ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት 10/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት 10/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© Servizio Fotografico L'Osservatore Romano)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “አንድ እረኛ ለስልጣን ጥማት ሊኖረ አይገባም”

“አንድ እረኛ ለስልጣን ያለውን ጥማት ለማርካት ብቻ በማሰብ በእዚህ ላይ ጊዜውን ማባከን የለበትም!”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ፡ “አንድ እረኛ ለስልጣን ያለውን ጥማት ለማርካት ብቻ በማሰብ በእዚህ ላይ ጊዜውን ማባከን የለበትም!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 10/2010 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት መሰረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የላቲን ስረዓተ አምልኮ ደንብ አቆጣጠር መስረት በእለቱ ከዩሐንስ ወንጌል 21፡15-19 ላይ ተወስዶ በተነበበው የወንጌል ክፍል ውስጥ በተጠቀሰው ኢየሱስ ከስምዖን ጴጥሮስ ጋር አድርጎት በነበረው ውይይት ላይ መስረርቱን ያደረገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አንድ እረኛ ለስልጣን ያለውን ጥማት ለማርካት ብቻ በማሰብ በእዚህ ላይ ጊዜውን ማባከን ወይም ማጥፋት የለበትም ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

እረኞች በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደ ሌለባቸው የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ እረኞች  “መውደድ፣ ማሰማራት እና ለመስቀል መዘጋጀት” ይኖርባቸዋል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ሐዋሪያቱን  በእዚሁ አግባብ ብቻ እንዲከተሉት አሳስቦዋቸው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቀደም ሲል እንደ ገለጽነው ቅዱስነታቸው በእለቱ ያደርጉት ስብከት መሰረቱን በዩሐንስ ወንጌል 21፡15-19 ላይ በተጠቀሰው  ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፣ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፤ ከእነዚህ አብልጠህ ትወደኛለህን?” ብሎ በጠየቀበት ጭብጥ ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእዚህ በኢየሱስ እና በስምዖን ጴጥሮስ መካከል በተደረገው የመጨረሻ ውይይት ላይ ተመስርተው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ኢየሱስ ““የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ” በማለት ስምዖን ጴጥሮስን በድሮ ስሙ የጠራበት ምክንያት ስሞን በአዲስ መልክ ኢየሱስን በመከተሉ የተነሳ ኢየሱስ ስሙን ወደ ጴጥሮስ ከመቀየሩ በፊት የነበረውን ጊዜይዊ ድክምቶችን በተለይም ደግሞ  በመጨረሻው ሰዓት ኢየሱስን በመካዱ ይህንንም ክህደቱን ዶሮ ሦስት ጊዜ በጮኸ ጊዜ እንዳስታወሰው የሚገልጸውን የድሮ ቀደም ሲል የነበረውን ሕይወቱን ለማስታወስ ፈልጎ ያደርገው መሆኑን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ለእኛም ቢሆን የቀድሞ ሕይወታችን ምን እንደ ነበረ በሚገባ ማስታወስ እንችል ዘንድ ጥሪ እንደ ሚያደርግልን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም አሁን ከእርሱ ጋር ሆነን በምናደርገው ጉዞ ያገኘናቸውን መልካም የሆኑ ነገሮችን በሚገባ እንድናስታውስ እና እንድንገነዘብ ስለሚረደና በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጴጥሮስ ያቀረበው ጥያቄ ሦስት አመላካች የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አቅፎ መያዙን በመጥቀስ ስብከታቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህም አመላካች ሁኔታዎች “ትወደኛለህን፣ በጎቼን ማሰማራት፣ ተዘጋጅ” የሚሉት ቅድመ ሆኔታዎች እንደ ሆኑ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ፍቅር የሚለው ሰዋስዉ ወይም ቃል አንድ ትክክለኛ የእግዚኣብሔር ልጅ የሆነ ሐዋሪያ ሊላበሰው የሚገባው ባሕሪይ እንደ ሆነ ገለጸው የአንድ ትክክለኛ እረኛ ተግባር በጎችን ማሰማራት እና መንከባከብ በመሆኑ የተነሳ በጎቹን በጥንቃቄ መንካባከብ እንደ ሚገባ ጠቅሰው በእዚህም ረገድ የአንድ ጳጳስ ወይም የአንድ ካህን ተግባር ሊሆን የሚገባው ለበጎቹ መልካም እረኛ መሆን ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

“ውደደኝ፣ አሰማራ እና ተዘጋጅ”፣ ከሁሉም አብልጠህ ውደደኝ፣ እስከ ምትችለው ድረስ ውደደኝ። ጌታ ከእረኞች እና ከእኛ ሁላችን የሚጥብቀ ነገር ይህንን ‘ውደደኝ’ የሚለውን ቃል ነው። ከጌታ ጋር ለመነጋገር ወይም ለመወያየት የሚያስችለን የመጀመሪያው እርምጃ እርሱን መውደድ ነው።

እየሱስን በቆራጥነት የሚከተሉ ሰዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታቸው “ሰማዕት” መሆን ነው መስቀሉን መሸከም መሆኑን በማስታወስ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ማለት እኛ ባልመረጥንበት መንገድ ላይ መጓዝ ማለት እንደ ሆነ ገልጽው ነገር ግን ይህ የአንድ እረኛን የጉዞ አቅጣጫ የሚያመላክት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ ተዘጋጅ፣ ከእዚያ የተሻለ ሌላ ነገር ስለምታገኝ ሁሉንም ነገር ትተህ አዲስ ነገር ሥራ። እነዚህን ነገሮች ከሕይወትህ ውስጥ ለምስወገድ ተዘጋጅ። ይህ ተግባርህ ወደ ውርደት መንገድ ወይም ደግሞ ምን አልባትም ሰማዕት ወደ መሆን እንድታመራ ሊያደርግህ ይችላል። እናም አንተ እረኛ በነበርክበት ቦታ የነበሩ ሰዎች አንትን በማመስገን ስለአንተ መልካም ነገር ይናገራሉ፣ ነገር ግን አንተ ከእዚያ ስፍራ በምትሄድበት ወቅት ከአንተ በኃላ የሚመጣው ሰው የተሻለ ነው ብለው ሰለሚያስቡ ስለአንተ መናገር ያቆማሉ። ምን አልባትም አንተ ያልፈለክበት ሥፍራ ሊወስዱህ ስለሚችሉ ራስህን ለመስቀል አዘጋጅ።  ወደደኝ፣ አስማር፣ ተዘጋጅ። ይህም የአንድ እረኛ የጉዞ መስመር ነው።

በሕይወታችን ውስጥ ከሚገጥሙን አስቸጋሪ እና አደገኛ ፈተናዎች መካከል አንዱ በሌሎች ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም የምናደርገው የራሳችንን ጥቅም እና ፍላጎት ለሟሟላት በምሰብ ብቻ እንደ ሆነ ገልጸዋል። ይህንንም በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል . . .

በራስ ሕይወት ዙሪያ እንጂ በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ አትግባ። አንድ እረኛ ይወዳል፣ ያሰማራል፣ መስቀሉን ለመቀበል ይዘጋጃል እንጂ በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ አይገባም፣ ለስልጣን ያለውን ጥማት ለማርካት በተለይም በቤተክርስቲያን ውስጥ ስልጣን ለማግኘት አይሯሯጥም። ይወዳል፣ ያሰማራል ፈተና ውስጥ ላለምግባት ይዘጋጃል” ።

18 May 2018, 09:23
ሁሉንም ያንብቡ >