ፈልግ

በአሜሪካ የሚኖሩ ፈቃድ የተከለከሉ ስደተኞች በአሜሪካ የሚኖሩ ፈቃድ የተከለከሉ ስደተኞች  

የአሜሪካ ጳጳሳት ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ስደተኞችን በተመለከተ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ!

የአሜሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ከጣሊያን የቴሌቭዥን ጣቢያ TV2000 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በትራምፕ አስተዳደር ባለስልጣናት የቀረበባቸውን ውንጀላ በመቃወም በአሜሪካ የስደት ፖሊሲ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአሜሪካ የምትገኘው ቤተክርስቲያን ለስደተኞች ልባዊ አሳቢነት ከማሳየት ባሻገር “የእነሱ መነሻ” የበለጠ እንደሚያሳስባት ለሚሰጡት ጥቆማዎች ምላሽ መስጠታቸውን ቀጥለዋል።

ባለፈው ሳምንት፣ አዲስ የተሾሙት ምክትል ፕሬዘዳንት ጄ.ዲ. ቫንስ፣ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ሲሆኑ ጳጳሳቱ “ከሰብዓዊ ጉዳዮች” ይልቅ ቤተክርስቲያን ከፌዴራል መንግሥት የምታገኘው የገንዘብ ድጋፍ ያሳስቧቸዋል ወይ ብለው በአደባባይ ጠይቀዋል።

ንግግሩ የቤተክርስቲያኗን “ስደተኞችን የማገልገል ረጅም ታሪክ” ለኢየሱስ ትምህርት ታማኝ በመሆን ከአሜሪካ ጳጳሳት ጉባኤ ጠንካራ ምላሽን አስነሳ።

እ.አ.አ “በ1980 የአሜሪካ ጳጳሳት ይህንን አገልግሎት ለመፈጸም ከፌዴራል መንግሥት ጋር ትብብር ማድረግ የጀመሩት የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም ሸንጎ (USRAP) ሲፈጥር ነው” ሲሉ መግለጫው ገልጿል፣ አክሎም፣ “የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም በኩል በአሜሪካ የሚሰፍር እያንዳንዱ ሰው ተመርምሮ ጸድቋል ያለው መግለጫው “የቤተ ክርስቲያን የምሕረት እና የአገልግሎት ሥራ” ሆነው የሚቀጥሉትን ከአሜሪካ መንግሥት የሚገኘው ገንዘብ “ለእነዚህ ፕሮግራሞች ወጪ ለመሸፈን በቂ አይደለም” ብሏል።

የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ ሰጥተዋል

የአሜሪካው የጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ፣ “ለድሆች ብለን ከምናገኘው የበለጠ ገንዘብ እናወጣለን” ሲሉም ይህን አባባል አስተጋብተዋል።

ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ በጣሊያን የቴሌቭዥን ጣቢያ TV200 ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም የተጠቃው በትራምፕ ባለስልጣናት ጥቃት “እውነት ስላልሆኑ ነው” ብለዋል። “የተጠቀሱት ቃላቶች ውሸት ናቸው፣ እናም እኛ ወደ ንግግሮች ይዘት ሳንሄድ እውነትን በመናገር በጣም ንጹህ በሆነ መንገድ ምላሽ ለመስጠት ወስነናል” ብሏል።

ሊቀ ጳጳሱ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁል ጊዜ ሕጎች እንዲከበሩ አጥብቃ መሥራት እንደምትቀጥል ገልጸው፣ ነገር ግን በተጨባጭ ሁኔታዎች፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ቢገቡም ቤተ ክርስቲያን የተቸገሩትን መርዳት እንዳለባት አስረድተዋል። "እንዲህ እንድናደርግ የሚጠይቀን ራሱ ክርስቶስ ነውና እነርሱን ልንረዳቸው ይገባል"

ያሉት ሊቀ ጳጳሱ ከስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር በሚያደርጉት ስራ ችግር ላጋጠማቸው ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀው የስደተኞች ህግን ለማሻሻል ከኮንግረሱ ጋር መነጋገር መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል። "መቀየር እንዳለበት ሁላችንም ከሞላ ጎደል ተስማምተናል" ብሏል።

ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ በመቀጠል፣ “ለመነጋገር ፈቃደኞች ነን፣ ከፕሬዚዳንቱ ወይም ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር በመገናኛ ብዙኃን ሳይሆን ፊት ለፊት ለመነጋገርም ጠይቀናል። በዚህ መንገድ ተግባብተን ወደፊት ለመራመድ እንደምንሞክር አምናለሁ ብለዋል።

31 Jan 2025, 15:07