2018.10.08 Papa Francesco Messa Santa Marta 2018.10.08 Papa Francesco Messa Santa Marta 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ምዕመናን ከአገልጋዮቻቸው ጋር ሆነው የክርስትናን ግዴታን መወጣት አለባቸው”።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምዕመናንና አገልጋዮቻቸው ክርስትና የሚጠይቀውን ግዴታ ለመወጣት ፍርሃት እንዳይዛቸው አሳሰቡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ጠዋት ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው በቅድስት ማርታ ጸሎት ቤታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ፣ መስዋዕተ ቅዳሴውን ለተካፈሉት ካህናት ደናግልና ምዕመናን ባሰሙት ስብከተ ወንጌል እንዳስረዱት ምዕመናንና አገልጋዮቻቸው  የክርስትናን ግዴታ ለመፈጸም እንዳፈሩ አሳሰቡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በዚህ ማሳሰቢታቸው ምዕመናንና አገልጋዮቻቸው ክርስትና የሚጠይቀውን ግዴታ ለመወጣት ወደ ኋላ ሳይሉ፣ ፍርሃትም ሳይዛቸው ለሌሎች ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ወደ ኋላ ሳይሉ ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በዛሬው ዕለት ከሉቃስ ወንጌል ምዕ. 10. 25-37 በተነበበው የወንጌል ክፍል ላይ በማስተንተን ባሰሙት ስብከት ኢየሱስ ክርስቶስ በሙሴ የሕግ መምህራን በኩል፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠየቁትን በማስታወስ የርህሩሁ ሳምራዊ ምሳሌን በመጥቀስ ባልንጀሮቻችንን መውደድ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በሉቃስ ወንጌል በምዕ. 10 ከ25-37 እንደተጻፈው የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ጌታ አምላክን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሃይልህና በፍጹም ሃሳብህ ውደድ የሚለውን ጠቅሰው ጌታ አምላክን በዚህ መንገድ ከወደድነው ለባልንጀሮቻችን ማድረግ ያለብን ምን እንደሆነ በሚገባ እናውቃለን ብለዋል። ከሕግ አዋቂዎች መካከል ኢየሱስን ሊፈትኑ ፈልገው፣ ባልንጀራዬ ማነው ለሚለው ጥያቄ ኢየሱስ ያቀረበውን የደጉ ሳምራዊ ምሳሌን በማስታወስ ባቀረቡት አስታንትኖ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳስገነዘቡት የእኛን እገዛ ፈልገው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለሚጮሁ፣ ምንም ዓይነት ምክንያት ሳናቀርብ በቅድሚያ የባልንጀራን ጥያቄ መመለስ፣ ከገባበት ችግር እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ ማገዝ፣ መታደግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

እኛ ማከናወን ያለብንን መልካም ሥራን ለሌሎች መተው ወይም አሳልፎ መስጠት ትክክል እንዳልሆነ፣ እንዲሁ የስም ክርስቲያን መሆን እንደማይገባ ቅዱስነታቸው አሳስበው እግዚአብሔር የሚያሳየንን ድንቅ ነገር ለማየት እውነተኛ የፍቅር ዓይንና ልብ እንዲኖረን ያስፈልጋል ብለዋል። ለሌሎች መልካምን አደርጋለሁ፣ በልቤም ክፋት የለኝም፣ እንዲያው ራሴን ከሌሎች ጋር ሳወዳድር ከብዙ ክርስቲያኖች የተሻልኩ ነኝ ብለው የሚያስቡ በርካታ ክርስቲያኖች መኖራቸውን የገለጹት ርዕሠ ሊቃነ ፍራንችስኮስ፣ እነዚህ ግብዝ ክርስቲያኖች እግዚ አብሔር ሊገልጥላቸው የሚፈልገውን ታላቅ ነገር ለመመልከት አይናቸውንም ሆነ ልባቸውን ዝግ ያድረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።

ኢየሱስና የመሠረታት ቤተክርስቲያን፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በዕለቱ በተነበበው የወንጌል ክፍል ያደረጉትን አስተንትኖ በመቀጠል፣ መላው ምዕመናንና አገልጋዮች በሙሉ፣ በእርግጥም የክርስትና ሕይወት ጥሪያቸውንን በእውነት እንኖራለን ወይ ብለን ራስን መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል።                       

08 October 2018, 18:01
ሁሉንም ያንብቡ >