃቂ ሁኔታ “አባታዊ የሆነ ልብ በመላበስ እና በእግዚኣብሔር መንፈስ በመታገዝ” የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ አድርጎ ማለፉን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“ሁለት በጣም የተራራቁ የሚመስሉ ነገር ግን ሁለቱም አንድ ዓይነት ግብ ያላቸው እውነታዎች አሉ፣ እነዚህም በሰው ዓይን እውነታን መመልከት እና እውነታን በአምላክ ዓይን መመልከት፣ እነዚህ ሐሳቦች በጣም የሚራራቁ ሐሳቦች ወይም እውነታዎች ቢሆኑም ቅሉ ነገር ግን አንድ እውነታን ያሳያሉ፣ ይህም ማለት ቅዱስ ቁርባን ወደ ሚቀመጥበት መንበረ ታቦት መመልከት ማለት ነው፣ ይህንን ምልከታ በምናደርግበት ወቅት ደግሞ ኢየሱስ መንገዱን አጥርቶ ያሳየናል” በማለት ጨምረው ገለጸዋል።

“ካህናት እውነታን በሰው ዓይን ብቻ መመልከት አይኖርባቸውም፣ ወይም እውነታን በእግዚኣብሔር ዓይን ብቻ መመልከትም ተገቢ አይሆንም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን የቅዱስ ዶን ቦስኮን አብነት በመከተል “ካህናት እውነታን በሰው እና በእግዚኣብሔር ዓይን ወይም ምልከታ በተቀናጀ መልኩ በማየት በጅግር ላይ ያሉ ሰዎችን በሰብዐዊነት እና በመንፈሳዊነት ለመርዳት የተቻለቸውን ሁሉ መጣር  ይኖርባቸዋል” ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

31 January 2019, 14:08
ሁሉንም ያንብቡ >