ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የክርስትናን ሕይወት ከዓለም ሕይወት ጋር አስታርቆ መኖር አይቻልም!”

በእኛ በክርስትና ሕይወት ሁኔታ ውስጥ እንኳን ሳይቀር የአረማዊያን ሕይወት ይንጸባረቃል። እኛ እንደ አንድ ክርስቲያን ነው ወይ የምንኖረው? አዎን! የመስለኛል እንደ እዚያ ነው የምንኖረው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሕዳር 20/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት እለቱ ከሉቃስ ወንጌል 21፡20-28 ላይ እና ከዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 18፡1-3, 19፡1-3,9 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ውስጥ በተጠቀሱት ውደቀት እና ተስፋ፣ ሽንፈት እና ድልን በሚያመልክቱ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ባደረገው ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “የክርስትናን ሕይወት ከዓለም ሕይወት ጋር አስታርቆ መኖር አይቻልም” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዛሬው (ሕዳር 20/2011 ዓ.ም ) ቀን ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበቡልን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት የዓለምን ፍጻሜ እና አንድ ቀን በእያንዳንዳችን ላይ የሚደርሰውን የፍጻሜ ቀን የሚገልጹ እንደ ሆነ በስብከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በቅድሚያ ከዮሐንስ ራእይ ከምዕራፍ 18፣19 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና "የቅንጦት፣ በራስ ኃይል የመተማመን፣ የእዚህ ዓለም ጉልበት እና ኃይል መገለጫ”   ታላቅ እና ውብ የነበረችው፣ የሥልጣኔ ሁሉ ተምሳሌት የሆነችው ባቢሎን መፈራረሷን የሚገልጽ ታሪክ እንመለከታለን ብለዋል። በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰው ደግሞ ዛሬ ከሉቃስ ወንጌል (21፡20-28) ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የተጠቀሰው የቅድስትቷ የእየሩሳሌም ውድቀት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የባቢሎን ውድቀት የተከሰተው በብልሹ ተግባሯ ምክንያት ነው!

“ፍርድ ቀን በብርቱ የድል አድርጊዎች ድምፅ የተነሳ ታላቂቱ ባቢሎን ትወድቃላች። በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችሁ ታላቂቱ ጋለሞታ ‘የመጥፎ መንፍስ ማደሪያ እና መሸሸጊያ የሆነችው ባቢሎን’ ጌታ ስለ ፈረደባት፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርጉም በሆኑ ምግባሮቿ የተነሳ የእርሷ ወገኖች ደስታ ሁሉ ሐሰት ሆነው ይታያሉ፣ አወዳደቋም በጣም የከፋ ስለሚሆን ማንም መልሶ ሊያገኛት አይችልም ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች። ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።  በገና የሚመቱና መዝሙር የሚዘምሩ ሰዎች ድምፅ፣ እንቢልታና መለከትንም የሚነፉ ሰዎች ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንች ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ ምንም ዓይነት ጥሩ የሆኑ ግብዣዎች በአንች ውስጥ ከቶ አይደርገም፣ ዕደ ጥበበኛ የሆነ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ብዙ ባለትዳሮች በውስጥሽ ይኖራሉ፣ ነገር ግን በመካከላቸው ፍቅር አይኖርም፣ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና። ይህ ውደቀት የጀመረው ከራስሽ ከውስጥሽ ነው፣ ውድቀትሽ የሚጠናቀቀው ጌታ “በቃ” ስልሽ ብቻ ነው። ጌታ በቃ የሚልበት አንድ ቀን ይመጣል “የዚህ ዓለም አትሁኑ የሚለበት ቀን ይመጣል”። ይህም በራሱ የሚተማመን ኩራተኛ፣ ራሱ ለራሱ በቂ እንደ ሆነ አድርጎ የሚያስብ፣ አምባገነን የሆነ ስልጣኔ የሚደርስበት የመጨረሻው ሰቆቃ ነው።

እየሩሳሌም ለአረማዊያን በሯን ከፍታለች

“እየሩሳሌም በሌላ ዓይነት የስነ-ምግባር ብልሹነት የተነሳ ትወድቃላች "ይህ የሚከሰተው ደግሞ በልጁ አማካይነት ለተገለጸው የእግዚኣብሔር ፍቅር እውቅና ባለመስጠቷ የተነሳ እንደ ሆነ” በመጥቀስ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይችህ ቅድስት የሆነች ከተማ “በአረማዊያን ትረገጣለች” ይህም የምሆንበት ምክንያት ጌታ እንደ ተናገረው የልቧን በር ለአረማዊያን በመክፈቷ የተነሳ ነው ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

በእኛ በክርስትና ሕይወት ሁኔታ ውስጥ እንኳን ሳይቀር የአረማዊያን ሕይወት ይንጸባረቃል። እኛ እንደ አንድ ክርስቲያን ነው ወይ የምንኖረው? አዎን! የመስለኛል እንደ እዚያ ነው የምንኖረው። በእውነት ከተመለከትነው ግን ሕይወታችንን እየኖርን ያለነው እንደ አንደ አረማዊያን ነው፣ እነዚህ ነገሮች ሲከሰቱ አማላይ በሆነው የባቢሎን ዓይነት ሕይወት ውስጥ ገብተን መኖር ስንጀምር እየሩሳሌም እንደ ባቢሎን መኖር ትጀምራለች። ማድረግ የማይገባንን ነገሮች ለመስራት እንሞክራለን። በሁለቱም ላይ ተፈርዶባቸዋል። አንተ ክርስቲያን ነህ ወይ? አንችስ ክርስቲያን ነሽ ወይ? ከሆንክ/ከሆንሽ እንደ ክርስትያን ኑሩ። ወሃን ከዜይታ ጋር ማቀላቀል አይችላም። ሁል ጊዜም ቢሆን ውሃ ከዜይት የተለየ ነው። በራሱ ጊዜ እርስ በእርሱ የተቃራነ ስልጣኔ መጨረሻው ክርስትያን ነኝ የሚል እና በተመሳሳይ ጊዜም አረማዊ ነኝ የሚል ይሆናል።

በጌታ ተስፋ የሚያደርጉ ሁሉ ደህንነትን ያገኛሉ

በወቅቱ በተነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ውስጥ ፍርድ የተፈረደባቸውን ሁለቱን ማለትም የባቢሎን እና የእየሩሳሌም ከተማን በተመለከተ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከተፈረደባቸው እና ከፈራረሱ በኋላ በመቀጠል የጌታ ድምጽ እንደ ሚሰማ በመገለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የሚያሳየው ከጥፋት በኋላ ደህንነት እንደ ሚመጣ ያሳያል ብለው “መልኣኩም እንዲ አለ። ኑ! ወደ ሰርጉ የተጠሩ ተጋባዦች ሁሉ የተባረኩ ናቸው! በማለቱ የተነሳ የትልቅ እና የእውነተኛ ግብዣ” ሰዓት ይሆናል ብለዋል።

 

ሁሉም ነገር ይጠፋል፣ ነገር ግን ትሁት የሆኑ ሁሉ ይኖራሉ!

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ እንደ ባቢሎን ዓይነት ሕይወት በመኖር ላይ የሚገኙት ኃያላን መንግሥታትን ለምሳሌም ባለፈው ክፍለ ዘመን እንዳየነው ሁሉም ይወድቃሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት እንደ ባቢሎን በመኖር ላይ የሚገኙ የዓለማችን ሀገራት በተመሳሳይ መልኩ እንደ ባቢሎን እንደ ሚወድቁ ገልጸው፣ እኛም አረማዊያን በሚጓዙበት ጎዳና ላይ መጓዛችንን ከቀጠልን ሕይወታች የሚጠናቀቀው ባቢሎን በወደቀችበት ዓይነት መንገድ ሊሆን እንደ ሚችል ቅዱስነታቸው አሳስበዋል። ተስፋቸውን በጌታ ላይ ያደርጉ የዋሕ ሰዎች ግን በሕይወት እንደ ሚኖሩ የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም ምክንያት እኛም አረማዊያን በሚጓዙበት መንገድ ላይ ሳይሆን በጌታ ላይ እምነታችንን እና ተስፋችንን በመጣል ሕይወታችንን በትሕትና እና በየዋህነት በመኖር የእርሱ ሕይወት ተካፋዮች መሆን ይኖርብናል ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

29 November 2018, 16:06
ሁሉንም ያንብቡ >