ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 04/10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 04/10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© VATICANMEDIA S.S. Francesco - Messa Domus Sanctae Marthae 11-01-2018)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ..መንፈስ ቅድስ የስብከተ ወንጌል ዋነኛው አጋዥ ነው

ኢየሱስ እኛን ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ብቻችንን አይልከንም፣ በፍጹም እንዲ አያደርግም! ነገር ግን የሚልከን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ለሚሰበሰቡ ቀሳውስት፣ ደናግልና እና ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት በሰኔ 04/2010 ዓ.ም በአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር የላቲን የስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ መሰረት የቅዱስ ባርናባስ አመታዊ በዓል በተከበረበት ወቅት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በማንኛውም ስብከተ ወንጌልን በማሰራጨት ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ “ተዋናይ”  መሆኑን ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

የእዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

ቅድሱ ወንጌልን የማብሰር ሂደት ከሌሎች የመገናኛ ዓይነቶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጉዳይ አለምሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ ወንጌልን የማስበር ሂደት በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ የሚከናወን በመሆኑ የተነሳ ልብን የመቀየር ኃይል አለው ብለዋል። አንዳንድ ጊዜ በጣም ምርጥ የሚባሉ ሐዋሪያዊ ተግባራትን የማከናወኛ እቅዶች ቢኖሩም እንኳን እነዚህ ምርጥ የተባሉ ሐዋሪያዊ እቅዶች በራሳቸው ልብን የመለወጥ ኃይል ወይም ብቃት እንደ ሌላቸው በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ እቅዶች በራሳቸው ወድ ግብ እንድናመራ የሚያደጉን ናቸው እንጂ በራሳቸው ወደ ግብ መስመር መውሰጃ መሳሪያዎች ግን አይደሉም ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን አሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“ኢየሱስ እኛን ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ብቻችንን አይልከንም፣ በፍጹም እንዲ አያደርግም! ነገር ግን የሚልከን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ነው እንጂ። ይህም የብርታታችን ምንጭ ነው። ከአንድ ብርቱ ወንጌላዊ በስተጀርባ ያለው የሰው ልጅ ድፍረት አይደለም። በፍጹም እንዲ አይደለም፣ ብርታትን የሚሰጥን እና ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚያደርገን መንፈስ ቅዱስ ነው።”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አገልግሎት ሁለተኛው ቅዱስ ወንጌልን የማብሰር ሂደት ገጽታ አድርገው የሚመለከቱ ሲሆን እንዲያውም ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ "አንድ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎትን ወይም ስኬትን የሚፈልግ ከሆነ ይህ ሰው ቅዱስ ወንጌልን ምንም እንደማያውቅ የሚያሳይ ምልክት ነው፣ የሚያዝ ሰው በራሱ የሚያገለግል ሰው ሊሆን የገባዋል” የሚል ከፍተኛ አቋም እንዳላቸው ይታወቃል።

ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“መልካም የሆኑ ነገሮችን መናገር እንችል ይሆናል፣ አገልግሎት ካልታከለበት ግን ስብከተ ወንጌል ነው ልንል በፍጹም አንችልም። ስብከተ ወንጌልን ሊመስል ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን አይደለም፣ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የጌታን እውነታዎች እና የጌታን ሕይወት ለማወጅ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት የሚመራን፣ ነገር ግን በተጨማሪም ትናንሽ በሚባሉ አገልግሎቶች ሳይቀር ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን እንድናገለግል ያደርገናል። ለማገልገል የተላኩ ወንጌላዊያን የሚባሉ ሰዎች በሌሎች ሰዎች ሲገለገሉ ማየት በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው። የስብከተ ወንጌል ንጉሥ ይሆናሉ. . . ይህም በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው።”

ወንጌል በነፃ የሚሰጥ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በነጻ የሚሰጥ አገልግሎት መሆኑ ደግሞ የወንጌላዊነት ሦስተኛው የመገለጫ ገጽታ እንደ ሆነ የጠቀሱ ሲሆን ምክንያቱም ማንም ቢሆን በራሱ ብርታ ታግዞ የዳነ ሰው ባለመኖሩ የተነሳ ነው፣ በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ ገለጸው ቅዱስ ወንጌል “ በነጻ የተቀበላችሁትንም በነጻ ስጡ” በማለት እንደ ሚናገር ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

“ሁላችንም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በነጻ ነው የዳነው። ስለዚህ እኛም በነጻ መስጠት ይገባናል። ሐዋሪያዊ ተግባሮችን የሚያከናውኑ ወንጌላዊያን ይህንን የግድ ሊማሩ ይገባል። ሕይወታቸውን በነጻ፣ በአገልግሎት፣ በማብሰር እና በመንፍስ ቅዱስ ዳግም በመወለድ ሊያከናውኑ ይገባል። ግላዊ የሆነ ድኽነታቸው ራሳቸውን ለመንፈስ ቅዱስ እንዲከፍቱ ያስገድዳቸዋል።”

11 June 2018, 13:30
ሁሉንም ያንብቡ >