ፈልግ

Jerusalem day in Jerusalem

ዓለም አቀፉ የአብያተክርስቲያናት ምክርቤት በእየሩሳሌም በክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ የሆኑት ብጹእ አቡነ ጄሪ ፒሊ ፥ ክርስቲያን ወንጌላዊያን በእየሩሳሌም ያዘጋጁትን መንፈሳዊ ዝግጅት በመቃወም የአይውድ አክራሪ ሃይሎች ያስነሱት ብጥብጥ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ ፥ እየሩሳሌም የሦስት ሃይማኖቶች የጋራ መኖሪያ የሆነች ቅድስት ከተማ መሆኗን አክለው ተናግረዋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ባለፈው ግንቦት 20 በእየሩሳሌም የተካሄደውን የወንጌላውያን ህብረት ዝግጅት በመቃወም ቀኝ ዘመም አክራሪ የአይውድ አክቲቪስቶች ያደረጉትን ተቃውሞ በማውገዝ በቅድስት ሀገር ክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን የመቻቻል እና የትንኮሳ ድርጊት በቶሎ እንዲቆም አሳስበዋል።

ክስተቱ

ክስተቱ የተፈፀመው በእየሩሳሌም አርኪኦሎጂካል ፓርክ - ዴቪድሰን ማዕከል ፥ ከምዕራባዊው ግንብ አጠገብ እና የአይሁዶች ቅዱስ ስፍራ አከባቢ ፥ የእስራኤል ወንጌላውያን ደጋፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ለጸሎት ስነ ሥርዓት በተሰበሰቡበት ቦታ ነው።

ከዚያም በደርዘን የሚቆጠሩ የቀኝ አክራሪ እስራኤላውያን ተቃዋሚዎች ክርስቲያኖቹን ሲሰድቡና ሲተፉባቸው ፣ እይጮሁ ‘ከዚህ አከባቢ ለቃችሁ ሂዱ’ እያሉ መስኮቶቻቸውን ሲሰባብሩባቸው ነበር። ከእነዚህም መካከል ራቢ ዚቪ ታው የተባለ የቀኝ አክራሪው የኖኦም ፓርቲ መንፈሳዊ መሪ ፣ የአቴሬት ኮሃኒም ድርጅት ሊቀመንበር ማቲያሁ ዳን እና ለተሰበሰቡትት ሰዎች “ከፈለጉ በአብያተ ክርስቲያኖቻቸው ውስጥ እንጂ በአይሁዶች ቅዱስ ስፍራ በሆነው ቦታ ላይ እንዲጸሊዩ አንፈቅድም” ማለቱ የተዘገበው የኢየሩሳሌም ምክትል ከንቲባ አሪዬ ኪንግ ይገኙበታል።

ከተቃዋሚዎቹም መካከል አስሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

ጸረ-ስም ማጥፋት ሊግ፡ በአይሁድ ጽንፈኞች የተሰነዘረ የጥላቻ ንግግር

የተቃውሞ ሰልፈኞቹን ድርጊት “በኢየሩሳሌም ባሉ ክርስቲያን አምላኪዎች ላይ የአይሁድ ጽንፈኞች ያደረሱት አጸያፊ የጥላቻ ንግግር” ሲል የገለጸውን የእስራኤል ፀረ-ስም ማጥፋት ሊግ የተቃውሞ ድምጹን አሰምቷል።

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ብጹዕ አቡነ ጄሪ ፒሌይ ማክሰኞ ዕለት “ኢየሩሳሌም የሶስት ሃይማኖቶች ማለትም የአይሁዶች ፣ የክርስቲያኖች እና የእስላሞች የጋራ ቅድስት ከተማ ናት” በማለት ድርጊቱን አውግዘዋል። በማከልም “በሁኔታው ላይ የሚፈጸሙ ጥሰቶች መለያየትን ፣ ችግርን እና ዓመፅን ያመጣሉ" በማለትም አስጠንቅቀው ፥ ኢየሩሳሌምን የሁሉንም ህዝቦች መብት የምታከብር ቅድስት ከተማ ሆና እንድትቀጥል የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ይህን ድርጊት በማውገዝ እንዲደግፏቸው አሳስበዋል።

የተቃውሞ ሰልፉን በግልፅ ባይጠቅስም የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው “በኢየሩሳሌም የሚፈጸመውን የእምነት እና የአምልኮ ነፃነት ጥሰት እንዲሁም በከተማዋ በሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ጥቃት እንደሚያወግዝ” ገልጿል።

በክርስቲያን ማህበረሰቡ ላይ እየጨመረ የመጣው ጥቃት

በቅድስት ሀገር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በእስራኤል ማህበረሰብ ውስጥ ባሉ ጽንፈኞች የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና እንግልት እንዲሁም በአካባቢው የክርስቲያኖች መገኘት ላይ ከፍተኛ ስጋት ስላለባቸው ስጋቶች ደጋግመው አንስተዋል።

አብያተ ክርስቲያናትን እና ክርስቲያናዊ ንብረቶች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ፣ በክርስቲያን ቀሳውስት ላይ ከሚደርሰው አካላዊ እና የቃላት ጥቃት በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በእስራኤል ታሪክ አክራሪ ቀኝ ዘመም ጽንፈኞችን መንግሥት ሲያበረታታ ማየት የተለመደ ክስተት ሆኗል።

በቅርቡ ግንቦት 7 የፍልስጤም አል ናክባን ለማሰብ በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሊቀ ጳጳሳት እና የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በሰጡት መግለጫ በ ‘ስታተስ ኮኦ’ (Status Quo) ደንቦች መሰረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሁሉንም ማህበረሰቦች ጥበቃ በመደገፍ እና ዬትኛውንም ቅዱሳን ቦታዎችን በመጠበቅ ረገድ የላቀ ሚና እንዲጫወት በድጋሚ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወቃል።

 

01 June 2023, 21:21