ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጥቅምት ወር ላይ በተካሄደው የሲኖዶስ ሁለተኛ ምዕራፍ ጉባኤ ወቅት ችግኝ ይዘው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጥቅምት ወር ላይ በተካሄደው የሲኖዶስ ሁለተኛ ምዕራፍ ጉባኤ ወቅት ችግኝ ይዘው  

ሲኖዶሳዊነት በናይጄሪያ በሚገኙ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴቶች የምስረታ ጥሪን እያገዘ እንደሚገኝ ተገለጸ

የሲኖዶሳዊነት መንፈስ በናይጄሪያ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለጥሪያቸው የሚተጉ ወጣት ልጃገረዶች እንዲፈጠሩ ፍሬያማ አስተዋጽዖ ማድረጉን የአውገስጢኖስ ማህበር አባል የሆኑት እህት ጀስቲና አዴጆ ገለጹ።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የኢየሱስ ምህረት የአውገስጢኖስ እህቶች ማህበር አባል የሆኑት እህት ጀስቲና አዴጆ፣ በሲኖዶሳዊነት መንፈስ ማዳመጥና እርስ በርስ ሃሳብ የመካፈል ባህል ገዳሙ በሚያስተዳድረው የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩ ልጃገረዶችን በማቋቋም ረገድ ባበረከተው አስተዋጽዖ ዙሪያ ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል።

እህት ጀስቲና ከቫቲካን ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ ልጃገረዶቹን ማዳመጥ ከእነሱ ጋር ይበልጥ እንዲግባቡ እድል እንደሰጣቸው እና ነፃነት እንደሚሰማቸው እንደሚያደርግ በመግለጽ፥ የገዳማዊያቱ ቀለል ያለ አቀራረብ እነርሱን በእርግጥ ለማዳመጥ ዝግጁ የሆኑ ሰዎች መኖራቸውን ያረጋግጥላቸዋል ብለዋል።

በመሆኑም ይሄንን አቀራረብ በመከተላቸው ሴቶቹ ወደ እነሱ ቀርበው የህይወት ተመክሮዋቸውን ለገዳማዊያቱ እንዲያካፍሉ ማስቻሉን ገልጸዋል።

በአሁኑ ጊዜ ‘ጉድ ካውንስል’ ተብሎ የሚጠራው የሴት ልጆች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተቋቋመበት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ ርዕሰ መምህር የሆኑት ሲስተር አዴጆ ይህ አካሄድ ልጃገረዶቹ “በሥነ ምግባር ቀና እንዲሆኑ፣ የበለጠ ግልጽ እንዲሆኑ፣ የበለጠ ራሳቸውን እንዲችሉ እና ዝግጁ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም በህይወት ዘመናቸው የሚያልሙትን ሥነ ስርዓት ያላት ሴት የመሆን ግብ ለማሳካት እንደረዳቸው አስታውሰዋል።

ሲኖዶሳዊ ተግባራት
ይህ የሲኖዶሳዊ ባህል በት/ቤቱ ውስጥ ዘላቂነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ተማሪዎቹ የህይወት ታሪካቸውን በቀላሉ እንዲያካፍሉ የሚያደርግ ስርዓት እና አካሄድ እንዳለው እህት አዴጆ አስረድተው፥ “ከእነሱ ጋር ዘወትር እንገናኛለን፣ ሴቶቹ በፈለጉት ጊዜ እንዲያገኙን እራሳችንን ዝግጁ እናደርጋለን” ካሉ በኋላ፥ በትምህርት ቤት ውስጥ የመመሪያ እና የምክር አገልግሎት መርሃግብር እንዳለ በመግለጽ፥ ምክንያቱም ግልጽ እና ቀለል ያለ ባህሪ ካሳየሃቸው ሴቶቹን ወደራስህ መሳብ ትችላለህ ብለዋል።

እህት አዴጆ አክለውም ከመምህራኑ ጋር ሁሌም በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያስችላቸው ብሎም እርስ በራሳቸው የሚሰማሙበት እና የሚደማመጡበት ስብሰባ እንደሚያደርጉ በመግለጽ፥ እነዚህ አካሄዶች ለሐዋሪያዊነታቸው እና ወጣቶችን ለማስተማር የበለጠ ቦታን እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።

ትምህርት የማስፋፋት ተልዕኮ
እህት አዴጆ በትምህርት ቤቱ ተግባራት እና የአውገስጢኖስ እህቶች ተልእኮ መካከል ስላለው ግንኙነት ሲገልጹ የትምህርት ቤቱ ተግባር እንደ አውግስጢኖስ እህቶች የተልዕኳቸው ዋነኛ ክፍል እንደነበር በማንሳት ወጣት ልጃገረዶችን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቅረብ ረገድ እገዛ ማድረጉን በአጽንዖት ገልጸዋል።

“ለእኛ እንደ አውገስጢኖስ እህቶች ለተልእኮአችን አስተዋፅኦ አድርጓል” ያሉት እህት አዴጆ፥ “ምክንያቱም በዚህ መንገድ፣ ክርስቶስን ወደ እነርሱ እነሱን ደግሞ ወደ ክርስቶስ እናመጣቸዋለን” ሲሉ ገልጸዋል።

ሲኖዶሳዊነት በማህበረሰብ ውስጥ
ሲኖዶሳዊነት ሁሉም ሰው እርስ በርስ ለመደማመጥ እና የራሱን ልብ ለመስማት ብሎም የእንደዚህ አይነት ልምዶችን ፍሬ ለመካፈል እድል ስለሚሰጥ በማህበረሰብ ህይወት ውስጥ አጋዥ ሆኖ ቆይቷል ያሉት እህት አዴጆ፥ “እንደ አውገስጢኖስ እህቶች፣ እንደ እህትማማች አንድ የሚያደርገንን የጋራ ነገር በማካፈል በጸሎታችን ውስጥ ብዙ ጊዜ እንድናገኝ በርካታ በሮችን ይከፍትልናል” ካሉ በኋላ “በተባረከው ቅዱስ ቁርባን ውስጥ ኢየሱስን ለማምለክ በጸሎት ቤት ውስጥ ተቀምጠናል ከዚያም ስንወጣ እንደ ማህበረሰብ እያንዳንዳችንን የሚነካውን ነገር እናካፍላለን” በማለት አብራርተዋል።

በጸጥታ የመጸለይ ፍሬዎች በአገልግሎት መገለጣቸው
የካልካታዋ እማሆይ ቴሬዛ በአንድ ወቅት “የዝምታ ፍሬ ጸሎት ነው፣ የጸሎት ፍሬ እምነት፣ የእምነት ፍሬ ፍቅር፣ የፍቅር ፍሬ አገልግሎት፣ የአገልግሎት ፍሬ ሰላም ነው” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

ሲኖዶሳዊው ሕይወት ከማህበረሰቡ ውጭ ለሌሎች እንዲካፈሉ የሚገፋፋው የአውገስጢኖስ የምሕረት እህትማማቾች ይህንን የእማሆይ ቴሬዛን ልምድ እንደሚካፈሉ በመግለጽ፥ “እንደ ማህበረሰብ አብረን ስንጓዝ፣ ከእኛ ጋር አብረው ለሚኖሩ ሌሎች ሰዎችም ልምዶቻችንን በማካፈል ወደ ፊት መሄድ እንችላለን” ብለዋል።

እህት አዴጆ በመጨረሻም “የሲኖዶሱ ህይወት ስለ ህይወታችን እና ስለ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የበለጠ እንድንካፈል ብዙ በሮችን ይከፍትልናል” በማለት አጠቃለዋል።
 

04 Feb 2025, 13:05