የዩክሬይን ህመም፣ ኪሳራ፣ እምነት፣ ተስፋ እና ጥንካሬ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ከዩክሬን የተመለሱት የኢየሱሳውያን ማኅበር የስደተኞች አገልግሎት ዓለም አቀፍ የእርቅ መርሃ ግብር ኃላፊ ዳንኤሌ ቬላ፣ ከዩክሬን ሕዝብ ጎን ለመቆም ቆርጠው ከተነሱት የኦስትሪያ ኢየሱሳዊ ካኅን አባ ክርስቲያን ማርቴ ጋር ተገናኝታለች። የኢየሱሳውያን የስደተኞች አገልግሎት ዓለም አቀፍ የእርቅ መርሃ ግብር ኃላፊ ዳንኤሌ ቬላ፣ በጦርነት ውስጥ ባለች ሀገር ዩክሬይን ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች ባደረጉት ጉብኝት ያዩትን ጥልቅ ስቃይ እና የፅናት ምስክርነት በማስመልከት ከቫቲካን ዜና ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች።
የጥፋት እና የመለያየት ምልክቶች
የኢየሱሳውያን ማኅበር የስደተኞች አገልግሎት ዓለም አቀፍ የእርቅ መርሃ ግብር ኃላፊ ዳንኤሌ ቬላ በግንባር ቀደምትነት የጎበኟቸው አካባቢዎች ሊቪቪ፣ ቼርኒቲስ እና ትራንስካፓቲያ ብቻ ባይሆኑም በሃገሪቱ ውስጥ ጦርነት መኖሩ ሊሰወር እንደማይቻል ገልጻለች።
“እነዚህ የተጠቀሱት አካባቢዎች ደህና እንደሆኑ ተደርገው ይወሰዳሉ” የምትለው ዳንኤሌ ቬላ ነገር ግን አካባቢዎቹ በጥልቅ መጎዳታቸውን ገልጸው፥ በትራንስካፓቲያ ግዛት የሚገኘው የግሪክ ካቶሊክ ሀገረ ስብከት ባልደረባ የሆኑት አቡነ ቴዎዶር ማትሳፑላ፥ “የዩክሬን አካል እንደመሆናችን መጠን የሞቱት ቤተሰቦች እና የወደሙ ቁምስናዎች አባላት ስቃይ ይሰማናል” ብለው፥ በቤተ ክርስቲያናቸው በየቀኑ ማለት በሚቻልበት የወታደሮች የቀብር ሥነ ሥርዓቶች እንዳሉ በግልጽ ተናግረዋል።
ዳንኤሌ ቬላ፥ በሄደችበት ሁሉ የመታሰቢያ ሐውልቶችን፣ የወደቁ ወታደሮች ፎቶግራፎችን፣ በአበቦች እና በግል ማስታወሻዎች ያጌጡ የመቃብር ቦታዎችን፣ በቢጫ እና በሰማያዊ ቀለማት የተሞሉ የቁልፍ መያዣዎችን እና የቤት እንስሳት ምስሎች እንዲሁም የልጆች መጫወቻዎችን ማየቷን ተናግራ “አሁንም ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ማስታወስ እንግዳ ነገር ነው” ስትል ገልጻለች።
በውጊያ ላይ ለሚገኙ ወታደሮች መጨነቅ ግልጽ ነው” ያለችው ዳንኤሌ ቬላ፥ በእያንዳንዱ ውይይት በተለይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሚደረግ ውይይት ላይ ይህ በግልጽ እንደሚታይ አስረድታለች።“በሕይወት በመቆየታቸው የሚያቀርቡት ታላቅ ምስጋና እና ለሀገራቸው እና ለነፃነታቸው ብለው ለሞቱት ሰዎች የሚያቀርቡት ምስጋና እንዲሁም ለወደፊት ሕይወታቸው እርግጠኝነትን በማጣት የሚሰማቸው ጭንቀቶች ሌሎች አስገራሚ ስሜቶች ናቸው” ስትል ገልጻለች።
በሕዝቡ መካከል ሰፊ ፍርሃት አለ!
