ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ክርስቲያን ለጠላቱ ይጸልያል፣ ጠላቱንም ይወዳል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ክርስቲያን ለጠላቱ ይጸልያል፣ ጠላቱንም ይወዳል” ማለታቸው ተገለጸ።
ቅዱስነታቸው ይህንን ቀደም ሲል የተጠቀሰውን የተናገሩት በዛሬው እለት ማለትም በሰኔ 12/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ጠላቶቻችሁን ውደዱ ለሚያሳድዱዋችሁ ሰውች ጸልዩ” የሚለው የጽሐፍ ቅዱስ ቃል እግዚኣብሔር ቅዱስ እንደ ሆነ ሁሉ እኛም ቅዱስ እንድንሆን የሚረዳን በመሆኑ የተነሳ ክርስቲያኖች ይህንን ሊከተሉ የገባል ብለዋል።
የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ ቫቲካን
በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5፡43 ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተመርኩዘው እኛን ሊያጠፉን ለሚፈልጉ ጠላቶቻችን በሙሉ ይቅርታን ማድረግ እና ጸሎት መጸለይ እንደ ሚገባ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁሉን አቀፍ የሆነ ፍቅር ያለውን የሰማያዊ አባታችን ጥሪ ተከትለን ለሰው ልጆች ከፍተኛ ተግዳሮት የሆነውን ጠላትን የመውደድ መንፈስ ማዳበር እንደ ሚገብ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ይህንን ጠላቶቻችንን መውደድ የሚያስችለን ጸጋ ይሰጠን ዘንድ ልንጠይቀው የገባል ብለዋል።
ይቅር ለመባል በቅድሚያ ይቅር እንበል
በእየዕለቱ አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት በምንጸልይበት ወቅት “እኛን የበደሉንን ይቅር እንደ ምንል በደላችንን ይቀር በለን” የሚለውን ጸሎት እንደ ምንጸልይ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ምክንያት ጠላቶቻችንን ይቅር ማለት እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ይህ ቀላል የሚባል ነገር ባይሆንም ቅሉ እኛ ይቅር እንደ ምንል ሁሉ ሌሎችም ይቅርታ እንዲያደርጉልን ልንጠይቅ የገባል ብለዋል። በተመሳሳይ መልኩም ለሌሎች ሰዎች በተለይም በእኛ ላይ ብዙን ጊዜ ችግር ለሚያደርሱብን፣ ለሚጠሉን እና ወደ ፈተና ውስጥ ለሚከቱን ሰዎች ሳይቀር ምንም እንኳን ከባድ የሚባል ነገር ቢሆንም መጸለይ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም የአንድ ክርስቲያን የመገለጫ ባሕሪይ ሆኖ ሊቀጥል እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .
ከኢየሱስ እና ሰማዕታት ከነበራቸው ስነ-አመክንዮ እንማር
ኢየሱስ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት በመጨረሻ ሰዓት ላይ እርሱን ስያሰቃዩ የነበሩ ሰዎችን “ጌታ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ያደርገውን የማጠቃለያ ጸሎት ሁኔታውን መረዳት በጣም አስቸጋሪ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ግን ይህንን ያቅርታ አድርጎላቸው ነበር ብለዋል። በተመሳሳይ መልኩም ሰመዕቱ እስጢፋኖስ የኢየሱስን ፈለገ በመከተል በድንጋይ ይወግሩት ለነበሩ ሰዎች ይቅርታ እንዳደረገላቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .
በእዚህም ምክንያት ይህንን ታላቅ የክርስቲያኖች ምስጢር የሆነውን ነገር ለመረዳት እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንጸልይ ይግባል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁሉንም ነገር በእኩልነት በክፉዎች ላይ ይሁን በደጎች ላይ የሚያዘንበው ሰማያዊ አባታችን ቅዱስ እንደ ሆነ እኛም ቅዱሱ እንሆን ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንለምነው ይገባል ብለዋል።
ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት ተስፋ አደርጋለሁ እኛ እያንዳንዳችን ጠላቶች ይኑሩናል ብዬ አስባለሁ፣ ስለጠላቶቻችን ማሰብ ጥሩ የሆነ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርገን እንደ ሚችል የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .