ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት፣  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የስብከተ ገና ወቅት የሰላም ልዑል ሰላሙን እንዲሰጥን የምንለምንበት ወቅት ነው

የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የሚከበረበትን የገና በዓለ በደመቀ ሁኔታ በታላቅ መንፈሳዊነት ለማክበር ይቻል ዘንድ ዝግጅት የሚደረግበት የስብከተ ገና ሳምንት በኅዳር 23/2011 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነስኮስ በዛረው እለት ማለትም በኅዳር 25/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የስብከተ ገና ወቅት በሕይወታችን፣ በቤተሰባችን እና በዓለም ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን የምናደርግበት ወቅት ነው ብለዋል በምንም ዓይነት ሁኔታ ጦርነቶችን ለማካሄድ ምክንያት መፍጠር ግን አይገባም ብለዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በሕይወታችን፣ በቤተስባችን እና ብሎም በዓለማችን ሰላም ይስፈን ዘንድ የተቻለንን በማድረግ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወልደበትን የገና ቀን በዚሁ ፣መለኩ ለማክበር መዘጋጀት ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው ሰላምን ለማስፈን መሞከር በራሱ የእግዚኣብሔርን ባሕሪ እንደ መላበስ ይቆጠራል ይህንን ተግባር በታላቅ ትህትና ማከናወን ይገባናል ብለዋል።

በእለቱ በቀዳሚነት ከትንቢተ ኢሳያስ ከምዕራፍ 11፡1-10 እና ከሉቃስ ወንጌል 10፡21-24 ላይ ተወስዶ በተነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መስረቱን ባድርገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ኢሳያስ በትንቢቱ  “ጌታ በሚመጣበት ዘመን ስለሚከሰቱት ነገሮች አመላክቶ እንደ ነበረ ገለጸው “ጌታ ሰላሙን ይዞ እንደ ሚመጣ፣ ሁሉም ነገር በሰላም እንደ ሚከናወን” ተስፋ ሰጥቶ እንደ ነበረ ኢሳያስ በትንቢቱ መግለጹን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ኢሳይያስ "ውስጣዊ ትርጉም ያላቸውን ተምሳሌታዊ ምስሎችን" የተጠቀመ ቢመስልም ነገር ግን ውብ በሆነ አገላለጽ "ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል” ብሎ ገልጾ እንደ ነበሩ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህ ማለት ኢየሱስ የሰዎችን ሕይወት እና ታሪክ በመለወጥ ሰላምን የሚሰጥ እና ይህንንም ሰላም የሚያመጣልን በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ ገለጸው "የሰላም ልዑል" ተብሎ የተጠራው ለዚህ ምክንያት ነው ብለዋል።

የሰላሙ ልዑል ለነፍሳችን ሰላምን እንዲሰጥ እንጠይቀው

በዚህም ምክንያት የስብከተ ገና ወቅት “ይህንን የሰላም ልዑል የሆነውን አምላክ የምንጠባበቅበት ወቅት እንደ ሆነ” የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ራሳችንን የማረጋጊይ ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል። ይህ መረጋጋት ከሁሉም በላይ እና ከሁሉ ቀድሞ ሊጀምር የሚገባው ራሳችንን በማረጋጋት ሊሆን እንደ ሚገባ በስበከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በዚህም መሰረት ነብሳችንን ከማረጋጋት መጀመር እንደሚገባ ጨምረው ገለጸዋል። እኛ ብዙ ጊዜ ሰላም በማጣታችን የተነሳ ደህና አይደለንም "በጭንቀት ውስጥ ገብትን ነው እየኖርን የምንገኘው፣ ይህም በከፍተኛ ጭንቀት እንድንገባ በማድረግ ያለ ተስፋ እንድንኖር ያደርገናል ብለዋል። በዚህ ረገድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሚያቀርብልን የመጀመርያው ጥያቄ ነፍስህ እንዴት ናት? ሰላም አላት ወይ? ብሎ እንደ ሚጠይቀን በስብከታቸው ያስታወሱስት ቅዱስነታቸው ሰላም በሕይወታችን ውስጥ የጎደለ ከሆነ የሰላም ልዑል የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን ይሰጠን ዘንድ ልንማጸነው ይገባል ብለዋል። ብዙን ጊዜ የሌሎችን ሕይወት መመልክት እንደ ሚቀናን የገልጹት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በቀዳሚነት የራሳችንን ሕይወት መመለከት እና መፈተሽ የጎደለ ነገር ካለ ደግሞ እርሱ እንዲሞላው መጠይቀ ይኖርብናል ብለዋል።

ቤተሰቡን ማረጋጋት

በመቀጠል ቤታችንን እና ቤተሰባችንን ማረጋጋት ያስፈልጋል፣ በቤተሰብ ውስጥ ብዙ ሐዘን፣ ብዙ ትግል፣ ይብዛም ይነስም ትልቅ ይሁን ትንሽ ጦርነቶች፣ እና ክርክሮች” ብዙን ጊዜ እንደ ሚንጸባረቁ በመግለጽ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ይረጋጉ ዘንድ በቤታቸውም ሰላም ይሰፍን ዘንድ ስለእነርሱ መጸለይ አስፈላጊ እንደ ሆነ ገለጸው የሚለያዩንን የጥል ግድግዳዎችን በመናድ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉንን ድልድዮች መገንባት ይኖርብናል ብለዋል።

በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ የሰላም ልዑል የሆነው ጌታ ለዓለማችን ሰላም ይሰጥ ዘንድ ልንልመነው፣ ልንጠይቀውም ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ከፍተኛ ጦርነት በመካሄድ ላይ ባሉባቸው ሀገራት ውስጥ፣ ከፍተኛ ውድመት በመድረስ ላይ በሚገኝባቸው ሀገራት ውስጥ፣ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ በሚታይባቸው ሀገራት ውስጥ፣ ከፍተኝ የሆነ የሐብት ብዝበዛ በሚታይባቸው ሀገራት ውስጥ ሰላም ሊኖር ሰለማይችል በዓለም ሁሉ ላይ ሰላም እዲወርድ የሰላሙን ልዑል ልንማጸነው ይገባል ብለዋል።

 

04 December 2018, 14:32
ሁሉንም ያንብቡ >