ከከባድ ሐዘን ባሻገር በሕዝቡ መካከል ሰፊት ፍርሃት አለ” በማለት የምትናገረው ዳንየሌ ቬላ፥ “ወንዶች ለውትድርና ለመመልመልና ወደ ጦር ግንባር ለመሄድ እንደሚፈሩ አስረድታለች። አገሪቱን ለቀው ከወጡ ሰባት ሚሊዮን የዩክሬን ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ ከውትድርና አገልግሎት የሸሹ መሆናቸውን ገልጻለች።
የቤተሰብ መለያየት ሌላው ከባድ ቁስል እንደሆነ ከኢየሱሳውያን ማኅበር የዕርዳታ አገልግሎት ሠራተኛ ማርታ ጋር ያደረገችውን ቆይታ በማስታወስ “በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ፍርሃት ነግሧል” በማለት እውነታውን መግለጿን ዳንየሌ ቬላ ተናግራለች። ባሎች፣ አባቶች እና ወንዶች ልጆች ለውጊያ መሄዳቸውን፣ መሰደዳቸውን ወይም ለደኅንነታቸው ሲሉ ወደ ሌላ ቦታ መሄዳቸውን ገልጻ፥ ሴቶች ስጋት ውስጥ ሆነው ሕፃናትን እና አረጋውያንን ለመንከባከብ ወደኋላ መቅረታቸውን አስረድታለች።
በዩክሬይን 3.7 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሉ
ለደህንነት አስተማማኝ ክልሎች ወደሚባሉ አካባቢዎች ጦርነቱ ከሚካሄድበት የዩክሬን ምሥራቃዊ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች እየመጡ ተጽእኖ ማሳደራቸው ታውቋል። በዩክሬን ውስጥ ሦስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ተፈናቃዮች መኖራቸውን የገለጸችው ዳንዬሌ ቤላ፥ እንደ ትራንስካርፓቲያ በመሳሰሉ አንዳንድ ክልሎች ከአራቱ ሰዎች መካከል አንዱ ተፈናቃይ እንደሆነ እና ክልሉ በዓለም ላይ በነፍስ ወከፍ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች ከሚያስተናግዱ እንደ ሊባኖስ ካሉ አገሮች ጋር እኩል እንደሆነ ገልጻለች።
በዩክሬይን የቤተ ክርስቲያን ሚና
በዚህ ውድመት መካከል ቤተ ክርስቲያን የቁሳቁስ፣ የሥነ-ልቦና ምክር አገልግሎት እና መንፈሳዊ ዕርዳታዎችን በመስጠት የድጋፍ ምሰሶ ሆና መቆሟን ዳንየሌ ቬላ ገልጻ፥ ቤተ ክርስቲያን ለሰዎች ባላት ጠንካራ ስሜት ማኅበረሰቡን እንደገና ለመገንባት የሚያስችል አስተማማኝ ቦታ እየሰጠች እንደምትገኝ አስረድታለች።
የኢየሱሳውያን ማኅበር የሕዝቡ የተስፋ ማዕከል በመሆን ለእናቶች እና ለወታደር ልጆች የተለያዩ ተነሳሽነቶችን በመጀመር የስነ-ልቦና ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደምትገኝ እና የካቶሊካዊ የዕርዳታ ድርጅት ካሪታስ ከኢየሱሳውያን ማኅበር የስደተኞች አገልግሎት ጋር በመተባበር ቤት ለወደመባቸው መጠለያዎችን በማዘጋጀት፣ የሕጻናት እንክብካቤ አገልግሎቶችን እና የትምህርት ፕሮግራሞችን በማስተባበር ላይ እንደሚትገኝ ዳንየሌ ቬላ አስረድታለች።
የዕርዳት ለጋሾች ልፋት
ሆኖም እነዚህ የተለያዩ ጥረቶች በቀጠሉበት በዚህ ወቅት የዓለም አቀፍ ዕርዳታ መቀነስ አሳሳቢነት እየጨመረ መምጣቱን የገለጸችው ዳንኤሌ ቬላ፥ የካሪታስ የዕርዳታ ድርጅት እና የኢየሱሳውያን ማኅበር ልገሳቸው እየቀዘቀዘ መምጣቱን ማስጠነቀቃቸውን ዳንየሌ ቬላ ገልጻ፥ “ጦርነቱ ቢያበቃም ሰብዓዊ ቀውሱ ይበልጥ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል” ስትል ተናግራለች።
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ ማድረግ
“ሕዝቡ ራሱ ትልቁ የተስፋ ምንጭ እና ጨለማ ቢኖርም የተስፋ ምልክቶች አሁንም አሉ” ስትል የተናገረችው ዳንኤሌ ቬላ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት በመካከላቸው እና በወደፊት ሕይወታቸው ላይ ያላቸው እምነት ቀጣይነት እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል” ብላለች።
ዩክሬይናዊው ኢየሱሳዊ ካኅን አባ ሚካሂሎቭ በአገሩ ውስጥ የሚሰጡትን ዘላቂ የሱባኤ እና የሐዋርያዊ አገልግሎት እንክብካቤን በማድነቅ፥ የተስፋ ምንጫቸው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እና ያለ እርሱ ድጋፍ ወደ ጦር ግንባር ሄደው መንፋሳዊ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ መናገራቸውን እና ይህ ተስፋ ጥንካሬን እንደሰጣቸው ተናግራለች።
ለአብሮነት መጮህ
ጦርነቱ እየገፋ በሄደ ቁጥር የዩክሬን ህዝብ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም እንደሚናፍቅ፣ ዩክሬንን እንደገና መገንባት እንደሚቻል ተስፋ እንደሚያደርጉ፣ ዩክሬይን ብዙ ሃብቶቿን አሳልፋ መስጠት እንደሌለባት፣ በስደት ላይ የሚገኙ ዜጎችም ወደ እገራቸው እንዲሚመለሱ ተስፋ ያደርጋሉ” ስትል ዳንኤሌ ተናግራለች።
ነገር ግን ይህን ሁሉ ብቻቸውን ማሳካት እንደማይችሉ፥ ዓለም ከእነርሱ ጋር እንዲሆን መፈለጋቸውን እና በአንድነት ለመቆም የውጭ ድጋፍ አስፈላጊ እንደሆነም አስረድታለች።